Get Mystery Box with random crypto!

Ahmed Habib Alzarkawi

የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alzarkawihabib — Ahmed Habib Alzarkawi
የሰርጥ አድራሻ: @alzarkawihabib
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.53K
የሰርጥ መግለጫ

Hello World

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-03-11 19:24:08
መልካም ዜና..!!!

በትናንትናው እለት የአፋልጉን ማስታወቅያ ለጥፈንባት የነበረችው ወጣት የስሚን ተገኝታለች ከቤተሰቧ ጋር በሰላም ተገናኝታለች። ለተጨነቃችሁ ሁሉ እናመሰግናለን ብለዋል ቤተሰቦቿ።
2.9K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 19:06:42
የአፋር ሱልጣኔት አልጋወራሽ አህመድ አሊማራህ ሰመራ ገቡ..!!!

የቀድሞ ቀድሞ የአፋር ሱልጣን የነበሩት የታላቁ የአባታችን የሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ ልጅ፣ እንዲሁም አባታቸውን ተክተወ ዙፋኑን ተረክበው የነበሩት የቀድሞው የአፋር ሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ወንድም የሆኑት አዲሱ ዙፋን ተረካቢው የአፋር ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ አፋር ሠመራ ገብተዋል።

ለአዲሱ ሱልጣንም በሠመራ ሱልጣን አሊ ሚራህ አየር ማረፊያ ደማቅ አቀበባል የተደረገላቸው ሲሆን በአቀባበሉም የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳን ክቡር ሐጂ አወል አርባ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ይገኙበታል።

እኛም “እንኳን ደህና መጣህ አባታችን ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ሀንፈሬ“ ለማለት እንደወዳለን
3.1K views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 21:11:48
የአፋልጉን ጥሪ..!!

ያስሚን ትባላለች የ14 አመት ልጅ ናት ኮምቦልቻ ሸዋበር ተክሌ ሆቴል አከባቢ ካለዉ መኖሪያ ቤቷ ወጥታ ከቀረች ዛሬ 4ተኛ ቀንዋ ነው እስካሁን ስለ የስሚን ምንም አይነት መረጃ አላገኘንም እናም የየስሚን ቤተሰቦች በጣም ተጨንቀዋል ልጅቱን ያየ ወይም መረጃ ያለው ሰዉ ከታች ባለው ስልክ ቁጥር ይደውልልን
( 0912940422 )

እባካችሁ ሁላችሁም ሼር በማድረግ ተባበሩን
6.7K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 15:49:56
መልካም ዜና ለሀገራችን አትክልትና ፍራፍሬ ጅምላ ነጋዴዎች..!!!

በየትኛውን የሀገራችን ክፍል ያለ የአትክልትና ፍራፍሬ ነጋዴ በፈለገው መጠንና ብዛት ተወዳጁን የበርሃ ሃብሃብ ምርት ለገበያ ተዘጋጅቷል።አጋጣሚ ሆኖ መጪው የረመዳን ወር በመሆኑ የሃብሃብ ምርት በጣም የሚያስፈልግ በመሆኑ አሁኑኑ ይዘዙን።

የዱብቲ ወረዳ እ/እ/ተ/ሃብት ፅ/ቤት ጥሪውን ያስተላልፋል።

0973008870
0911959612

t.me//afarmertgebeya
7.5K views12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 15:42:04 ሰበር...

የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረጽዮን!
የትግራይ ክልል ም/ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ!

ሆነው ተመርጠዋል!
5.3K views12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 23:51:23
ሶሪያዊው ህፃን ክሪስቲያኖን የማገኘት ህልሙ ተሳካለት..

