Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkun_zemede — Zemedkun Bekele (ዘመዴ) Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkun_zemede — Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
የሰርጥ አድራሻ: @zemedkun_zemede
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-22 14:21:56 ሰበር ዜና
በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚገኙበት የሱዳን አል-ሁዳ ወህኒ ቤት ተሰበረ 

እስር ቤቱ የወንጀለኛ ቡድን መሪዎችና እጽ አዘዋዋሪዎች የሚገኙበት ሲሆን በፖሊሶች ሲያዙ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያንም የታሰሩበት ነበር 


ከካርቱም በስተምስራቅ የሚገኙ አካባቢዎች በጀነራል አህመድ ሃምዳን ዳጋሎ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ትልቁ የአል-ሁዳ ወህኒ ቤት መሰበሩ ተሰምቷል።

እስር ቤቱ ብዙ ኢትየጵየዊያን በሱዳን የፀጥታ ኃይሎች የሚታሰሩበት ሲሆን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እስረኞቹ እንዲለቀቁ ማድረጉን የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ተናግረዋል።

ከካርቱም 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኦምዱሩማን መንገድ የሚገኝና የወንጀለኛ ቡድን መሪዎች፣ አደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎች እና ከመኖሪያ ፈቃድ ጋር በተገናኘ ብዙ ኢትዮጵያውያን የሚታሰሩበት እንደነበረ ምንጮቻችን ተናግረዋል።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እስረኞቹን ማስለቀቁን ተከትሎ ሃሳባቸውን የሰጡ ምንጮች ታስረው ለነበሩት ኢትዮጵያውያን መፈታት በጎ ቢሆንም በከባድ ወንጀል የታሰሩ ሰዎችም መፈታታቸው ስጋት ፈጥሯል።

ግጭቱ ከተጀመረ ጀምሮ 15 የሚደርሱ ኢትዮጵያዊያን በጦርነቱ መገደላቸው የተገለፀ ሲሆንሲሆን በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቂ መረጃ እየሰጠ ባለመሆኑና ስለተገደሉት ዜጎች ጉዳይ መንግስት ያለው ነገር አለመኖሩ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ትችቶች እንዲሰነዘሩ አድርጓል።

በግጭቱ መባባስ ምክንያት ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሀገሪቱ አእያስወጡ ሲሆንአሁን የኢትዮጵያ መንግስትም ዜጎቹን ለመታደግ ሀገራዊ ግብረ ሀይል ማቋቋሙን ይፋ አድርጓል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
173 views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 14:17:03 "የውጭ አገራት ዜጎች ከካርቱም ሊወጡ ነው"- የሱዳን ጦር

ሳምንት የደፈነው የሱዳን ጦርነት ተፋፍሞ ከመቀጠሉ ጋር ተያይዞ የውጭ አገራት ዜጎቻቸውን ከመዲናዋ ካርቱም ሊያስወጡ ነው።የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይ እና የቻይና ዲፕሎማቶች እና ዜጎች ከሱዳን ሊወጡ መሆኑንም የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫው አስታውቋል።የሱዳን ጦር አዛዥ አብደል ፈታህ አል ቡርሃን የውጭ አገር ዜጎቹ “በሚቀጥሉት ሰአታት ውስጥ” የሚወጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እና ለማስተባበር ተስማምተዋል ።

ሳዑዲ አረቢያም በሱዳን ያሉ ዜጎቿን “ከወንድም” ሱዳን አገር ልታስወጣ በዝግጅ ላይ መሆኗን አስታውቃለች።የሳዑዲ አረቢያ ዲፕሎማቶች ሱዳንን ለቀው መውጣታቸውን የሱዳን ጦር አስታውቋል።

የአውሮፓ ህብረት ዜጎቹን ከካርቱም ለማስወጣት እቅድ መንደፉን አስታውቋል።አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን እንዳሉ የህብረቱን አባል አገራት ዜጎችም ለማስወጣት የተለያዩ አማራጮችን እያጤኑ እንደሚገኙም ነው።በካርቱም ወደ 1 ሺህ 500 የሚጠጉ የህብረቱ አባል አገራት ዜጎች ይገኛሉ።ሰባት የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት በሱዳን ተልዕኮ አላቸው።የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አና ባየርቦኮክ ዜጎችን ለማስወጣት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረስ ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ግጭቱ ከተከሰተበት ሚያዝያ 7፣ 2015 ዓ.ም ጀምሮ የካርቱም አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደተዘጋ ይገኛል።

