Get Mystery Box with random crypto!

በደቡባዊ ቱርክ እና ሰሜናዊ ሶርያ ከ1 ሺ 800 በላይ ሰዎችን ሰለባ ያደረገው ከባድ የመሬት መንቀ | Ahmed Habib Alzarkawi

በደቡባዊ ቱርክ እና ሰሜናዊ ሶርያ ከ1 ሺ 800 በላይ ሰዎችን ሰለባ ያደረገው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የተረፉ ሰዎችን ለማዳን ርብርቡ ቀጥሏል።

7 ነጥብ 8 በሬክተር የተመዘገበውና ዛሬ ረፋድ ላይ የተከሰተው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ በቱርክ ብቻ ከ1 ሺ 100 በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ከ5 ሺ 300 በላይ የሚሆኑት ደግሞ አቁስሏል።

የሶሪያ ባለስልጣናት ስለአደጋው በገለፁት መሰረት 783 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ2 ሺ በላይ መቁሰላቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

በሁለቱም ሀገራት በመቶዎች የሚቆጠሩ ህንጻዎች ወድቀው ከፍርስራሹ በታች ያሉ ሰዎችን ለማዳን የነፍስ አድን ሰራተኞች ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ እየተረባረቡ ነው።

ቱርክ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ጥሪ ካቀረበች በኋላ የበርካታ ሀገራት መሪዎች ዕርዳታ ለመላክ ቃል ገብተዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ አደጋ ከቱርክ እና ሶሪያ በተጨማሪ በሊባኖስ፣ በቆጵሮስ እና በእስራኤል መሰማቱን የቢቢሲ ዘገባ ጠቁሟል።