Get Mystery Box with random crypto!

Ahmed Habib Alzarkawi

የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi
የሰርጥ አድራሻ: @alzarkawihabib
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.53K
የሰርጥ መግለጫ

Hello World

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-02-16 21:32:14
እንኳን ደስ አለህ ጀግናችን..

የሌቪን 3000 ሜ የአለም የቤት ውስጥ ውድድር ሪከርድ ከ25 አመታት በኋላ ለኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ እጁን ሰጥቷል፣
3.7K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 21:04:15 #የሱልጣን_አሊሚራህ_የግብፅ_ጉብኝት!

ስለሱልጣን አሊሚራህ በተነሳ ቁጥር በሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘንድ የሚወደሱበት አይረሴ የሆነ ንግግራቸው ቀድሞ ይነሳል፡፡ እሱም የክብራችን መገለጫ የሆነው ባንዲራችን በማስመልከት የተናገሩት

" የኢትዮጵያ ባንዲራ እንኳን አፋር ግመሎቻችን ለይተው ያውቋታል"

..... በሚለው ታሪካዊ ንግግራቸው ሁሉም ይታወሳሉ፡፡ የኢትዮጵያ መለያ የሆነው ባንዲራና የአንድነታችን ጉዳይ በተነሳ ቁጥር በግንባር ቀደምነት የሳቸው ሥም አብሮ ይነሳል፡፡ ይህ የማይካድ ሐቅ ነው፡፡ ንግግራቸው ግልፅ ነበር፡፡ እሱም የኤርትራ አፋር ወደ ኤርትራ(የቀይባህር በራችን የነበረው አሰብ) መገንጠልን በ1983 በተደረገው የሠላም ኮንፈረንስ መድረክ ላይ ከመሪዎች የተቋመወ ብቸኛ መሪ ናቸው፡፡ ያኔ የሳቸውን ንግግር የእግር እሳት ሆኖባቸው መደረኩን ረግጠው ከወጡት ባለስልጣናት መካከል አንዱ የኤርትራው አንባገነን መሪ አቶ ኢሳየስ አንዱ ነበሩ፡፡ ይህ ቅሬታቸው ዛሬም ድረስ በታሪክ አምድ የአሰብ ጉዳይ በተነሳበት መድረክ ሁሌ በመነሳት ላይ ነው፡፡ ፡

ወደ ርእሰ ጉዳያችን ስንመለስ ሱልጣን አሊሚራህ በቀጥታም ሆነ በምስጢር ለተለየ የፖለቲካ አላማ ወደ ውጭ አገራት የሥራ ጎብኝት መድረግ የጀመሩት በ1957አ.ል ላይ ነበር፡፡ የጉዞው አላማ አፋርን በአረብ፡በአውሮፓ፡ በአሜሪካ ምድር የማስተዋወቅ ቀጥተኛ የውጭ ፈንድ ለማገኛትና በልማት ግዛቱን ለመለወጥ ያደረጉት የጉዞ ጅማሮ ነበር፡፡ የሱልጣን ጉብኝት በመጀመሪያ የጀመረው ከሱዳን ነበር፡፡ የጉዞ አመቻች " ሚሼል ኮትስ" የተባለ ኩባንያ የሥራ ሐላፊዎች ለሳቸው ባደረጉት የግብዥያ ጥሪ መሠረት ነበር፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ የሥራ ሐላፊነት በቁንጮ ይመራ የነበረው አቶ ከተማ ይፍሩ የተባለ ባለስልጣን ነበር፡፡ ከሱልጣን አሊሚራህ ጋር ጥብቅ የሆነ የወዳጅነት ግንኙነት ነበሯቸው፡፡ ሱልጣኑ ከኩባንያው ግንኙነት በተጨማሪም በወቅቱ በሱዳን የፖሎቲካ መድረክ ተቆጣጥረው የነበሩ ሁለት ቤተሰቦች ማለትም " የአል- ማህዲና የአል- ሚርጋኒ ቤተሰቦችን (እነ ሳዲቅ አልማህዲና አሊ አልሚርጋኒ ) ተገናኝተው ነበር፡፡ በተለይ የማህዲ የልጅ ልጅ (ሳዲቅ አልማህዲ ) ከፍተኛ አቀባበል አድርጎለት አስተናግዶታል፡፡ በተመሳሳይ ሰኢድ አሊ አልሚርጋኒ በወቅቱ በሽምግልና እድሜ ላይ ውስጥ ቢሆኑም በግኑኘታቸው ወቅት ለሱልጣን ምክርንም ጭምር " አፋርን ከቀረው አለም ጋር አስተዋውቋል፡፡ በዚህ ዙሪያ አልሰረህም ሥራ " የሚል አስተያየት እንደሰጣቸው ሱልጣኑ በአንደበታቸው ገልፀው ነበር፡፡ ከዚህ ቡሗላ ነበር ሱልጣን ከሌሎች መንግሥታት ጋር ይፋዊ ጎብኝት መድረግ የጀመሩት፡፡

ሱልጣን አሊሚራህ በ1957 በሱዳን የጀመሩት ይፋዊ የጉብኝት ጉዞ በቀጥታ ወደ ግብፅ ነበር ያመሩት፡፡ አቶ ከተማ ይፍሩ በግብፅ የኢትዮጵያ አንባሳደር እንድቀበሏቸው ትዕዛዝ አስተላለ፡፡ በዚህ መሠረት ሱልጣን ግብፅ - ካይሮ ሲገቡ የኢትዮጵያ አንባሳደር የነበሩት አቶ መለስ አንዶም(የጄኔራል አማን ወንድም) አውሮፕላን ጣቢያ ድረስ በመምጣት አቀባበል አደረጉላቸው፡፡ የግብፅ ጉብኝት ጉዞ የተመቻቸው በልጃቸው በመሀመድ አሊሚራህና አዲስ አበባ በሚገኘው የግብፅ ድፕሎማሲ በኩል ነበር፡፡ በግብፅ ቆይታ በርካታ ነገሮችን አሳክተዋል፡፡ ያኔ የግብፅ መሪ የነበሩት ጀማል አብዱል ናሲር ነበር፡፡ጥንታዊ የሆነችው የግብፅ መንግሥት የአውሳ ሱልጣኔት መኖርና አስፈላጊነት የምትገነዘብ አገር ስለነበረች የቀድሞ ግነንኙነታቸውን መሠረት በመድረግ ለሱልጣኑ ልዩ አቀባበልና መስተንገዶ አድርጋለች፡፡ በዚህ ጉብኝት ወቅት ሱልጣን አሊሚራህ ለጀማል አብዱልናስር መንግሥት ያቀረበው የመጀመሪያ ጥያቄ የሁለተኛ ደረጃና ከፍተኛ የትምህርት እሰስኮላርሽፕ እድል እንዲሰጣቸው ነበር፡፡ ይሄም ተቀባይነት አገኘ፡፡ በዚህ ሰአት የኢትዮጵያ ገዥ የነበረው ሐይለሥላሴ ይህን እድል ለሙሥሊሙ እሺ ብለው ስለማይፈቅዱ ነገሩ በሱልጣንና በግብፅ መካከል በምስጢር እንድያዝ ሆኖ ለትምህርት ወደ ግብፅ የሚሄዱ ተማሪዎች ሱልጣኑ በራሳቸው መንገድ በቀይባህር በኩል እንደሚልኩ በሥምምነት ላይ ደረሱ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሱልጣን ጥያቄ መሠረት በግብፅ መንግስት ድጋፍ በካይሮ ሬዲዮ የአፋርኛ ቋንቋ ኘሮግራም አየር ሰአት እንዲኖራቸው ተፈቀደላቸው፡፡ በዚህ መሠረት የአፋር ኘሮግራም በሬዲዮ የማስተላለፍ ስርጭት በአፋር ታሪክ ለመጀመሪያ የሬዲዬ ስርጭት የተጀመረው በካይሮ ከሚተላለፈው ጣቢያ ነበር፡፡ ይህ ማለት ከኢትዮጵያ የአፋርኛ ሬዲዮ ኘሮግራም ከመጀመሩ ቀደም ብሎ የካይሮ አፋርኛ ሬዲዮ የተከፈተ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ያኔ በካይሮ በሱልጣን ጥያቄ የተከፈተው ሬዲዮ ዛሬም ድረስ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ለ58 አመታት አገልግሎት ዛሬም ድረስ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የአፋር ተማሪዎች በባህር በኩል አድርገው የግብፅ መንግሥት በሰጧቸው የት/ት እድል ተጠቃሚ በመሆን ወደ ግብፅ ከ1957 ጀምሮ መጓዝ ጀመሩ፡፡ የግብፅ መንግስት ከሱልጣን አሊሚራህ ጉብኝት ቡሗላ ለአፋር ህዝብ በሩን ክፍት አደረገ፡፡

