Get Mystery Box with random crypto!

መንግሥት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን፣ ፕሬዝዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና የቴክኒክ ረዳቶ | Ahmed Habib Alzarkawi

መንግሥት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን፣ ፕሬዝዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና የቴክኒክ ረዳቶች ከ125 እስከ 380 በመቶ የመኖሪያ ቤት አበል መጨመሩን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጻፈውን ደብዳቤ ጠቅሶ ዘግቧል። መንግሥት የቤት አበል ጭማሪ የፈቀደው፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን በጥር ወር ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር መወያየታቸውን ተከትሎ ነው። እስካሁን ለመምህራን በወር የሚከፈላቸው ዝቅተኛው የቤት አበል 800 ብር ሲሆን፣ ከፍተኛው 2 ሺህ 500 ብር ደሞ ለፕሬዝዳንቶች የሚከፈል ነበር። ከቤት አበል በተጨማሪ በተለያዩ እርከኖች ለሚገኙ ኃላፊዎች የኃላፊነት አበል ጭማሪ መደረጉን ዘገባው ጠቅሷል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የቤት አበል፣ የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ጭማሪ ጥያቄያቸው ምላሽ ባለማግኘቱ፣ ከሦስት ወር በፊት ከፊል የሥራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር።