Get Mystery Box with random crypto!

አፋር በግብርና አብዮት በዚህ ደረጃ ሲነቃነቅ በታሪክ የመጀመሪያው ነው... እንደሚታወቀው የ | Ahmed Habib Alzarkawi

አፋር በግብርና አብዮት በዚህ ደረጃ ሲነቃነቅ በታሪክ የመጀመሪያው ነው...

እንደሚታወቀው የአፋር ክልል አብዛሃኛው መሬቱ ለእርሻ ተስማሚ የሆነ መሬት ነው እናም በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ህዝቡ ፊቱን ወደ እርሻ እንዲያዞር በፕሬዚዳንት ሀጂ አወል አርባ በተላለፈ ጥሪ ምክንያት የአፋር ህዝብ ጥሪውን ተቀብሎ በሁሉም የአፋር አከባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ የስንዴ ምርት እንዲመርት በተጠየቀው መሰርት አምርቶ እነሆ ዛሬ ምርቱን እየሰበሰበ ይገኛል። በአሁን ሰአት በአፋር ክልል ከስንዴ በተጨማሪ ከፍተኛ የቲማቲም ሽንኩርት ቃሪያ ምርት ወደ ተለያዩ የሀገራችን ክፍል ለገበያ እያቀረበ ይገኛል። የአፋር ህዝብ የሚሰራ የሚያሰራ መሪና መንግስት ካገኘ ምን ያህል የመሪውን ቃል አክባሪ ታታሪ ጀግና ህዝብ መሆኑ በተግባር እያሳየ ነው። እናም አንዴ ጎርፍ አንዴ አምበጣ አንዴ ጦርነት ቢያሳልፍም የአፋር ህዝብ ለምንም ችግር ሳይንበረከክ በጠንካራ ምራል ህዝቡ ንቅናቄውን እንደ ጠብቀ ወደ ልማት በማለት የተጀመረው የግብርና አብዮት ከዳር ለማድርስ ታጥቀው ተነስተዋል።

ኢንሻአላህ ኢትዮጵያ ሀገራችን ከተረጅነት ዝርዝር ወጥታ ወደ ረጅነት የምትቀየርበት ጊዜ ደርሷል።