Get Mystery Box with random crypto!

Ahmed Habib Alzarkawi

የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi
የሰርጥ አድራሻ: @alzarkawihabib
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.53K
የሰርጥ መግለጫ

Hello World

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-02-24 18:32:35
ለቦረና ወገኖች እንድረስላቸው መንግስት ለቦረና ህዝብ ትኩረት ይስጥ....
5.8K views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 11:00:00
4.6K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 10:59:51
4.6K views07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 10:59:22
አፋር በግብርና አብዮት በዚህ ደረጃ ሲነቃነቅ በታሪክ የመጀመሪያው ነው...

እንደሚታወቀው የአፋር ክልል አብዛሃኛው መሬቱ ለእርሻ ተስማሚ የሆነ መሬት ነው እናም በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ህዝቡ ፊቱን ወደ እርሻ እንዲያዞር በፕሬዚዳንት ሀጂ አወል አርባ በተላለፈ ጥሪ ምክንያት የአፋር ህዝብ ጥሪውን ተቀብሎ በሁሉም የአፋር አከባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ የስንዴ ምርት እንዲመርት በተጠየቀው መሰርት አምርቶ እነሆ ዛሬ ምርቱን እየሰበሰበ ይገኛል። በአሁን ሰአት በአፋር ክልል ከስንዴ በተጨማሪ ከፍተኛ የቲማቲም ሽንኩርት ቃሪያ ምርት ወደ ተለያዩ የሀገራችን ክፍል ለገበያ እያቀረበ ይገኛል። የአፋር ህዝብ የሚሰራ የሚያሰራ መሪና መንግስት ካገኘ ምን ያህል የመሪውን ቃል አክባሪ ታታሪ ጀግና ህዝብ መሆኑ በተግባር እያሳየ ነው። እናም አንዴ ጎርፍ አንዴ አምበጣ አንዴ ጦርነት ቢያሳልፍም የአፋር ህዝብ ለምንም ችግር ሳይንበረከክ በጠንካራ ምራል ህዝቡ ንቅናቄውን እንደ ጠብቀ ወደ ልማት በማለት የተጀመረው የግብርና አብዮት ከዳር ለማድርስ ታጥቀው ተነስተዋል።

ኢንሻአላህ ኢትዮጵያ ሀገራችን ከተረጅነት ዝርዝር ወጥታ ወደ ረጅነት የምትቀየርበት ጊዜ ደርሷል።
4.3K views07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 20:03:35
ባለቤቷን በመግደል ወንጀል ተከሳ

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት በሱ ሳዶ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባት

#Ethiopia | አትሌት በሱ ሳዶ ከሁለት ወንድሞቿ እና ከሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በመሆን ባለቤቷን በመግደሏ፣ ድርጊቱን መፈጸሟ በመረጋገጡና እሷም የእምነት ክህደት ቃላን በመስጠቷና ባሏን እንደገደለችው በማረጋገጧ በሷና በአንደኛው ወንድሟ ላይ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

የ27 ዓመቷ አትሌት በሱ ሳዶ እና ባለቤቷ ተሻለ ታምሩ የአዳማ አትሌቲክስ ክለብ አባል ነበሩ።

በሱ ባለቤቷ “እንዳይሳካልን በቤተሰቤ፣ በእናቴ፣ በወንድሞቼ እና በእኔ ላይ ያስጠነቁላል” በሚል ይህንን ወንጀል እንደፈጸመች ቃሏን በሰጠችበት ወቅት መናገሯን ቢቢሲ አስነብቧል ።

በጥንዶቹ መካከልም ከገንዘብ ጋር በተያያዘ አለመግባባት እንደነበር ተከሳሿ በሰጠችው የእምነት የክህደት ቃል ላይ መስፈሩን ተገልጿል።

ከዚህ ግድያ በፊት ይህች አትሌት ሟችን እንደምታስገድለው ትዝትበት እንደነበር ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ወቅት እንደ ደረሰበት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቀሪዎቹ ሦስቱ ተጠርጣሪዎች ግን የዚያኑ ዕለት ሌሊት ስለጠፉ እስካሁን ድረስ ያሉበት እንዳልታወቀ እና በፖሊስ እየተፈለጉ መሆናቸው ተገልጿል።

የትዳር አጋሮቹ በቆይታቸው ልጅ ባይኖራቸውም የተለያየ ንብረት ማፍራታቸውን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።
2.2K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 18:23:24
ስለ አፋር ዳጉ ...

