Get Mystery Box with random crypto!

Breaking news ጃፓን ልታስወነጭፈው የነበረው የጠፈር መንኮራኩር ሮኬት ከመሬት ሳይነሳ ከሸ | Ahmed Habib Alzarkawi

Breaking news

ጃፓን ልታስወነጭፈው የነበረው የጠፈር መንኮራኩር ሮኬት ከመሬት ሳይነሳ ከሸፈ።

H3 የተባለው የጃፓን ሮኬት ከመሬት ሆኖ ጠፈርን የሚቆጣጠር ሳተለይት ገና ሳይነሳ ነው የከሸፈው።

Tanegashima Space Center ከተባለው የጃፓን ጠፈር ምርምር ማእከል የተተኮሰው ሮኬት ፈንድቶ መውጣት አልቻለም ወይም አልተተኮሰም። ችግሩ የተከሰተው የሮኬቱ ሞተር ባጋጠመው ብልሽት ነው። ያ ማለት የሮኬቱ ሞተር መቀጣጠል ስላልቻለ ነው እንደ ሚዲያዎች ዘገባ።

በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ሲተላለፍ የነበረው የሮኬቱ ተኩስ ሊተኮስ እስከ መጨረሻው ቁጥር ተቆጥሮ ዜሮ ላይ ቢደርስም የ 57 ሜትሩ ሮኬት ካለበት ሳይነሳ እየጨሰ ተገትሮ ቀርቶዋል።

ዛሬ አርብ ለጃፓናውያን የሀዘን ቀን ሆኖዋል ተብሎዋል። የጃፓን ጠፈር ምርምር ተቋም(JAXA) ዋና ስራ አስኪያጅ Masashi Okada እዛው Live በተላለፈው ስነ ስርአት ላይ ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ በጠፈሩ መጨናገፍ የተሠማውን ሀዘን ገልፆ ይቅርታ ጠይቆዋል።

ስራ አስኪያጁ ችግሩ የሞተር አለመሆኑና ከኤሌክትሪክ ሲስተም ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልፆዋል።

በተቻለ ፍጥነት የችግሩን መንስኤ አጥንተን በቅርቡ ሌላ እንሞክራለን ብሎዋል።

ሙከራው ቢሳካ ኖሮ H3 የተባለው ይህ ሮኬት የጃፓኑ ALOS-3 የመሬት ሳተለይት ጋር በመገናኘት የአደጋ መከላከል ስራን ከማገዝ ውጪ ጃፓን የሰሜን ኮርያ ሚሳኤል ፕሮግራም በቅርበት እንድትከታተል ያስችላት ነበር። ከዛም በተረፈ የአለም ቁጥር አንድ ሀብታም በሆነው ደቡብ አፍሪካዊ Elon Musk በሞኖፖል በተያዘው የ space technology ኢኮኖሚ ገቢ ዘርፍ ጃፓን ጠንካራ ተወዳዳሪ ሆና እንድትወጣና የራሷ ገቢ እንድታገኝ ያስችላት ነበር።

Al jazeera