Get Mystery Box with random crypto!

#ድርድር የኢትዮጵያ መንግሥት ከሸኔ ወይም እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ከሚጠራው ታጣቂ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

#ድርድር

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሸኔ ወይም እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ገልጸዋል።

ይህንን ያሳወቁት ፥ በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ግጭት በሰላም ስምምት እንዲቋጭ ቁልፍ ሚና ለነበራቸው አካላት የምስጋና እና የዕውቅና ሥነ ስርዓት በተካሄደበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ የወለጋ ሕዝብ እፎይ እንዲል ሁሉም ወገን የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል በቀጣዩ ሣምንት በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት የተመራ ልዑክ ወደ መቐለ እንደሚያቀና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሳውቀዋል።

ልዑኩ የሁሉንም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ያካተተ እንደሚሆን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡
#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja