Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkun_zemede — Zemedkun Bekele (ዘመዴ) Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkun_zemede — Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
የሰርጥ አድራሻ: @zemedkun_zemede
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-24 19:54:23 ሰኞ ምሽት! ሚያዝያ 16/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ታንዛኒያ መግባታቸውን የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ደመቀ ዛሬ በታንዛኒያ የወደብ ከተማ ዛንዚባር ከአገሪቷ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሳሉሁ ጋር በኹለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደተወያዩ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴርን ጠቅሰው ዘግበዋል። ደመቀ ከፕሬዝዳንት ሳሉሁ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የታንዛኒያ መንግሥት በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር ሲሞክሩ ታንዛኒያ ላይ በቁጥጥር ስር ለዋሉ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ተገቢውን አያያዝ እንዲያደርግላቸው ፕሬዝዳንቷን ጠይቀዋል ተብሏል። ደመቀ ዛሬ ታንዛኒያ የገቡት፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግሥታቸው ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ነገ ማክሰኞ የሰላም ድርድር እንደሚጀምር በገለጡ ማግስት ነው። ደመቀ ከታንዛኒያ ቀጥሎ በኮሞሮስ፣ ቡሩንዲ እና ኡጋንዳ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገልጧል።

2፤ የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ዛሬ ባዋለው ችሎት በ"ኡትዮ ንቃት" የዩትዩብ ጣቢያ ባለቤት መስከረም አበራ ላይ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀናት መፍቀዱን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 13 ቀናት ከተጠርጣሪዋ እጅ ያዝኳቸው ባላቸው የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ላይ ምርመራ እንዲደረግለት ለሚመለከተው አካል ልኮ የምርመራ ውጤቱን መቀበሉን፣ የተጠርጣሪዋን የገንዘብ ዝውውር ለማወቅ ለባንክ ደብዳቤ መጻፉን፣ ከመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ማስረጃ ለማግኘት ጥያቄ ማቅረቡንና ሌሎች ቀሪ የምርመራ ሥራዎችን እያከናወነ መኾኑን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ፖሊስ መስከረምን ከሁለት ሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር ያዋላት፣ "ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት" ወንጀል ጠርጥሬያታለሁ በማለት ነበር።

3፤ የኬንያ መንግሥት ኬንያዊያን ዜጎችን ከሱዳን ማስወጣት መጀመሩን ደይሊ ኔሽን ጋዜጣ ዘግቧል። ኬንያ ዜጎቿን ማስወጣት የጀመረችው፣ በኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ግብጽና ሳዑዲ ዓረቢያ በኩል በየብስ እና በአውሮፕላን መኾኑን የጠቀሰው ዘገባው፣ 400 ያህል ኬንያዊያን ከሱዳን ለመውጣት መመዝገባቸውን አመልክቷል። 29 ኬንያዊያን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ደሞ ከሱዳን ገዳሪፍ በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውንና በየብስ ወደ ጎንደር መጓጓዛቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

4፤ ከሱዳኑ ግጭት የሸሹ 27 የሱማሊያ ዜጎች ባለፈው ቅዳሜ በመተማ ከተማ በከል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ድንበር አቋርጠው ኢትዮጵያ ከገቡት መካከል፣ የቀድሞው የቢቢሲ ዘጋቢ አብዲሰላም ሄረሪ እንደሚገኝበት ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ሱማሊያዊያኑ መተማ የገቡት፣ ከካርቱም በገዳሪፍ በኩል ወደ ጠረፋማዋ ጋላባት በአውቶብስ በመጓዝ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል። ከሱዳኑ ውጊያ ለሚሸሹ የውጭ አገር ዜጎች፣ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሚወስደው መስመር እስካሁን ደኅንነቱ አስተማማኝ እንደኾነ ይነገራል።

5፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ1133 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ1956 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 64 ብር ከ2567 ሳንቲም እና መሸጫው 65 ብር ከ5418 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ59 ብር ከ3352 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ60 ብር ከ5219 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
250 views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 13:44:04 አምባሳደር ሬድዋን:ዶ/ር ጌዲዎን:ጀነራል ደምሰው አመኑ:አቶ ከፍያለሁ አስራት እና አቶ ቦንሳ እውነቱ ከሸኔ ጋር ለመደራደር ዛሬ ታንዛኒያ ደርሰዋል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
263 views10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 07:17:45 Watch Video &share


