Get Mystery Box with random crypto!

የትዊተርን አዲስ አሰራር ተከትሎ የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የበርካታ ታዋቂ ሰዎች የማረጋገጫ ም | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የትዊተርን አዲስ አሰራር ተከትሎ የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የበርካታ ታዋቂ ሰዎች የማረጋገጫ ምልክት ተነሳ።

ታዋቂው ቱጃር ኤሎን መስክ በ44 ቢሊዮን ዶላር ትዊተርን ከገዛው በኋላ በመተግሪያው ላይ የመጡ ለውጦች በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ከሆኑ ሰንበትበት ብሏል።

ከዚህም ውስጥ አንዱ ትዊተር ታዋቂ ግለሰቦች የሚሰጠውን የማረጋገጫ መልክት (Twitter verification) በክፍያ መጀመሩ ይጠቀሳል።

ለግለሰብ በወር 8 ዶላር ለድርጅት ደግሞ 1000 ዶላር ማስከፈል የጀመረው መተግበሪያው ከትላንት ጀምሮ ክፍያ ያልፈጸሙ ያላቸውን አካውንቶች የማረጋገጫ ምልክታቸውን አንስቷል።

ከእነዚህ ውስጥም የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሲጠቀስ፥ የሌሎች በርካታ ታዋቂ ግለሰቦች ተሰጥቶ የነበረው የማረጋገጫ ምልክት ተነስቷል። (ለአብነት የተጠቀሱ ገጾችን በምስሉ ይመልከቱ)

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja