Get Mystery Box with random crypto!

በጄነራል አበባው ታደሰ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታዳራዊ ልዑክ በቱርክ ጉብኝት አደረገ ***** | Ahmed Habib Alzarkawi

በጄነራል አበባው ታደሰ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታዳራዊ ልዑክ በቱርክ ጉብኝት አደረገ
********

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰ የተመራው ወታደራዊ የልዑካን ቡድን በቱርክ ወታደራዊ ኃይል በተዘጋጀው ወታደራዊ ልምምድ ላይ ተሳትፏል።

የቱርክ ወታደራዊ ኃይል በክረምት ወቅት የተጣለበትን አገራዊ እና ዓለም-አቀፋዊ ግዳጅ ለመወጣት ያለውን አቅምና ዝግጁነት ለማሳየት ከጥር 24-25 ቀን 2015 ዓ.ም በምስራቅ ቱርክ በምትገኘው ካርስ ግዛት ወታደራዊ ልምምድ አካሂዷል።

በቱርክ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታዳራዊ ልዑክ በወታደራዊ ልምምድ ላይ ከመሳተፍ በተጨማሪ በወታደራዊ ዘርፍ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከቱርክ አቻው ጋር እንደሚመከር በአንካራ የኢዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።