Get Mystery Box with random crypto!

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በስራ ላይ የነበሩ ሶስት ወጣቶች ከአራተኛ ፎቅ ላይ ወድቀዉ ህይወታቸው አለ | Ahmed Habib Alzarkawi

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በስራ ላይ የነበሩ ሶስት ወጣቶች ከአራተኛ ፎቅ ላይ ወድቀዉ ህይወታቸው አለፈ

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የተሽከርካሪ ማሰልጠኛ ልዩ ቦታው ማደያ አካባቢ በግንባታ ላይ ካለ ህንጻ ላይ በስራ ላይ የነበሩ 3 ወጣቶች ወድቀዉ ህይወታቸው ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

አደጋው በዛሬው እለት ከቀኑ 9፡10 የተከሰተ ሲሆን ሶስቱ ሰራተኞች በስራ ላይ እንዳሉ ከአራተኛ ፎቅ ተንሽራተው የኤሌክትሪክ መብራት ሀይል ሽቦ ላይ ወድቀው ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን ተገልጿል፡፡

ይህን መሰል አደጋ በተደደጋሚ እየተከሰተ ነዉ ያሉት አቶ በቀለ ፤ በተለይም በቀን ስራ ላይ ያሉ ግለሰቦች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደርጉ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል