Get Mystery Box with random crypto!

ለተሰንበት ግደይ ምንድነው የገጠማት? በአውስትራሊያ የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ በአዋቂ | Ahmed Habib Alzarkawi

ለተሰንበት ግደይ ምንድነው የገጠማት?

በአውስትራሊያ የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ በአዋቂ ሴቶች ለተሰንበት ውድድሩን በአንደኝነት ለማጠናቀቅ ከደቂቃዎች በታች ቀርተዋት ነበር። ከኋላዋ ኬንያዊያን አትሌቶች እና ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት እግር በእግር እየተከታተሉ ነበር።

ሆኖም ለተሰንበት ሪቫኑ ከፊቷ እንዳለ እየተመለከተች ቁርጭምጭሚቷ በመጎዳቱ ወደቀች። በአሰልጣኝዋ ድጋፍ ከወደቀችበት ተነስታ መቀጠል ብትችልም፣ ከውድድሩ ተሰርዛለች ወይም (disqualified ) ሆናለች።

ሱሉልታ ላይ በጃንሜዳው ውድድር በአስደናቂ አጨራረስ ወደ አውስትራሊያ ያቀናችው ለተሰንበት ድል አልቀናትም። ውድድሩን ኬንያዊቷ ቢቲሪሲ ቼቤት በአንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ፣ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ፅጌ ገብረሰላማ ሁለተኛ ሆና ማጠናቀቅ ችላለች።

Via Dawit Tolesa
Pics:African Athletics United