Get Mystery Box with random crypto!

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕወሃት ፕሪቶሪያ ላይ የተፈራረሙት | Ahmed Habib Alzarkawi

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕወሃት ፕሪቶሪያ ላይ የተፈራረሙትን የዘላቂ ግጭት ማቆም ስምምነት "አዘጋጅቶ ያቀረበው የአሜሪካ መንግሥት ነው" ሲሉ ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። ኢሳያስ፣ አሜሪካ የግጭት ማቆም ስምምነቱ በጥድፊያ እንዲፈረም ያደረገችው፣ "ሕወሃትን ከሙሉ ሽንፈት ለማዳን" ነበር ብለዋል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በደረሱበት የሰላም ስምምነት አሜሪካ ደስተኛ አልነበረችም ያሉት ኢሳያስ፣ አሜሪካ የሁለቱን አገሮች የሰላም ስምምነት ለማደፍረስ ሕወሃትን በመሳሪያነት ተጠቅማበታለች በማለት ከሰዋል። ሕወሃት በጦርነቱ ወቅት የኤርትራን 72 ዒላማዎች ለመምታት አቅዶ ነበር ያሉት ኢሳያስ፣ ኤርትራ የሕወሃትን ጥቃት ለመመከት በብዙ መስኮች ከኢትዮጵያ ጋር በቅንጅት መስራቷን ይፋ አድርገዋል።