Get Mystery Box with random crypto!

#ጾመ_ሐዋርያት ‹‹ይኽ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባ | ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

#ጾመ_ሐዋርያት

‹‹ይኽ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባለ ምዕመናን እንዳይጾሙት ብዙ ተለፍቷል..››

በየዓመቱ በዕለተ ሰኑይ የሚዠምሩ ሶስት አጽዋማት ብቻ አሉ ፡፡ ከእነርሱ መሀከል አንዱ ጾመ ሐዋርያት ነው ፡፡ ቅበላው በዕለተ እሑድ ይሆንና ጾሙ ሰኞ ይውላል ፡፡ የ2015 ዓ.ም ጾመ ሐዋርያት ግንቦት 28 ይገባል ፡፡

ይህ ጾም እራሱ ጌታቸን ኢየሱስ ክርቶስ ትንቢት የተናገረለት ጾም ነው፡፡
ይኽ ታላቅ ጾም የዛሬ 1902 ዓመት በፊት በራሳቸው በቅዱሳን ሐዋርያት የተጀመረ ጾም ነው ፡፡ ከሰባቱ አጽዋማት መሀከልም አንዱ ነው ፡፡
ፈሪሳውያ ጌታችንን ደቀ መዛሙርትህ አይጾሙም ብለው በጠየቁት ጊዜ እርሱም ‹‹ ሚዜዎች ሙሽራ ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን ? ነገር ግን መሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል ፤ በዚያ ጊዜም ይጾማሉ ፡፡ በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም ፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና ፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል ፡፡ በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም ፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል የወይን ጠጁም ይፈሳል ፡፡አቁማዳው ይጠፋል ፡፡ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል ሁለቱም ይጠባበቃሉ ፡፡›› ማቴ 9 ፥ 14-17 አላቸው ፡፡ይኽ ቃለ እራሱ ጌታችን መድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ስለ ጾመ ሐዋርያት የተናገረው ትንቢት ነው ፡፡

‹‹#መሽራው_ከተወሰደ በኃላ›› ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ካረገ በኃላ ማለት ሲኾን ይኽን ጾም ከዕረገት በኋላ የምንዠምረው ፤ ይኽን ምሳሌ በማድረግ ነው ፡፡ ዐሥር ቀን ዘግይቶ መዠመሩም የሐዋርያት ሰውነት ለጾሙ መዘጋጀት ነበረበትና ነው ፡፡

ይኽ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባለ ምዕመናን እንዳይጾሙት ብዙ ተለፍቷል ልናውቅ የሚገባው ነገር ግን ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ከማስተማራቸው በፊት ይህን ጾም ጾመዋል ፡፡ በዚህም ጌታችን የተናረው ተንቢት ተፈጽሟል፡፡ ከሰባቱ አጽዋማትን አንዱ ነው ፡፡ በዚህ ምክንያት ይህን ጾም ታላቅ እና ልዩ ያስብለዋል ፡፡ ይኽንን አውቀን ሁላችንም በሕግ በሥርዓት ልንጾመው ይገባል ፡፡