ዳጉ ገመድ አልባው የአፋር ባህላዊ የመረጃ ልውውጥ ስነስርአት አለም አቀፍ ይዘት ያለው መሆኑን የሚያረጋግጡ በውስጡ የሚያካትተው አንኳር ነጥቦች።

¤100% እውነተኛነቱ የተረጋገጠ መረጃ
¤ሁሉኑም ያከተተ የሰላም መረጃ
¤የማህበራዊ ጉዳይ መረጃ
¤የጤና መረጃ
¤የአየር ሆኔታ መረጃ
¤የኢንፖርት ኤክስፖርት ቢዝነስ መረጃ
¤የፀጥታ የደህንነት መረጃ
¤የእንስሳት ውሃ እና የግጦሽ መረጃ
¤የትብብርና የእርዳታ ጥሪ መረጃ

በጣም የሚደንቀው በአፋር ዘመናዊ መገናኛ ዘዴዎች ሳይኖሩ #በኤርትራ #በጂቡቲ #በኢትዮጵያ በሶስቱም ሀገር የለ ሆኔታ በጣም ከቆየ 2'ቀን ነው የሚዳረሰው ምናልባት በሌላ አከባቢዎች ከ30-60 ቀናት የሚደርስ መረጃ በአፋር 1-2ቀን ብቻ ነው የሚፈጀው።
ለምሳሌ፦አንድ መረጃ በሶስቱም ማዕዘናት እኩል ተሰራጭቶ በ24 ሰአት ይደርሳል።
.
አዘጋጅ፦Ahmed Habib Alzarkawi
3.3K views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 17:46:37
3.6K views14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 20:15:19
ነገ የምንፈልጋትን ሀገር ለመገንባት በዛሬው ትውልድ ላይ መሥራት ይኖርብናል-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ነገ የምንፈልጋትን ሀገር ለመገንባት በዛሬው ትውልድ ላይ መሥራት ይኖርብናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በልደታ ክፍለ ከተማ ሳር ቤት አካባቢ እንደ አዲስ የተገነባውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ስራ አስጀምረዋል፡፡

የስፖርት ማዘውተሪያው ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እና በሁሉም የበቃ ትውልድ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም በአካል፣ በሥነ ምግባር እና በሥነ ልቡና የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር የሚያግዝ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ገንብተናል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ነገ የምንፈልጋትን ሀገር ለመገንባት በዛሬው ትውልድ ላይ መሥራት ይኖርብናል ሲሉም ገልፀዋል።

በየአካባቢው ተመሳሳይ የስፖርት ማዕከላትን እያስፋፋን እንቀጥላለንም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
3.5K views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 18:39:25
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በስራ ላይ የነበሩ ሶስት ወጣቶች ከአራተኛ ፎቅ ላይ ወድቀዉ ህይወታቸው አለፈ

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የተሽከርካሪ ማሰልጠኛ ልዩ ቦታው ማደያ አካባቢ በግንባታ ላይ ካለ ህንጻ ላይ በስራ ላይ የነበሩ 3 ወጣቶች ወድቀዉ ህይወታቸው ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

አደጋው በዛሬው እለት ከቀኑ 9፡10 የተከሰተ ሲሆን ሶስቱ ሰራተኞች በስራ ላይ እንዳሉ ከአራተኛ ፎቅ ተንሽራተው የኤሌክትሪክ መብራት ሀይል ሽቦ ላይ ወድቀው ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን ተገልጿል፡፡

ይህን መሰል አደጋ በተደደጋሚ እየተከሰተ ነዉ ያሉት አቶ በቀለ ፤ በተለይም በቀን ስራ ላይ ያሉ ግለሰቦች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደርጉ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል
4.3K views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 16:29:51
ታዳጊ ማላኔ ለህክምና ወደ ጣሊያን ሀገር ሄዳለች...

ታደጊ ማላኔ የጎፋ ዞን መሎኮዛ ወረዳ ተወላጅ ስትሆን ፎቶዋ በማህበራዊ ሚድያ በስፋት ሲንሸራሸር የነበረ ሲሆን ይህችን ታዳጊ ለመርዳት ክብርት ዶ/ር ሰናይት ማሪዮ እና አርቲስት አለሙ አይዛ ባደረጉት ርብርብና ጥረት ተሳክቶላቸው ታዳጊዋ ለህክምና ወደ ጣሊያን መሄዱዋ ታውቋል። ለዚህም በጎ ስራቸው የመሎ ኮዛ ወረዳ አስተዳደር ለክብርት ዶክተር ሰናይት ማሪዮ እና ለአርቲስት አለሙ አይሳ የዕውቅና ምስክር ወረቀትና ምስጋና አቅርበዋል።

በዕውቅና መረሃ-ግብሩ ላይ የመሎ ኮዛ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤርምያስ ወሰኔን ጨምሮ ሌሎች የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የላሃ ከተማ ክቡር ከንቲባ አቶ ሰለሞን ስብሃቱና የላሃ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።
5.0K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