Get Mystery Box with random crypto!

Ahmed Habib Alzarkawi

የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi
የሰርጥ አድራሻ: @alzarkawihabib
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.53K
የሰርጥ መግለጫ

Hello World

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-02-20 22:35:34
ሰበር ዜና..!!!

ቱርክና ሶሪያ ድንበር አከባቢ ድጋሜ 6.4 Magnitude ርድአ መሬት ተከሰተ።

ያአላህ አንተ እዘንላቸው
7.1K views19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 18:58:33
ለሱልጣን አሊሚራህ ሐንፈሬ የምስጋና ዕውቅና ኘሮግራም በሠመራ ከተማ..

ለሀገር ባለውለታው ሱልጣን አሊሚራህ ሐንፈሬ የተዝኪራ አንድ ትናንት እና ዛሬ የዝግጅት ክፍል ሱልጣኑ የእሰልምና ሐይማኖት እና የማህበረሰባቸውን ላቅ ያለ አገልግሎት በመፈፀማቸው ዕውቅና የሰጠ ሲሆን የሱልጣን ልጅ አቶ ኡስማን አሊሚራህ ከኘሮፌሰር አደም ካሚል እጅ ተቀብለዋል።
3.8K views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 21:39:36 የሶማሌ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር በክልሉ መንግስት ተሰጥቶት የነበረው ፈቃድ ተሰረዘ

#Ethiopia | የሶማሌ ክልል ፍትህ ቢሮ “ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ፈጽሟል” ያለውን የሶማሌ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር ፈቃድ ሰረዘ።

የሶማሌ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር በበኩሉ እርምጃው “የመገናኛ ብዙሃንን ነጻነት ለማፈን የተወሰደ ነው” ሲል ውሳኔውን ነቅፏል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ 24 የጋዜጠኛ ማህበራት ውስጥ አንዱ የሆነው የሶማሌ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር የተመሰረተው ከሶስት ዓመት ገደማ በፊት በህዳር 2012 ዓ.ም ነው።

ማህበሩ የተቋቋመው፤ በክልሉ በጋዜጠኝነት ሙያ ረገድ ያለውን “አነስተኛ ልምድ ለማሳደግ” እና በጋዜጠኞች ላይ ለሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች “ድምጽ ለመሆን” በሚል ዓላማ እንደነበር መስራቾቹ ይናገራሉ።

በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ 86 ጋዜጠኞችን በአባልነት ያቀፈ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ማህበር፤ ፈቃዱ የተሰረዘው ከሁለት ሳምንት በፊት ነው።

የሶማሌ ክልል ፍትህ ቢሮ ለማህበሩ የሰጠውን ፈቃድ መሰረዙን ያስታወቀው፤ ለክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ጥር 23፤ 2015 በጻፈው ደብዳቤ ነው።

ማህበሩ ፈቃዱ የተሰረዘበት “ተገቢ ያልሆነ ድርጊት” በመፈጸሙ መሆኑን የክልሉ ፍትህ ቢሮ በደብዳቤው አስፍሯል።

ይህ ደብዳቤ የደረሰው የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ፤ የጋዜጠኞች ማህበሩ በክልልም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ “ፈቃድ የሌለው” መሆኑን በመግለጽ ለክልሉ የጸጥታ ቢሮ እና ፖሊስ ኮሚሽን ደብዳቤ ጽፏል።

የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ በዚሁ ደብዳቤው፤ የጋዜጠኞች ማህበሩ “ህዝብን የሚያሳስት እና የአካባቢውን መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል የተሳሳተ መልዕክቶችን ለማሰራጨት” በዝግጅት ላይ መሆኑን ጠቅሶ ነበር።

የጋዜጠኞች ማህበሩን “ማህበራዊ ንቅናቄ” (social mobilization) በማደራጀት የሚወቅሰው የኮሚዩኒኬሽን ቢሮው፤ የክልሉ የጸጥታ አካላት “በህጉ መሰረት ተገቢውን እርምጃ” በማህበሩ ላይ እንዲወስዱ አሳስቧል።

