Get Mystery Box with random crypto!

# የአፋር ልማት ማህበር(አፋልማ)....በአዲስ ሐይል የማህበረሰብ አጋርነቱን ሊያረጋግጥ ተነስቷል | Ahmed Habib Alzarkawi

# የአፋር ልማት ማህበር(አፋልማ)....በአዲስ ሐይል የማህበረሰብ አጋርነቱን ሊያረጋግጥ ተነስቷል

የአፋር ልማት ማህበር የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ አወል አርባ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ሪፎርም አካሂዶ የነበሩበትን ክፍተቶች ለማስተካከል እና ማህበሩን በማስተዋወቅ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ተግባራት መከናወኑ ተነግሯል።

የክልሉ መንግስት ማህበሩ ከነበረበት አመቺ ካልሆነ ስፍራ እንዲወጣ ባለ ሶስት ፎቅ ህንጻ በከፊል በመሰራት ላይ የሚገኝ ገዝቶ ከመስጠት በተጓዳኝ ለገቢ ማስገኛ የሚሆን #3 መቶ ሺህ ካሬ የጨው መሬት ማህበሩ እንዲረከብ በማድረጉ ከዚህ በሚገኝ ገቢ የአርብቶ አደሩን አንገብጋቢ ችግሮች ለማቃለል እንደሚውል የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኑረዲን ሰዲቅ ገልጸውልናል።

በተለይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ አወል ወደ ክልሉ የሚመጡ የአለም አቀፍ ተቋማት ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ጨምሮ የሀገራት አምባሳደሮችና የመሳሰሉት ጋር ማህበሩን ወክየ ስለ አፋር ልማት ማህበር ገለጻ እንዳቀርብ ምቹ ሁኔታ ስለፈጠሩልን ከምንግዜውሞ በተሻለ ሰፊ ግንዛቤ እንድናስጨብጥ አግዞናል ሲሉም አቶ ኑረዲን ነግረውናል።
አሁን ላይ ማህበሩ አባላትን በስፋት ለማሳተፍ ከተደረገው እንቅስቃሴ በተጓዳኝ በሃገር ውስጥና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአጋርነት ድጋፍ እንዲሰጡ ባደረግነው እንቅስቃሴም #ከጠበቅነው በላይ ከኢትዮጵያውያን አበረታች ምላሽ አግኝተናል ሲሉም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።

ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ተፈናቅለው ለነበሩ ወገኖችም ሰብአዊ ድጋፍ በማቅረብ ማህበሩ ሰፊ ስራ ሰርቷል።
እንደ ግሎባል አልያስ ያሉ በአጋርነት ያልተቋረጠ ድጋፍ አድርገውልናል ያሉት አቶ ኑረዲን ተስ የተባለ #በእንግሊዝ የሚኖር የአፋር ወዳጅ ደግሞ የአፋር ቤቶችን በመስራት ድጋፍ አድርጎልናል ብለዋል።

በመጠጥ ውሃ ፣ በትምህርት ፣ በጤና የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት በኮንስትራክሽንና መልሶ ማቋቋምም ሰፊ ስራ ለመስራት ታቅዷል። የአፋር ልማት ማህበር በቀጣይ በልማትም ሆነ በክልሉ በሚያጋጥሙ የተፈጥሮ ክስተቶች ፈጣን ምላሽ መስጠት በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲደርስም ላስቀመጥነው አቅጣጫ የክልሉ መንግስት እየሰጠ ያለው ድጋፍና ክትትል አበረታች ነውም ብለዋል።

ማህበሩ ወደፊት በክልሉ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመፍታት #የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን ገዝቶ ለማሰማራትም እቅድ ይዟል።የማህበረሰቡን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የበኩሉን አስተዋጾ ለማበርከትም በመስኖ እርሻ ልማት ለመሰማራትም መታሰቡን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹልን።

የአፋር ልማት ማህበር ከተመሰረተ ከ 10 ዓመት በላይ ቢሆነውም በተለያዩ ምቹ ያልሆኑ ሁኔታዎች የሚገባውን ያህል እንቅስቃሴ ባያደርግም ቀደም ሲል የነበሩ ሃላፊዎች ህልውናው ተጠብቆ እንዲቆይ ጥረት አድርገዋል። ካለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ወዲህ ግን ሪፎርሞ አድርጎ የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል።


በዳጉ መጽሔት በተከ