2023-02-01 21:18:39
ጤና ቢሮ ከሚስተር ያሲን ሀቢብ በኋላ ያሳየው ለውጥ....
1ኛ:- ከቢሮ ዉስጥ ስንጀምር ሁሉም የቢሮ ሰራተኞች የስራ ድርሻቸውን አውቀው እንዲሰሩ የተመደቡበትን የስራ ሀላፊነት ከነተጠያቂነት ጭምር ተሰጥቷል።
2ተኛ:- ስቀጥል ድሮ በቢሮው በጥቅሉ ለሁሉም ሆስፒታሎችና ወረዳዎች ሲገዛ የነበረውን የመድኃኒት አቅርቦት ግዢ በማቋረጥ ወደ ሆስፒታሎች በጀት በማውረድ ሆስፒታሎች እንደየ አገልግሎታቸዉ የሚያስፈልጋቸውን የመድሃኒት ግዢ እንዲፈፅሙ መመሪያ በመስጠት የነበረውን ዉስብስብ የመድሃኒት ግዢ ችግር ተፈትተዋል።
3ተኛ:- ባለን ሆስፒታሎች የነበረውን የዘመናዊ ቴክኖሎጂ መመርመሪያ መሳሪያዎችን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ግዢ በመፈጸም ዱብቲ ሆስፒታልና መሀመድ አክሌ ሆስፒታል የሲቲስካን ባለቤት ተደርገዋል። በተጨማሪም በእነዚህ ሆስፒታሎች የነበረው የዉሃ ችግር እንዲፈታ መፍትሔ ተሰጥቷል።
4ተኛ:- ቁጥራቸው 20 የነበረውን ተንቀሳቃሽ የጤና ቡድን 10 ተንቀሳቃሽ ቡድን እንዲጨመር በማድረግ ወደ 30 እንዲሆኑ ተደርገዋል።
5ተኛ:- የጤና መድህን አገልግሎት በሁለት ወረዳዎች ተጀምሯል፣እንዲሁም በሌሎች ሁሉም ወረዳዎች እንዲጀመር በቁርጠኝነት እየተሰራበት ይገኛል።... ወዘተ..
<>በጦርነቱ ዉስጥ ለማመን የሚከብዱ ከባባድ ስራዎች ተሰርቷል። በሁሉም ግምባር ህይወት አድን አስቸኳይ የህክምና ቡድን በማቋቋም አመርቂ ስራ ተሰርቷል። በጦርነት ዉስጥ ሆነን ለቢሮው ተጨማሪ በጀት ሳይመደብ የጠላት ሀይል የወጡባቸዉ አከባቢዎች ላይ የሚገኙ የጤና ተቋማትን በፍጥነት ተጠግኖ ለህዝቡ አገልግሎት እንዲሰጥ በመደረግ ላይ ነበር።
➛ይህ ሁሉ ስራ የተሰራው አክሳሪ በሆነው ጦርነት ዉስጥ ሆነን እያለ መሆኑ ለየት ያደርገዋል።
➛ከጦርነት ማግስት ጦርነት ከነበረባቸው ቦታዎች የበራህሌ ጤና ጣቢያ እና የጭፍራ ጤና ጣቢ ወደ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በማሳደግ አገልግሎቱን ከፍ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፣ ሁሉም የጤና ተቋማት ወደ አገልግሎት መስጠት ደረጃ የመመለስ ስራ ተሰርቷል።
እንደቢሮም እንደክልሉም ዘንድሮ በቢሮ ዉስጥ ያደገውና የጤናን ስራ ከላይ እስከታች የሚያዉቀው ያሲን ሀቢብ ቢሮ ሀላፊ ተደርጎ መቆየቱ ከዘርፈ-ብዙ ችግሮች ለማሸነፍ ጠቅሞናል።
ክብር ይገባሃል my boss
Habib Aysaqita Apf
8.1K viewsedited 18:18