Get Mystery Box with random crypto!

ታዳጊ ማላኔ ለህክምና ወደ ጣሊያን ሀገር ሄዳለች... ታደጊ ማላኔ የጎፋ ዞን መሎኮዛ ወረዳ ተ | Ahmed Habib Alzarkawi

ታዳጊ ማላኔ ለህክምና ወደ ጣሊያን ሀገር ሄዳለች...

ታደጊ ማላኔ የጎፋ ዞን መሎኮዛ ወረዳ ተወላጅ ስትሆን ፎቶዋ በማህበራዊ ሚድያ በስፋት ሲንሸራሸር የነበረ ሲሆን ይህችን ታዳጊ ለመርዳት ክብርት ዶ/ር ሰናይት ማሪዮ እና አርቲስት አለሙ አይዛ ባደረጉት ርብርብና ጥረት ተሳክቶላቸው ታዳጊዋ ለህክምና ወደ ጣሊያን መሄዱዋ ታውቋል። ለዚህም በጎ ስራቸው የመሎ ኮዛ ወረዳ አስተዳደር ለክብርት ዶክተር ሰናይት ማሪዮ እና ለአርቲስት አለሙ አይሳ የዕውቅና ምስክር ወረቀትና ምስጋና አቅርበዋል።

በዕውቅና መረሃ-ግብሩ ላይ የመሎ ኮዛ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤርምያስ ወሰኔን ጨምሮ ሌሎች የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የላሃ ከተማ ክቡር ከንቲባ አቶ ሰለሞን ስብሃቱና የላሃ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።