Get Mystery Box with random crypto!

የአፋር ሱልጣኔት አልጋወራሽ አህመድ አሊማራህ ሰመራ ገቡ..!!! የቀድሞ ቀድሞ የአፋር ሱልጣን የ | Ahmed Habib Alzarkawi

የአፋር ሱልጣኔት አልጋወራሽ አህመድ አሊማራህ ሰመራ ገቡ..!!!

የቀድሞ ቀድሞ የአፋር ሱልጣን የነበሩት የታላቁ የአባታችን የሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ ልጅ፣ እንዲሁም አባታቸውን ተክተወ ዙፋኑን ተረክበው የነበሩት የቀድሞው የአፋር ሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ወንድም የሆኑት አዲሱ ዙፋን ተረካቢው የአፋር ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ አፋር ሠመራ ገብተዋል።

ለአዲሱ ሱልጣንም በሠመራ ሱልጣን አሊ ሚራህ አየር ማረፊያ ደማቅ አቀበባል የተደረገላቸው ሲሆን በአቀባበሉም የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳን ክቡር ሐጂ አወል አርባ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ይገኙበታል።

እኛም “እንኳን ደህና መጣህ አባታችን ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ሀንፈሬ“ ለማለት እንደወዳለን