ፈቃዱ የተሰረዘበት የሶማሌ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር በክልሉ ፍትህ ቢሮ የተወሰደበትንም እርምጃም ሆነ በኮሚዩኒኬሽን ቢሮው በኩል የቀረበትን ወቀሳ አይቀበልም።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት አብዱራዛቅ ሀሰን፤ የማህበሩን ፈቃድ መሰረዝ “የመገናኛ ብዙሃንን ነጻነት ለማፈን የተወሰደ እርምጃ ነው” ሲሉ ተችተውታል።

የክልሉ ፍትህ ቢሮ በማህበሩ ላይ የወሰደው እርምጃ፤ በሶማሌ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ 15 መገናኛ ብዙሃን እና ወኪሎች “ከስራ እንዲታገዱ ከተላለፈው ውሳኔ ጋር የተያያዘ ነው” የሚል እምነት እንዳላቸውም የማህበሩ ፕሬዝዳንት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

አማኑኤል ይልቃል
2.9K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 21:39:29
2.8K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 11:32:35
ለተሰንበት ግደይ ምንድነው የገጠማት?

በአውስትራሊያ የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ በአዋቂ ሴቶች ለተሰንበት ውድድሩን በአንደኝነት ለማጠናቀቅ ከደቂቃዎች በታች ቀርተዋት ነበር። ከኋላዋ ኬንያዊያን አትሌቶች እና ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት እግር በእግር እየተከታተሉ ነበር።

ሆኖም ለተሰንበት ሪቫኑ ከፊቷ እንዳለ እየተመለከተች ቁርጭምጭሚቷ በመጎዳቱ ወደቀች። በአሰልጣኝዋ ድጋፍ ከወደቀችበት ተነስታ መቀጠል ብትችልም፣ ከውድድሩ ተሰርዛለች ወይም (disqualified ) ሆናለች።

ሱሉልታ ላይ በጃንሜዳው ውድድር በአስደናቂ አጨራረስ ወደ አውስትራሊያ ያቀናችው ለተሰንበት ድል አልቀናትም። ውድድሩን ኬንያዊቷ ቢቲሪሲ ቼቤት በአንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ፣ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ፅጌ ገብረሰላማ ሁለተኛ ሆና ማጠናቀቅ ችላለች።

Via Dawit Tolesa
Pics:African Athletics United
1.1K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 11:11:10
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ጎን ለጎን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ረዳት ዳይሬክተር ሜሪ ካትሪን ፒ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው በሁለትዮሽ ጉዳዮች እና በሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ላይ መምከራቸውም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
1.6K views08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 11:10:20
አሳዛኝ ዜና ከቱርክ

ለቀናት ሲፈለግ የቆየው ጋናዊው የቀድሞ የቼልሲ እና የኒውካስትል ዩናይትዱ ተጫዋች ክርስቲያን አትሱ በቱርክ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ህይወቱ አልፏል
1.6K views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 22:54:06
#Algeria

የአለም የመጀመሪያው ዩኒቨርስቲ የት ተሰራ መቼ ተሰራ?

የአለማችን የመጀመሪያው ዩኒቨርሲቲ የተሠራው ዛሬ አልጄሪያ በምትባለው ሀገር ነው።ስሙ Madaura University ይባላል።

ዩኒቨርሲቲው አልጀሪያ ውስጥ Souk Ahras በተባለው ቦታ ነው የተሠራው። ዩኒቨርስቲው ተገንብቶ የተጠናቀቀው በ 75 BC( ከ 2098 አመት በፊት) ነው።ዩኒቨርስቲውን የገነባው ንጉስ Syphax የተባለው የ Numidian ኢምፓየር መሪ ነው።