የአፋር ወጣቶች ከኢትዮጵያ፡ ከኤርትራ ፡ ከጀቡቲም ጭምር ወደ ካይሮ በመሄድ መማር ጀመሩ፡፡ በአል- አዝሃር ዩንቨርስቲ የተማሩ ወጣቶች በሐይማኖት እውቀት ተምረው ወደ አገራቸው በመመለስ በርካታ ኡለማዎችን ሊያፈሩ ችለዋል፡፡ በተመሳሳይም በአለማዊ እውቀት የቀሰሙት እተየለሌ ነው። ፕረዝዳንት ጋማል አብዱልናስር ለሌሎች አረብ አገራት ድጋፍ እንዳደረጉ ሁሉ ለአፋር ህዝብም በርካታ ውለታ ሊውሉ ችለዋል፡፡ለዚህ ነበር ጋማል አብዱልናስር በሞቱ ጊዜ በአውሳ የሐዘን ዱንካን ዘርግተው ሐዘናቸውን የገለጹት፡፡ የሱልጣን አሊሚራህ የግብፅ ስኬት ዛሬም ድረስ ህያው ሆኖ ቀጥለዋል፡፡መልካም ሥረራ ከመቃብር በላይ ይዉላል የሚባለው አባባል በተግባር ስገለፅ እንዲህ ነው ለካ ፡፡ ለማንኛውም ለዛሬው በዚሁ መሰናበቴ ነው ቸር ያሰማን፡፡

አሎ ያዮ

#ምንጭ:- የሱልጣን ህይዎት ትዝታዎች
4.0K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 21:04:15
3.8K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 20:34:54 መንግሥት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን፣ ፕሬዝዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና የቴክኒክ ረዳቶች ከ125 እስከ 380 በመቶ የመኖሪያ ቤት አበል መጨመሩን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጻፈውን ደብዳቤ ጠቅሶ ዘግቧል። መንግሥት የቤት አበል ጭማሪ የፈቀደው፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን በጥር ወር ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር መወያየታቸውን ተከትሎ ነው። እስካሁን ለመምህራን በወር የሚከፈላቸው ዝቅተኛው የቤት አበል 800 ብር ሲሆን፣ ከፍተኛው 2 ሺህ 500 ብር ደሞ ለፕሬዝዳንቶች የሚከፈል ነበር። ከቤት አበል በተጨማሪ በተለያዩ እርከኖች ለሚገኙ ኃላፊዎች የኃላፊነት አበል ጭማሪ መደረጉን ዘገባው ጠቅሷል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የቤት አበል፣ የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ጭማሪ ጥያቄያቸው ምላሽ ባለማግኘቱ፣ ከሦስት ወር በፊት ከፊል የሥራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር።
4.2K views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 19:12:53
3.9K views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 19:12:50 # የአፋር ልማት ማህበር(አፋልማ)....በአዲስ ሐይል የማህበረሰብ አጋርነቱን ሊያረጋግጥ ተነስቷል

የአፋር ልማት ማህበር የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ አወል አርባ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ሪፎርም አካሂዶ የነበሩበትን ክፍተቶች ለማስተካከል እና ማህበሩን በማስተዋወቅ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ተግባራት መከናወኑ ተነግሯል።

የክልሉ መንግስት ማህበሩ ከነበረበት አመቺ ካልሆነ ስፍራ እንዲወጣ ባለ ሶስት ፎቅ ህንጻ በከፊል በመሰራት ላይ የሚገኝ ገዝቶ ከመስጠት በተጓዳኝ ለገቢ ማስገኛ የሚሆን #3 መቶ ሺህ ካሬ የጨው መሬት ማህበሩ እንዲረከብ በማድረጉ ከዚህ በሚገኝ ገቢ የአርብቶ አደሩን አንገብጋቢ ችግሮች ለማቃለል እንደሚውል የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኑረዲን ሰዲቅ ገልጸውልናል።

በተለይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ አወል ወደ ክልሉ የሚመጡ የአለም አቀፍ ተቋማት ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ጨምሮ የሀገራት አምባሳደሮችና የመሳሰሉት ጋር ማህበሩን ወክየ ስለ አፋር ልማት ማህበር ገለጻ እንዳቀርብ ምቹ ሁኔታ ስለፈጠሩልን ከምንግዜውሞ በተሻለ ሰፊ ግንዛቤ እንድናስጨብጥ አግዞናል ሲሉም አቶ ኑረዲን ነግረውናል።
አሁን ላይ ማህበሩ አባላትን በስፋት ለማሳተፍ ከተደረገው እንቅስቃሴ በተጓዳኝ በሃገር ውስጥና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአጋርነት ድጋፍ እንዲሰጡ ባደረግነው እንቅስቃሴም #ከጠበቅነው በላይ ከኢትዮጵያውያን አበረታች ምላሽ አግኝተናል ሲሉም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።

ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ተፈናቅለው ለነበሩ ወገኖችም ሰብአዊ ድጋፍ በማቅረብ ማህበሩ ሰፊ ስራ ሰርቷል።
እንደ ግሎባል አልያስ ያሉ በአጋርነት ያልተቋረጠ ድጋፍ አድርገውልናል ያሉት አቶ ኑረዲን ተስ የተባለ #በእንግሊዝ የሚኖር የአፋር ወዳጅ ደግሞ የአፋር ቤቶችን በመስራት ድጋፍ አድርጎልናል ብለዋል።

