Get Mystery Box with random crypto!

#የሱልጣን_አሊሚራህ_የግብፅ_ጉብኝት! ስለሱልጣን አሊሚራህ በተነሳ ቁጥር በሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘንድ | Ahmed Habib Alzarkawi

#የሱልጣን_አሊሚራህ_የግብፅ_ጉብኝት!

ስለሱልጣን አሊሚራህ በተነሳ ቁጥር በሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘንድ የሚወደሱበት አይረሴ የሆነ ንግግራቸው ቀድሞ ይነሳል፡፡ እሱም የክብራችን መገለጫ የሆነው ባንዲራችን በማስመልከት የተናገሩት

" የኢትዮጵያ ባንዲራ እንኳን አፋር ግመሎቻችን ለይተው ያውቋታል"

..... በሚለው ታሪካዊ ንግግራቸው ሁሉም ይታወሳሉ፡፡ የኢትዮጵያ መለያ የሆነው ባንዲራና የአንድነታችን ጉዳይ በተነሳ ቁጥር በግንባር ቀደምነት የሳቸው ሥም አብሮ ይነሳል፡፡ ይህ የማይካድ ሐቅ ነው፡፡ ንግግራቸው ግልፅ ነበር፡፡ እሱም የኤርትራ አፋር ወደ ኤርትራ(የቀይባህር በራችን የነበረው አሰብ) መገንጠልን በ1983 በተደረገው የሠላም ኮንፈረንስ መድረክ ላይ ከመሪዎች የተቋመወ ብቸኛ መሪ ናቸው፡፡ ያኔ የሳቸውን ንግግር የእግር እሳት ሆኖባቸው መደረኩን ረግጠው ከወጡት ባለስልጣናት መካከል አንዱ የኤርትራው አንባገነን መሪ አቶ ኢሳየስ አንዱ ነበሩ፡፡ ይህ ቅሬታቸው ዛሬም ድረስ በታሪክ አምድ የአሰብ ጉዳይ በተነሳበት መድረክ ሁሌ በመነሳት ላይ ነው፡፡ ፡

ወደ ርእሰ ጉዳያችን ስንመለስ ሱልጣን አሊሚራህ በቀጥታም ሆነ በምስጢር ለተለየ የፖለቲካ አላማ ወደ ውጭ አገራት የሥራ ጎብኝት መድረግ የጀመሩት በ1957አ.ል ላይ ነበር፡፡ የጉዞው አላማ አፋርን በአረብ፡በአውሮፓ፡ በአሜሪካ ምድር የማስተዋወቅ ቀጥተኛ የውጭ ፈንድ ለማገኛትና በልማት ግዛቱን ለመለወጥ ያደረጉት የጉዞ ጅማሮ ነበር፡፡ የሱልጣን ጉብኝት በመጀመሪያ የጀመረው ከሱዳን ነበር፡፡ የጉዞ አመቻች " ሚሼል ኮትስ" የተባለ ኩባንያ የሥራ ሐላፊዎች ለሳቸው ባደረጉት የግብዥያ ጥሪ መሠረት ነበር፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ የሥራ ሐላፊነት በቁንጮ ይመራ የነበረው አቶ ከተማ ይፍሩ የተባለ ባለስልጣን ነበር፡፡ ከሱልጣን አሊሚራህ ጋር ጥብቅ የሆነ የወዳጅነት ግንኙነት ነበሯቸው፡፡ ሱልጣኑ ከኩባንያው ግንኙነት በተጨማሪም በወቅቱ በሱዳን የፖሎቲካ መድረክ ተቆጣጥረው የነበሩ ሁለት ቤተሰቦች ማለትም " የአል- ማህዲና የአል- ሚርጋኒ ቤተሰቦችን (እነ ሳዲቅ አልማህዲና አሊ አልሚርጋኒ ) ተገናኝተው ነበር፡፡ በተለይ የማህዲ የልጅ ልጅ (ሳዲቅ አልማህዲ ) ከፍተኛ አቀባበል አድርጎለት አስተናግዶታል፡፡ በተመሳሳይ ሰኢድ አሊ አልሚርጋኒ በወቅቱ በሽምግልና እድሜ ላይ ውስጥ ቢሆኑም በግኑኘታቸው ወቅት ለሱልጣን ምክርንም ጭምር " አፋርን ከቀረው አለም ጋር አስተዋውቋል፡፡ በዚህ ዙሪያ አልሰረህም ሥራ " የሚል አስተያየት እንደሰጣቸው ሱልጣኑ በአንደበታቸው ገልፀው ነበር፡፡ ከዚህ ቡሗላ ነበር ሱልጣን ከሌሎች መንግሥታት ጋር ይፋዊ ጎብኝት መድረግ የጀመሩት፡፡