በዚህ ንጉስ ጊዜ ግዛቱ ለየት ያለ የባህል የኢኮኖሚ የእውቀት ና የቴክኖሎጂ እድገት ማሳየቱ ይታወሳል። እስከ ዛሬ አለም ላይ የሚታወቁ አንዳንድ የጥራጥሬ ዘሮችና የወይራ ዘይት እርሻ የተጀመረውና የተስፋፋው በዚሁ ጊዜ ነበር።

የሚገርመው የዩኒቨርስቲው ግንባታ ከታች እንደሚታየው ብዙ ተከታታይ ጦርነት ውድመት ጊዜና የአየር ፀባይ ለውጥ ተቋቁሞ ዛሬም ድረስ በጉልህ ይገኛል።

A.F.Z
698 views19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 19:44:38
ለክፉ ቀን ወዳጃችን ቱርኪዬ...

በቱርክ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ኢትዮጵያ ባላት አቅም የቁሳቁስ እና የነፍስ አድን ቡድን ለቱርክ ማበርከቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

ይገባታል ቱርኪዬ
3.5K views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 19:12:44
Breaking news

ጃፓን ልታስወነጭፈው የነበረው የጠፈር መንኮራኩር ሮኬት ከመሬት ሳይነሳ ከሸፈ።

H3 የተባለው የጃፓን ሮኬት ከመሬት ሆኖ ጠፈርን የሚቆጣጠር ሳተለይት ገና ሳይነሳ ነው የከሸፈው።

Tanegashima Space Center ከተባለው የጃፓን ጠፈር ምርምር ማእከል የተተኮሰው ሮኬት ፈንድቶ መውጣት አልቻለም ወይም አልተተኮሰም። ችግሩ የተከሰተው የሮኬቱ ሞተር ባጋጠመው ብልሽት ነው። ያ ማለት የሮኬቱ ሞተር መቀጣጠል ስላልቻለ ነው እንደ ሚዲያዎች ዘገባ።

በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ሲተላለፍ የነበረው የሮኬቱ ተኩስ ሊተኮስ እስከ መጨረሻው ቁጥር ተቆጥሮ ዜሮ ላይ ቢደርስም የ 57 ሜትሩ ሮኬት ካለበት ሳይነሳ እየጨሰ ተገትሮ ቀርቶዋል።

ዛሬ አርብ ለጃፓናውያን የሀዘን ቀን ሆኖዋል ተብሎዋል። የጃፓን ጠፈር ምርምር ተቋም(JAXA) ዋና ስራ አስኪያጅ Masashi Okada እዛው Live በተላለፈው ስነ ስርአት ላይ ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ በጠፈሩ መጨናገፍ የተሠማውን ሀዘን ገልፆ ይቅርታ ጠይቆዋል።

ስራ አስኪያጁ ችግሩ የሞተር አለመሆኑና ከኤሌክትሪክ ሲስተም ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልፆዋል።

በተቻለ ፍጥነት የችግሩን መንስኤ አጥንተን በቅርቡ ሌላ እንሞክራለን ብሎዋል።

ሙከራው ቢሳካ ኖሮ H3 የተባለው ይህ ሮኬት የጃፓኑ ALOS-3 የመሬት ሳተለይት ጋር በመገናኘት የአደጋ መከላከል ስራን ከማገዝ ውጪ ጃፓን የሰሜን ኮርያ ሚሳኤል ፕሮግራም በቅርበት እንድትከታተል ያስችላት ነበር። ከዛም በተረፈ የአለም ቁጥር አንድ ሀብታም በሆነው ደቡብ አፍሪካዊ Elon Musk በሞኖፖል በተያዘው የ space technology ኢኮኖሚ ገቢ ዘርፍ ጃፓን ጠንካራ ተወዳዳሪ ሆና እንድትወጣና የራሷ ገቢ እንድታገኝ ያስችላት ነበር።

Al jazeera
4.0K views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