Get Mystery Box with random crypto!

Ahmed Habib Alzarkawi

የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi
የሰርጥ አድራሻ: @alzarkawihabib
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.53K
የሰርጥ መግለጫ

Hello World

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-02-07 19:33:26
ደስ የሚል ዜና !

የ6 ወር ልጇ እና እናት ከ29 ሰአት የህንፃ ፍርስራሽ ውስጥ ቆይታ በኋላ በህይወት አዳኙ ቡድን በደህና መውጣት ችለዋል።

አልሀምዱሊላህ
5.9K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 18:07:22
ያሳዝናል!በስተመጨረሻ የTDF አባላት እውነቱን መናገር ጀመሩ። ትርጉም በናትናኤል አስመላሽ

ተፃፈ በዳንኤል  ወዲ አቡነ እንድርያስ

"ለካ በህይወት መትረፍ ያሳዝናል"
ሁሌም ፈጣሪዬን ሳመሰግን፣ለኔ ያደረግክልኝ ለማን አደረግክለት እል ነበር፤ ዛሬ ግን ምን ነበር እንደተሰዉት ብሰዋ ኖሮ ለምን በቀላሉ ተመትቼ በህይወት ተረፍኩ ብዬ አምርሬ የቁጭት ለቅሶ አለቀስኩ።መስዋእትነት ተመኘሁ!ግን ማን በሰጠኝ!ወይኔ!እነዛ ከፊቴ የረገፉት ምልምል ወጣቶች ሁሉ ለካ ህዝብን ለማዳን አልነበረም ።
.
.
.
በመሃከላችን የወደቀው ሞርታር ፈንድቶ ለኔ እግሬ ላንተ ደሞ ልብህ ላይ አርፎ ወድያው ክቡር መስዋዕትነት የተቀበልከው የትግል ጓደኛዬ ዛሬ ትዝ አልከኝ፣ካንተ ጋር መስዋእት ሆኜ በነበር ብዬ ተመኘሁ!ግን ማን በሰጠኝ!በምን ዕድሌ!

ክቡር ህይወታችሁን የከፈላቹ ጓደኞቼ እንኳንም አሁን እየሆነ ያለው ነገር አላያችሁ፣ አልሰማችሁ፤ትገረሙ ነበር!ጉድ ነው!
እጃችን፣እግራችን እና የዓይን ብርሃናችን ያጣነው ለዚህ ነበር እንዴ?፣ከ800ሺ ወጣቶች ያጣነው፣እንደ ህዝብ ከሰው በታች የሆንነው ለእናንተ ስልጣን(ወንበር) ነው እንዴ?፣ይሔ ሁሉ ዋጋ ለእናንተ ስልጣን ነው እንዴ?

የትግራይ ህዝብ ሆይ እኔ በግሌ ይቅርታ ልጠይቅህ ፍቀድልኝ፤ታግዬ ነፃነትህ ስላላስጠበቅኩልህ፣ከዚህም አልፎ ማስደፈርያህ እና ማስገደያህ ሆንኩኝ፤ወደ ትግል የወረድኩት እኮ ነፃ ላወጣህ መስሎኝ ነበር፤ግን ለካ እንደዛ አይደለም።ይቅርታ!ይቅርታ አድርግልኝ!

ዘልአለማዊ ክብር ለጀግና ሰማእታት ይሁን
6.7K views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 17:58:56
ክርስቲያን አትሱ ከቱርክ ርዕደ መሬት ተርፎ ከፍርስራሽ ወጣ

የቀድሞው የቼልሲ እና ኒውካስትል ተጫዋች መጠነኛ ጉዳት ቢደርስበትም ከብዙ ድካም በኋላ ከፍርስራሽ እንዲወጣ ተደርጓል።
6.5K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 23:04:32
ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን

የ Saied Kiar A እናት ወደ አሄራ ሄደዋል
አላህ ይዘንላቸው:: ማረፊያቸውንም በጀነት ያድርግላቸው:: ለአንተ እና ለቤተሰቦችህም ሰብሩን ይለግሳችሁ
5.1K views20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 17:58:20
በደቡባዊ ቱርክ እና ሰሜናዊ ሶርያ ከ1 ሺ 800 በላይ ሰዎችን ሰለባ ያደረገው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የተረፉ ሰዎችን ለማዳን ርብርቡ ቀጥሏል።

7 ነጥብ 8 በሬክተር የተመዘገበውና ዛሬ ረፋድ ላይ የተከሰተው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ በቱርክ ብቻ ከ1 ሺ 100 በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ከ5 ሺ 300 በላይ የሚሆኑት ደግሞ አቁስሏል።

