Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙር በእንተ ጰራቅሊጦስ . .///ሐዋርያት ተባበሩ ሐዋርያት ተባበሩ በአዲስ | ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

መዝሙር በእንተ ጰራቅሊጦስ
.
.///ሐዋርያት ተባበሩ

ሐዋርያት ተባበሩ
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ
ቃሉን አስተማሩ/፪/

ከዐረገ በኋላ በዐሥረኛው ቀን
ወደ ዓለም ላከው ጰራቅሊጦስን
በዝግ ቤት ውስጥ ቆዩ ቀኑን ሲጠብቁ
የተሰጣቸውን ተስፋውን እስኪያውቁ

አዝ
ቀኑም ደረሰና ሃምሣኛው ዕለት
ተሰብስበው ሳሉ በአንድነት ጸሎት
መንፈስ ቅዱስ ታየ በነደ እሳት

አዝ
ያ የተናገረው ያ የተስፋ ቃል
ወረደ ከሰማይ በእሳት አምሳል
ጴጥሮስ አሳመነ ሦስት ሺ ነፍሳት
ያን ጊዜ ገሊላ በሰጠው ትምህርት

አዝ
ከሦስት አካል አንዱ መንፈስ ቅዱስን
ልኮ አናገራቸው ኹሉን በልሳን