በቅርቡ በሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ወደ ሶሪያ ከቀናው የሰኡዲ የነፍስ አድን ሰራተኞች አንዱ አንድን ህፃን ቃለ መጠየቅ ያደርግለታል እናም ልጁ የአለም ምርጡ ለአል ነስር የሚጫወተውን ክሪስቲያኖን ማየት እንደሚፈልግና እሱን ማገኘት ለሱ ትልቅ ህልሙ እንደሆ ይነግረዋል። ይህ ሰው ከህፃኑ ጋር ያደረገው ውይይትን የያዘ ቪዲዮ በትዊተር ገፁ ይለጥፋል።እናም በመጨረሻም ሶሪያዊው ህፃን ክሪስቲያኖ ሮናልዶን የማገኘት ህልሙ ተሳካለት።

Ahmed Habib Alzarkawi
892 views20:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 18:12:54
አፋር .....

127ኛዉ የአደዋ ድል መታሰቢያ በአል በአፋር ክልል በተለያዩ ዝግጅቶች በሰመራ በመከበር ላይ ነው ።

በድል መታሰቢያ በአሉ ላይ የሀገርመከላከያ ሠራዊት ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዪ የህብረተሰብ ክፍሎች አንዲሁም የፌደራልና የክልሉ ፖሊስ ተገኝተዋል ።

መልካም የአደዋ ድል በዓል ይሁንላችሁ

ሰመራ፣ የካቲት 23/2015 (አፋ.ብ.መ.ድ)
4.4K views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 23:18:56
«በሙሽራዋ ኪሎ ልክ የወርቅ ስጦታ»

በዱባይ የሚኖሩ አዲስ ፓኪስታናውያን ተጋቢዎች የባህል ልብስ ለብሰው እየተራመዱ መጡ ሙሽራዋ ትልቅ ደረጃ ላይ ደርሳ በአንደኛው ትከሻው ላይ ተቀመጠች እና ከተሰበሰቡት አንዱ ወርቁን በሌላ ሚዛን አስቀመጠ። ሙሽራዋ በወርቅ የምትመዝነውን ያህል ሰጣት። ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያ ከተዘዋወረ በኋላ አንዳንዶች የሚስት ዋጋ በወርቅ እና በገንዘብ እንደማይለካ ሲገልፀ፣ አንዳንዶች የሴቶችን ዋጋ እንደ ማንቋሸሽ ሲቆጥሩ ሌሎች ደግሞ እንደ ክብር ቆጥረዋታል። ለእሷ አድናቆት እና ፍቅር እና አክብሮት የሚገልጽበት መንገድ ነው በማለት ይሟገታሉ።
738 views20:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 17:37:56 የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ሃጂ አወል አርባ ለ127ኛው የአድዋ ድል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ...

የአድዋ ድል የአንድነት፣ የጅግንነትና የፅናት ተምሳሌት ነው። አባቶቻችን ሀገር ሊወር የመጣ ወራሪን ከጫፍ እስከ ጫፍ እንደ አንድ ሰው ልብ አንድነታቸውን አጠናክረው፣ ጀግንነትን አንግበው በመሰለፍ በፅናት በመፋለም ጠላት ያልጠበቀው ሽንፈት እንዲከናነብ ማድረግ ችለዋል። የእነሱ ድል ማድረግና አሸናፊነትም በወቅቱ የተጠናቀቀ ድል ብቻ ሳይሆን ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ለመላው ኢትዮጵያውያን፣ አፍሪካውያን፣ ብሎም ለጥቁር ህዝቦችና ለነፃነት ለሚታገሉ ህዝቦች ትልቅ አርአያ ሆኖ ሁሌም እየተገለጠ የሚጠቀስ ዋቢ መፅሀፍ እንዲሆን አድርገው አልፈዋል።

የአድዋ ድል ትልቁ ምስጢር የአባቶቻችን የጠነከረ አንድነት ፣ ሀገርን ያስቀደመ በተግባር የሚገለፅ ጀግንነትና ዓላማን ዳር ለማድረስ የነበራቸው የበረታ ፅናት ነው። ከምስራቅ፣ ከምዕራብ፣ ከደቡብ፣ ከሰሜን 'ሀገሬን' ብሎ የተሰባሰበው በርካታ ልዩነቶችን በማቻቻል ለአንድ አላማ ሀገርን ከወራሪና ከቅኝ ግዛት የማዳን የፀና የሀገር ፍቅርን በማሳየት ውድ የሆነውን የህይወት መስዋእትነት በመክፈል ሀገርን ከነሙሉ ክብሯ ለቀጣይ ትውልድ ማስተለለፍ ችለዋል።

የአድዋ ድል የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ ድል ነው። አባት አርበኞች አድዋ ላይ መስዋእትነት ሲከፍሉ ያለ ሀይማኖት፣ ብሄር ቋንቋና ማንነት ልዩነት በጋራ ነበር። ድሉም ለሆነ አካል ተቆርሶ የሚሰጥ እና ለሌላው የሚከለከል ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያውያን በጋራ መስዋእት የሆኑለት የጋራ የአሸናፊነት ታሪካችን ነው።

ይህን የጋራ የአሸናፊነት ታሪካችንንም አዲስ ታሪክ ፅፈን ለማለፍ ዋቢ መፅሀፍ በማድረግ በርካታ ቁም ነገሮችን በመቅሰም በርካታ ድሎችን ልናስመዘግብ ይገባናል። ኢትዮጵያችን የተሻለችና የበለፀገች፣ የዜጎቿን የምግብ ዋስትና ያረጋገጠች፣ ሰላማቸው የተጠበቀ ህዝቦች እንድንሆን ሁላችንም በየተሰማራንበት መስክ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል።

አባት አርበኞች ህይወታቸውን በመገበር ነፃነታችንን ማረጋገጥ እንደቻሉት፣ እኛ ደግሞ እውቀታችንን፣ ጊዜያችንን እና ጉልበታችንን በማቀናጀት ከድህነት ራሳችን ነፃ ማድረግ ይኖርብናል። ስራዎቻንን በሙሉ አንድነት እና በህብረት ፣በመተባበር እና በመደጋገፍ ፣ በጀግንነትና ፅናትን በመላበስ ማስኬድ ግድ ይለናል። ድህነትን ማሸነፍ የምንችለው ከፈጣሪ በታች በጋራ እጅ ለእጅ በመያያዝ እውነተኛ የሀገር ፍቅር እና አርበኝበትን በመሰነቅ የአንዳችን እድገትና ብልፅግና የአንዳችን እድገትና ብልፅግና መሆኑን በመገንዘብ በተቃራኒው ደግሞ ውድቀታችን የጋራ መሆኑን ጠንቅቀን በማወቅ ላለመውደቅና ወደ ተሻለ ከፍታና ብልፅግና በህብረት ለመሸጋገር የጀመርናቸውን የልማት ስራዎችን በፅናት ማስቀጠል ይኖርብናል።

የጀመርናቸው የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም፣ የስንዴ ልማት፣ የተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶችና የልማት ስራዎችን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በባለቤትነት ስሜት የበኩሉን ግዴታ በመወጣት እንደ አንድ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ አሻራውን ማኖር የዜግነት ግዴታ ነው።

የአድዋ ድል የቅኝ አልገዛም ባይነት፣ የባርነት እና የጭቆና ጠል እንቅስቃሴ ነው። የአሁንም ትውልድ የአባቶቹን ታሪክ በመድገም ለሁሉም ችግሮቹ ሀገር በቀል መፍትሄዎችን መነሻ በማድረግ ችግሮቹን በብልሀትና በጥበብ በመፍታት ከኢትዮጵያችን አልፎ ለአፍሪካ ብሎም ለአለማችን ችግሮች ሁነኛ መፍትሄ ሆኖ ሊገኝ ይገባል።

ለልማት ለእድገትና ለሰላም ጉዞው በየመንገዱ ላይ ለሚያጋጥሙ መሰናክሎችና ጊዚያዊ ችግሮች እጅ ባለመስጠት።

(ኢ.ፕ.ድ)
4.1K views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 17:37:54
3.9K views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