Get Mystery Box with random crypto!

ባለቤቷን በመግደል ወንጀል ተከሳ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት በሱ ሳዶ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባት | Ahmed Habib Alzarkawi

ባለቤቷን በመግደል ወንጀል ተከሳ

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት በሱ ሳዶ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባት

#Ethiopia | አትሌት በሱ ሳዶ ከሁለት ወንድሞቿ እና ከሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በመሆን ባለቤቷን በመግደሏ፣ ድርጊቱን መፈጸሟ በመረጋገጡና እሷም የእምነት ክህደት ቃላን በመስጠቷና ባሏን እንደገደለችው በማረጋገጧ በሷና በአንደኛው ወንድሟ ላይ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

የ27 ዓመቷ አትሌት በሱ ሳዶ እና ባለቤቷ ተሻለ ታምሩ የአዳማ አትሌቲክስ ክለብ አባል ነበሩ።

በሱ ባለቤቷ “እንዳይሳካልን በቤተሰቤ፣ በእናቴ፣ በወንድሞቼ እና በእኔ ላይ ያስጠነቁላል” በሚል ይህንን ወንጀል እንደፈጸመች ቃሏን በሰጠችበት ወቅት መናገሯን ቢቢሲ አስነብቧል ።

በጥንዶቹ መካከልም ከገንዘብ ጋር በተያያዘ አለመግባባት እንደነበር ተከሳሿ በሰጠችው የእምነት የክህደት ቃል ላይ መስፈሩን ተገልጿል።

ከዚህ ግድያ በፊት ይህች አትሌት ሟችን እንደምታስገድለው ትዝትበት እንደነበር ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ወቅት እንደ ደረሰበት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቀሪዎቹ ሦስቱ ተጠርጣሪዎች ግን የዚያኑ ዕለት ሌሊት ስለጠፉ እስካሁን ድረስ ያሉበት እንዳልታወቀ እና በፖሊስ እየተፈለጉ መሆናቸው ተገልጿል።

የትዳር አጋሮቹ በቆይታቸው ልጅ ባይኖራቸውም የተለያየ ንብረት ማፍራታቸውን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።