በመጠጥ ውሃ ፣ በትምህርት ፣ በጤና የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት በኮንስትራክሽንና መልሶ ማቋቋምም ሰፊ ስራ ለመስራት ታቅዷል። የአፋር ልማት ማህበር በቀጣይ በልማትም ሆነ በክልሉ በሚያጋጥሙ የተፈጥሮ ክስተቶች ፈጣን ምላሽ መስጠት በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲደርስም ላስቀመጥነው አቅጣጫ የክልሉ መንግስት እየሰጠ ያለው ድጋፍና ክትትል አበረታች ነውም ብለዋል።

ማህበሩ ወደፊት በክልሉ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመፍታት #የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን ገዝቶ ለማሰማራትም እቅድ ይዟል።የማህበረሰቡን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የበኩሉን አስተዋጾ ለማበርከትም በመስኖ እርሻ ልማት ለመሰማራትም መታሰቡን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹልን።

የአፋር ልማት ማህበር ከተመሰረተ ከ 10 ዓመት በላይ ቢሆነውም በተለያዩ ምቹ ያልሆኑ ሁኔታዎች የሚገባውን ያህል እንቅስቃሴ ባያደርግም ቀደም ሲል የነበሩ ሃላፊዎች ህልውናው ተጠብቆ እንዲቆይ ጥረት አድርገዋል። ካለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ወዲህ ግን ሪፎርሞ አድርጎ የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል።


በዳጉ መጽሔት በተከ
4.0K views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 18:33:47 "በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በንግግርና ውይይት ተፈታ" Etv
4.2K views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 16:25:04
(በጅምላ ለመግዛት የምትፈልጉ ሁሉ)

መልካም ዜና ለሀገራችን አትክልትና ፍራፍሬ ግብይት..!!

የአፋር ክልል የዱብቲ ወረዳ አርብቶአደር ፅ/ቤት በማይታመን ዋጋ ትኩስና አሁን የተሰበሰበ የሽንኩርትና የቲማቲም ምርት ለገበያ ለማቅረብ ሙሉ ዝግጅት አድርጓል። ሆኖም ይሄን ምርት ለመግዛት የሚፈልግ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያለ ሰው በቀጥታ ከማሳው የሚፈልገውን ያህል መግዛት ይችላል። ከሰመራ 15 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ለትራንስፖርት ምቹ የሆነ መንገድ ስላለን ይሄ አትራፊ እድል እንዳያመልጣችሁ ተጠቀሙበት ይላችኋል የአፋር ክልል የዱብቲ ወረዳ የአርብቶ አደር ፅ/ቤት።

የዱብቲ ወረዳ አርብቶአደር ፅ/ቤት ሃላፊን ከታች ባለው ስልክ በቀጥታ መገኘት ይችላሉ

0973008870
5.3K views13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 07:25:01
#የኢትዮጵያን_ይግዙ
በመጀመሪያ ዙር በኢትዮጵያ መንግስት ለገበያ የቀረበ ስንዴ፧
➔ 3,000,000 ኩንታል ለዉጪ ገበያ
➔ 2,900,000 ኩንታል ለሀገር ዉስጥ ፍጆታ ለገበያ ቀርቧል።
3.1K views04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 19:49:39
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕወሃት ፕሪቶሪያ ላይ የተፈራረሙትን የዘላቂ ግጭት ማቆም ስምምነት "አዘጋጅቶ ያቀረበው የአሜሪካ መንግሥት ነው" ሲሉ ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። ኢሳያስ፣ አሜሪካ የግጭት ማቆም ስምምነቱ በጥድፊያ እንዲፈረም ያደረገችው፣ "ሕወሃትን ከሙሉ ሽንፈት ለማዳን" ነበር ብለዋል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በደረሱበት የሰላም ስምምነት አሜሪካ ደስተኛ አልነበረችም ያሉት ኢሳያስ፣ አሜሪካ የሁለቱን አገሮች የሰላም ስምምነት ለማደፍረስ ሕወሃትን በመሳሪያነት ተጠቅማበታለች በማለት ከሰዋል። ሕወሃት በጦርነቱ ወቅት የኤርትራን 72 ዒላማዎች ለመምታት አቅዶ ነበር ያሉት ኢሳያስ፣ ኤርትራ የሕወሃትን ጥቃት ለመመከት በብዙ መስኮች ከኢትዮጵያ ጋር በቅንጅት መስራቷን ይፋ አድርገዋል።
5.5K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