ሱልጣን አሊሚራህ በ1957 በሱዳን የጀመሩት ይፋዊ የጉብኝት ጉዞ በቀጥታ ወደ ግብፅ ነበር ያመሩት፡፡ አቶ ከተማ ይፍሩ በግብፅ የኢትዮጵያ አንባሳደር እንድቀበሏቸው ትዕዛዝ አስተላለ፡፡ በዚህ መሠረት ሱልጣን ግብፅ - ካይሮ ሲገቡ የኢትዮጵያ አንባሳደር የነበሩት አቶ መለስ አንዶም(የጄኔራል አማን ወንድም) አውሮፕላን ጣቢያ ድረስ በመምጣት አቀባበል አደረጉላቸው፡፡ የግብፅ ጉብኝት ጉዞ የተመቻቸው በልጃቸው በመሀመድ አሊሚራህና አዲስ አበባ በሚገኘው የግብፅ ድፕሎማሲ በኩል ነበር፡፡ በግብፅ ቆይታ በርካታ ነገሮችን አሳክተዋል፡፡ ያኔ የግብፅ መሪ የነበሩት ጀማል አብዱል ናሲር ነበር፡፡ጥንታዊ የሆነችው የግብፅ መንግሥት የአውሳ ሱልጣኔት መኖርና አስፈላጊነት የምትገነዘብ አገር ስለነበረች የቀድሞ ግነንኙነታቸውን መሠረት በመድረግ ለሱልጣኑ ልዩ አቀባበልና መስተንገዶ አድርጋለች፡፡ በዚህ ጉብኝት ወቅት ሱልጣን አሊሚራህ ለጀማል አብዱልናስር መንግሥት ያቀረበው የመጀመሪያ ጥያቄ የሁለተኛ ደረጃና ከፍተኛ የትምህርት እሰስኮላርሽፕ እድል እንዲሰጣቸው ነበር፡፡ ይሄም ተቀባይነት አገኘ፡፡ በዚህ ሰአት የኢትዮጵያ ገዥ የነበረው ሐይለሥላሴ ይህን እድል ለሙሥሊሙ እሺ ብለው ስለማይፈቅዱ ነገሩ በሱልጣንና በግብፅ መካከል በምስጢር እንድያዝ ሆኖ ለትምህርት ወደ ግብፅ የሚሄዱ ተማሪዎች ሱልጣኑ በራሳቸው መንገድ በቀይባህር በኩል እንደሚልኩ በሥምምነት ላይ ደረሱ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሱልጣን ጥያቄ መሠረት በግብፅ መንግስት ድጋፍ በካይሮ ሬዲዮ የአፋርኛ ቋንቋ ኘሮግራም አየር ሰአት እንዲኖራቸው ተፈቀደላቸው፡፡ በዚህ መሠረት የአፋር ኘሮግራም በሬዲዮ የማስተላለፍ ስርጭት በአፋር ታሪክ ለመጀመሪያ የሬዲዬ ስርጭት የተጀመረው በካይሮ ከሚተላለፈው ጣቢያ ነበር፡፡ ይህ ማለት ከኢትዮጵያ የአፋርኛ ሬዲዮ ኘሮግራም ከመጀመሩ ቀደም ብሎ የካይሮ አፋርኛ ሬዲዮ የተከፈተ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ያኔ በካይሮ በሱልጣን ጥያቄ የተከፈተው ሬዲዮ ዛሬም ድረስ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ለ58 አመታት አገልግሎት ዛሬም ድረስ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የአፋር ተማሪዎች በባህር በኩል አድርገው የግብፅ መንግሥት በሰጧቸው የት/ት እድል ተጠቃሚ በመሆን ወደ ግብፅ ከ1957 ጀምሮ መጓዝ ጀመሩ፡፡ የግብፅ መንግስት ከሱልጣን አሊሚራህ ጉብኝት ቡሗላ ለአፋር ህዝብ በሩን ክፍት አደረገ፡፡

የአፋር ወጣቶች ከኢትዮጵያ፡ ከኤርትራ ፡ ከጀቡቲም ጭምር ወደ ካይሮ በመሄድ መማር ጀመሩ፡፡ በአል- አዝሃር ዩንቨርስቲ የተማሩ ወጣቶች በሐይማኖት እውቀት ተምረው ወደ አገራቸው በመመለስ በርካታ ኡለማዎችን ሊያፈሩ ችለዋል፡፡ በተመሳሳይም በአለማዊ እውቀት የቀሰሙት እተየለሌ ነው። ፕረዝዳንት ጋማል አብዱልናስር ለሌሎች አረብ አገራት ድጋፍ እንዳደረጉ ሁሉ ለአፋር ህዝብም በርካታ ውለታ ሊውሉ ችለዋል፡፡ለዚህ ነበር ጋማል አብዱልናስር በሞቱ ጊዜ በአውሳ የሐዘን ዱንካን ዘርግተው ሐዘናቸውን የገለጹት፡፡ የሱልጣን አሊሚራህ የግብፅ ስኬት ዛሬም ድረስ ህያው ሆኖ ቀጥለዋል፡፡መልካም ሥረራ ከመቃብር በላይ ይዉላል የሚባለው አባባል በተግባር ስገለፅ እንዲህ ነው ለካ ፡፡ ለማንኛውም ለዛሬው በዚሁ መሰናበቴ ነው ቸር ያሰማን፡፡

አሎ ያዮ

#ምንጭ:- የሱልጣን ህይዎት ትዝታዎች