63 views04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 07:06:19 ሰኞ ማለዳ! ሚያዝያ 16/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግሥታቸው ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ነገ የሰላም ድርድር ሊጀምር መኾኑን ትናንት የሰሜኑ ጦርነት እንዲቆም አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እውቅና ለመስጠት በተዘጋጀው ልዩ ስነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል። ዐቢይ፣ ከቡድኑ ጋር የሰላም ድርድር የሚደረገው በታንዛኒያ አስተናጋጅነት መኾኑን በንግግራቸው ላይ ጠቅሰዋል። መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ድርድር ለመጀመር ባለፈው መጋቢት ላይ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት የሚመሩት ኮሚቴ ማቋቋሙን አስታውቆ ነበር።

2፤ አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከመንግሥት ጋር የሰላም ድርድር ሊጀምር ነው ስለመባሉ ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል ። ቡድኑ፣ ለሰላም ድርድሩ ያቀረብኳቸው "ቅድመ ሁኔታዎች በመንግሥት ዘንድ ተቀባይነት አግኝተዋል" ብሏል።

3፤ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመርን ትናንት በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በትዊተር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። በውይይቱ ላይ፣ ደመቀ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕወሃት መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ዙሪያ ለሐመር ማብራሪያ እንደሰጧቸው ሚንስቴሩ ገልጧል። ደመቀ፣ ኢትዮጵያ በጦርነቱ ማግስት እያካሄደች ላለችው የመልሶ ግንባታና ማቋቋም እንቅስቃሴ አሜሪካ ተጨባጭ ድጋፍ እንድታደርግ መጠየቃቸውን ሚንስቴሩ ጨምሮ አመልክቷል።

4፤ የአዲስ አበባ መምህራን ማኅበር የከተማዋ አስተዳደር ለ29 ሺህ 500 አባላቱ የመኖሪያ ቤት ችግር መፍትሄ እንዲሰጥ ለከንቲባ አዳነች አቤቤ በጻፈው ደብዳቤ መጠየቁን ሪፖርተር አስነብቧል። ከንቲባ አዳነች በከተማዋ አስተዳደር ስር የሚገኙ መምህራን በማኅበር ተደራጅተው ቤት እንዲገነቡ ከኹለት ዓመት በፊት ያሳለፉት ውሳኔ እስካሁን ተግባራዊ እንዳልሆነ ማኅበሩ መግለጡን ዘገባው ጠቅሷል። ማኅበሩ መምህራን ለከፍተኛ የኑሮ ውድነት እንደተጋለጡ ጠቅሶ፣ የከተማዋ አስተዳደር ከችግሩ ጋር የሚመጣጠን የገንዘብ ድጎማ እንዲያደርግ መጠየቁንም ዜና ምንጩ አመልክቷል።

5፤ የሱዳን ጦር ሠራዊትና ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት በካርቱም እና ሌሎች ግዛቶች የሚያካሂዱት ውጊያ ቀጥሏል። አሜሪካ እና ብሪታኒያ ትናንት ዲፕሎማቶቻቸውን ከካርቱም በአውሮፕላን አስወጥተዋል። አሜሪካ ዲፕሎማቶቿን ስታስወጣ፣ ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ትብብር እንዳደረጉላት ገልጻለች። ሌሎች በርካታ የአውሮፓ አገራትም ዜጎቻቸውንና ዲፕሎማቶቻቸውን በማስወጣት ሂደት ላይ እንደኾኑ ዓለማቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
69 views04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 23:43:32 " የእኔን ወላጆች ጨምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች አሉን መመለስ መቻል አለባቸው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ዛሬ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ " ጦርነት ይብቃ፣ ሰላምን እናፅና " በሚል መሪ ቃል የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት በሰላም እና በንግግር እንዲቋጭ ላደረጉ አካላት የምስጋና መርሀ ግብር ተካሂዶ ነበር።

በዚህ ስነስርት ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት፣ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ አምባሳደር ማይክ ሀመር እና ሌሎችም በርካታ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተው ነበር።

በዚሁ መድረክ ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ንግግር አድርገው ነበር።

በንግግራቸው ምን አሉ ?

አቶ ጌታቸው ረዳ ፦

" የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል። ጠብመንጃ የመነቅነቅ አባዜ በፍፁም አይኖረም በዚህ አጋጣሚ ከትግራይ ይዤ የመጣሁት መልዕክት የሰላም እና የፍቅር መልዕክት ብቻ ነው።

አሁንም አራት ዓመት በላይ ትምህርት የሚባል ያላየሁ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ልጆች አሉን ትምህርት ቤት መግባት መቻል አለባቸው።

አሁንም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች አሉን የኔን ወላጆች ጨምሮ መመለስ መቻል አለባቸው ፣ ስራቸውን መስራት መቻል አለባቸው።

ሁሉንም ነገር ለሰላም በሚሆን መልኩ እናድርገው ፣ ከጎረቤት ወንድም ህዝቦች በተለይም ከአማራ እና ከአፋር ጋር ሊያጋጨን የሚገባ ነገር ሳይኖር ፣ ግጭት ተፈጥሮ በሁላችንም ዘንድ ታሪክ ይቅል ሊለው የማይገባ ብዙ ጥፋት ተፈፅሟል።

ይሄንን ነገር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ዘግተን ቋንቋችንን የሰላም እና የመከባበር፣ ልዩነቶቻችንን በመከባበር ፣ በመቻቻል እና በህግ ብቻ ለመፍታት እስከሰራን ድረስ በጋራ ሀገራችንን ከመገንባት አልፈን ፣ በሁለቱም በሶስቱም ጎረቤት እህትማማች፣ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ተጥሮ ያለውን መቃቃይ የሚመስል ስሜት አስወግደን ወደ ተሻለ ደረጃ የማናሳድግበት ምክንያት የለም።

... አሁንም ደግሜ ደጋግሜ የምለው የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል ፤ አንገሽግሾታል ይህ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አካባቢዎች እንደ ኖርማል የሚወሰዱ ህፃናትን ትምህርት ቤት በሰዓቱ መላክ መመለስ የሚመስሉ ጉዳዮች፣ ማረስ፣ ማለስለስ፣ ማጨድ መዝራት የሚባሉ ነገሮች ይናፍቁታል ፈጥነን ወደዚህ መመለስ መቻል አለብን።

ሁሉንም ለማድረግ የሁሉንም አቅም መጠቀም ያስፈልገናል። ከምንም ነገር በላይ ጠንካራ ሰራተኛ የሆነው የትግራይ ህዝብ ተመልሶ ወደ ስራው ተሰማርቶ የሰላም ችግር ሳይሆን ምን ያክል አተረፍኩ ምን ያክል አመረትኩ በሚል ፉክክር ውስጥ እንዲገባ ለማስቻል የጀመርነውን ጥረት አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል፤ ሁሉም ክልሎች የዚህ እንቅስቃሴ አካል እንደሚሆኑ እምነቴ የፀና ነው ፤ ከፌዴራል መንግሥት ጋር የጀመርናቸው መልካም ግንኙነቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ አውንታዊ በሆነ መልኩ ትልቅ ደረጃ ላይ እንደሚደርሱ እምነታችን የፀና ነው። "

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
90 views20:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 23:43:31
የእኔ ወላጆችም ተፈናቅለዋል!
89 views20:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 22:52:32
#ድርድር

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሸኔ ወይም እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ገልጸዋል።

ይህንን ያሳወቁት ፥ በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ግጭት በሰላም ስምምት እንዲቋጭ ቁልፍ ሚና ለነበራቸው አካላት የምስጋና እና የዕውቅና ሥነ ስርዓት በተካሄደበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ የወለጋ ሕዝብ እፎይ እንዲል ሁሉም ወገን የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል በቀጣዩ ሣምንት በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት የተመራ ልዑክ ወደ መቐለ እንደሚያቀና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሳውቀዋል።

ልዑኩ የሁሉንም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ያካተተ እንደሚሆን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡
#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
105 views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 11:13:50
የትዊተርን አዲስ አሰራር ተከትሎ የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የበርካታ ታዋቂ ሰዎች የማረጋገጫ ምልክት ተነሳ።

ታዋቂው ቱጃር ኤሎን መስክ በ44 ቢሊዮን ዶላር ትዊተርን ከገዛው በኋላ በመተግሪያው ላይ የመጡ ለውጦች በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ከሆኑ ሰንበትበት ብሏል።

ከዚህም ውስጥ አንዱ ትዊተር ታዋቂ ግለሰቦች የሚሰጠውን የማረጋገጫ መልክት (Twitter verification) በክፍያ መጀመሩ ይጠቀሳል።

ለግለሰብ በወር 8 ዶላር ለድርጅት ደግሞ 1000 ዶላር ማስከፈል የጀመረው መተግበሪያው ከትላንት ጀምሮ ክፍያ ያልፈጸሙ ያላቸውን አካውንቶች የማረጋገጫ ምልክታቸውን አንስቷል።

ከእነዚህ ውስጥም የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሲጠቀስ፥ የሌሎች በርካታ ታዋቂ ግለሰቦች ተሰጥቶ የነበረው የማረጋገጫ ምልክት ተነስቷል። (ለአብነት የተጠቀሱ ገጾችን በምስሉ ይመልከቱ)

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
182 views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 22:52:49
ሰበር ዜና