የሶሪያ ባለስልጣናት ስለአደጋው በገለፁት መሰረት 783 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ2 ሺ በላይ መቁሰላቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

በሁለቱም ሀገራት በመቶዎች የሚቆጠሩ ህንጻዎች ወድቀው ከፍርስራሹ በታች ያሉ ሰዎችን ለማዳን የነፍስ አድን ሰራተኞች ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ እየተረባረቡ ነው።

ቱርክ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ጥሪ ካቀረበች በኋላ የበርካታ ሀገራት መሪዎች ዕርዳታ ለመላክ ቃል ገብተዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ አደጋ ከቱርክ እና ሶሪያ በተጨማሪ በሊባኖስ፣ በቆጵሮስ እና በእስራኤል መሰማቱን የቢቢሲ ዘገባ ጠቁሟል።
1.2K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 21:19:50
በስልካችን ላይ ሊኖሩ የማይገቡ አደገኛ መተግበሪያዎቸ

በውስጣቸው አጥፊ ቫይረሶችን የያዙ ነገር ግን አገልግሎት የሚሰጡ በመመስል የተሰሩ መተግበሪያዎች አሉ።
ቀጥለው የተዘረዘሩ አፕሊኬሽኖች በስልካችን ላይ ተጭነው ካሉ በፍጥነት ልናጠፋቸው ይገባል።
7.2K views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 20:09:49
#ሱብሃን_አላህ
ይቺ ትንሽዬ ባግወርም ለራሱ ትንሽዬ የእንጨት ጎጆ ለመሥራት ትንንሽ እንጨቶችን ሰብስቧል

ይህ ትንሽ ኢንጅነር የአላህ ታላቅነት ምሳሌ ነው።

Hijra Tube ኢስላማዊ ድህረ ገፅ
7.5K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 19:40:58
የ 12 አመቱ ናይጄሪያዊ Chika Ofili አዲስ የሂሳብ ቀመር(Formula) ፈጠረ።

የማንኛውም ሙሉ ቁጥር የመጨረሻ Digit በ 5 ታባዛለህ ከዛ ከቀሪው ቁጥር ጋር ትደምረውና አዲስ ቁጥር ታገኛለህ። ያ ያገኘኸው አዲስ ቁጥር በ 7 divisible ከሆነ(ለ 7 ሚካፈል ከሆነ) የመጀመሪያው ቁጥርም ለ 7 የሚካፈል ነው ማለት ነው።

ይህ ያልተለመደ ና አስገራሚ ግኝቱ ነው የ TruLittle Hero Award ሽልማት ያስገኘለት።

TruLittle Hero Award በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለየት ያለ ግኝት ላገኙ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች ለተውጣጡ ሰዎች ልዩ ሽልማት ይሸልማል።

ናይጄሪያውያን ወጣቶች በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ና የእውቀት ዘርፎች ስመ ጥር ግኝቶች እያገኙ መሆኑ በተለምዶ አፍሪካውያን በፈጠራ ችሎታ ደከም ያለ ብቃት አላቸው የሚለውን ዘረኛ አስተሳሰብ እየሸረሸረ ይገኛል።

A. Home
7.4K views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 16:50:03
ሰላም ለሀገራችን..

በሰላም ስምምነቱ መሰረት የፌድራል መንግስት ከህወሓት የተረከበውን ከባድ መሳሪያ ወደ መሃል ሀገር ተጭኖ እየሄደ ነው።
7.9K views13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 17:08:52
በጄነራል አበባው ታደሰ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታዳራዊ ልዑክ በቱርክ ጉብኝት አደረገ
********

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰ የተመራው ወታደራዊ የልዑካን ቡድን በቱርክ ወታደራዊ ኃይል በተዘጋጀው ወታደራዊ ልምምድ ላይ ተሳትፏል።

የቱርክ ወታደራዊ ኃይል በክረምት ወቅት የተጣለበትን አገራዊ እና ዓለም-አቀፋዊ ግዳጅ ለመወጣት ያለውን አቅምና ዝግጁነት ለማሳየት ከጥር 24-25 ቀን 2015 ዓ.ም በምስራቅ ቱርክ በምትገኘው ካርስ ግዛት ወታደራዊ ልምምድ አካሂዷል።

በቱርክ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታዳራዊ ልዑክ በወታደራዊ ልምምድ ላይ ከመሳተፍ በተጨማሪ በወታደራዊ ዘርፍ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከቱርክ አቻው ጋር እንደሚመከር በአንካራ የኢዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
6.3K views14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