ኤርትራ ጦሯን ወደ ሱዳን ድንበር አስጠጋች
ኤርትራ በሱዳን የተከሰተውን ጦርነት ምክንያት በማድረግ ካሳላ ወደ ሚባል የሱዳን አዋሳኝ ድንበር በርካታ ሰራዊት ሰሞኑን አስጠግታለች። ካሳላ የሚባለው ቦታ አሁን ላይ በሱዳን የሚተዳደር ቢሆንም ካሳላ በታሪክ የኤርትራ ነው ብለው የሚያምኑም አሉ። ሱዳናዊያን ደግሞ ኤርትራ ጦሯን ያስጠጋችው ካሳላን በሀይል ለመውረር ነው እያሉ ይገኛሉ። ኤርትራ ግን ጦሯ ዳር ድንበሯን ለማስከበር እንዳስጠጋች ምንጮች ገልጸዋል።
በሌላ መረጃ
ከ10 በላይ ሄሊኮፕተሮች ዛሬ ደሴ ዙሪያ ለብዙ ደቂቃዎች መታየታቸውን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል። በገራዶ አካባቢም አድርገው ወደ ሱዳን ድንበር እንዳቀኑም ተገልጿል። የቅኝት ስራ እንደሚሰሩ ይገመታል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
76 views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 19:12:43 ቅዳሜ ምሽት! ሚያዝያ 14/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ ዛሬ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ የአውቶብስ መጓጓዣ አገልግሎት መጀመሩን ድምጸ ወያኔ ዘግቧል። ከኹለት ዓመታት በኋላ ዛሬ መንገደኞችን ማጓጓዝ የጀመረው፣ ሰላም ባስ የግል ትራንስፖርት ኩባንያ መኾኑን ዘገባው አመልክቷል። በዛሬው የመጀመሪያ ጉዞ 54 መንገደኞች ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ እንደተጓዙ ዜና ምንጩ ገልጧል።

2፤ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት ሲሚንቶ ለማገበያየት ያዋጣው እንደኾነ ለመወሰን ጥናት እያደረገ መኾኑን ሪፖርተር አስነብቧል። ድርጅቱ ጥናቱን አጠናቆና ከመንግሥት አስፈቅዶ ግብይቱን ከጀመረ፣ በኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ግብይት ሲሚንቶ በድርጅቱ ታሪክ የመጀመሪያው ይኾናል። የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት አንድን ምርት ለማገበያየት ፍቃድ የሚያገኘው ከንግድ ሚንስቴር ነው። የሲሚንቶ የአገር ውስጥ ምርትና ግብይት በአሁኑ ወቅት በበርካታ ችግሮች ተተብትቦ የተያዘ እንደዳኾነ በተደጋጋሚ ተነግሯል።

3፤ የሱዳን ጦር ሠራዊትና የፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት የውጭ አገር ዜጎችን ከካርቱም ለማስወጣት አውሮፕላን ጣቢያውን በከፊል ለመክፈት መስማማታቸውን ዛሬ በየፊናቸው አስታውቀዋል። ይህንኑ ተከትሎ፣ የአሜሪካ፣ ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ እና ቻይና ዜጎችና ዲፕሎማቶች በወታደራዊ አውሮፕላን ከካርቱም እንዲወጡ ኹኔታዎችን ማመቻቸተን የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ባወጣው መግለጫ ገልጧል። ሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎቿን በሰሜናዊቷ ፖርት ሱዳን በኩል ዛሬ በማስወጣት የመጀመሪያዋ አገር ኾናለች።

4፤ የሱዳን ጦር ሠራዊትና ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት የሚያደርጉት ውጊያ ዛሬም መቀጠሉን የውጭ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች ከትናንት ጀምሮ ለኢድ አልፈጥር በዓል ተግባራዊ እንዲኾን በተናጥል የተስማሙበት የ72 ሰዓታት ተኩስ አቁም ተፈጻሚ ሳይኾን ቀርቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎ ሙሉ ተኩስ አቁም ስለማድረግና በረድዔት ሠራተኞች ደኅንነት ዙሪያ ከተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር በስልክ እንደተነጋገሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

5፤ የሱማሊያ መንግሥት የአፍሪካ ኅብረት ሰላም ተልዕኮ ከቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ በኋላ ቆይታው በድጋሚ እንዲራዘም ፍቃደኛ መኾኑን ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቧል። የፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ መንግሥት የኅብረቱ ሰላም አስከባሪዎች ቆይታ ይራዘም የሚለውን ጥያቄውን ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ያዋጡ የቀጠናው አገሮችና ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ እንዲቀበሉት ማግባባት መጀመሩን ዘገባው ጠቅሷል። አፍሪካ ኅብረት ቀደም ሲል ከሱማሊያ መንግሥት ጋር በደረሰው ስምምነት መሠረት፣ የኅብረቱን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ከመጭው ሰኔ ጀምሮ ደረጃ በደረጃ በመቀነስ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ታህሳስ ወር ሙሉ በሙሉ ከአገሪቱ እንዲወጡ ታቅዶ ነበር። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
133 views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