አሜሪካ የዲፕሎማቲክ ሰራተኞች ካርቱምን ለቀው እንዲወጡ ለማድረግ ውሳኔ ላይ እንዳልደረሰች ገልጻለች።ባለስልጣናቱ ከኤምባሲው ሰራተኞች ውጭ ያሉ ሌሎች የአሜሪካ ዜጎች ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ በራሳቸው እንዲዘጋጁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።ባለስልጣናቱ ይህንን ይበሉ እንጂ አሜሪካ ዜጎቿን ለማስወጣት በዝግጅት ላይ መሆኑን ዘገባዎች አሳይተዋል።የአሜሪካ ጦር የኤምባሲውን ሰራተኞች ከካርቱም ለማስወጣት እየተዘጋጀ መሆኑንም ተዘግቧል።የአሜሪካ ወታደሮች በጂቡቲ ወደሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ እየተወሰዱ እንደሆነም የአገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

አርብ እለት የአሜሪካ የጦር ሰራዊት ጀነራል ማርክ ሚሌይ ከጦር አዛዡ ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር በሱዳን ስላሉት አሜሪካውያን ደህንነት ተወያይተዋል።ፔንታጎን በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።
#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
168 views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 07:28:50 መተማ
የመተማ ወረዳ ነዋሪዎች በሱዳን ተይዞ የነበረው የእርሻ መሬታችን ተለቋል፣ማረስ እንፈልጋለን የመንግስት እሳቤ ምንድን ነው? በማለት የአካባቢው አመራሮችን እየጠየቁ ይገኛሉ። የሰሜን ዕዝን ጥቃት ተከትሎ ሱዳን ይሄን ክፍተት በመጠቀም በርካታ የኢትዮጵያ መሬቶችን መውሰዷ ይታወቃል። በዚህ የተነሳ በርካታ አርሶአደሮች ማሳቸውን ማረስ ካቆሙ አመታት ተቆጥረዋል። ሰሞኑን በሱዳን ፈጥኖ ደረሽ ሀይል እና በሱዳን መከላከያ ጦር መካከል ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ የሱዳን ጦር እነዚህ መሬቶች ለቆ ወደ ኋላ ሄዷል። ለምሳሌ ደለሎ ቁጥር ሶስት እና አራት ሙሉ በሙሉ ተለቀዋል። መንግሥት በበኩሉ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ መሬቶች ከሱዳን ጋር ተወያይቶ በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚሞክር በተደጋጋሚ ገልጿል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
193 views04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 16:57:54 የተዘነጉት በጎጃም የሚገኙት ተፈናቃዮች
በጥቃቶችና በጦርነት ተፈናቅለው አማራ ክልል የተጠለሉ ተፈናቃዮች ጤና በየጊዜው እያሽቆለቆለ ነው ተብሏል
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ የተፈናቀሉ 300 ሽህ የሚደርሱ ዜጎች ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም ከወለጋ፣ ከመተከልና ከወልቃይት የተፈናቀሉ ዜጎች ድረሱን እያሉ ናቸው፡፡
በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ተበትነውና ከማህበረሰቡ ጋር ተጠግተው አዲሱን መደበኛ ህይወታቸውን የሚመሩት ተፈናቃዮቹ ዛሬና ነገ እያሳሰባቸው ነው፡፡
ኦነግ ሸኔ በምስራቅ ወለጋ ዞን 50 ተፈናቃዮችን መግደሉን ኢሰመኮ ገለጸ
ተፈናቃይ እና ከስደት ተመላሽ ኢትዮጵያዊያንን ለመርዳት 111 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ
ተፈናቃዮቹ የእለት ጉርስ ማግኘትና የነገ እጣ ፈንታቸው እያስጨነቃቸው መሆኑን ለአል ዐይን ተናግረዋል፡፡ የበጎ አድራጊዎችንና የመንግስትን እጅ ከመጠበቅ ጀምሮ ህይወታቸውን ለማቃናት የጉልበት ስራ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ በእርሻ ስራ ተሰማርተው የነበሩ ሲሆኑ፤ የአፈሩ ሽታና የእህል ጎተራ ናፍቋቸዋል፡፡ ያሉበትን ሁኔታ ሲገልጹም ህይወት በዚህ መንገድ መቀጠል የለባትም ሲሉ ድጋፍን አጥብቀው ሽተዋል፡፡ 
በ40ዎቹ እድሜ አጋማሽ የሚገኙት ደመላሽ አዱኛ ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ ተፈናቅለው ምዕራብ ጎጃም ከተበተኑ አያሌ ተፈናቃዮች አንዱ ናቸው፡፡ ለደህንነታቸው ሰግተው ሩብ ክ/ዘመን ከኖሩበት አካባቢ ስድስት ልጆቻቸውን ይዘው ከአካባቢው መፈናቀላቸውን የሚናገሩት ደመላሽ "ልጆቼን ለማዳን ሳይቀጣጠል ቅድሚያ ላኳቸው" ይላሉ፡፡ 
"ልጆቼን ከላኩ በኋላ ምንአልባት ይረጋጋ ከሆነ ብዬ እኔ ወደ ኋላ ቀረሁ፡፡ ነገሩ እየተባባሰ ሲመጣ በእግሬ አቋርጬ ጎጃም ገባሁ" በማለት የተፈናቀሉበትን ቅጽበት ያስረዳሉ፡፡
ሰብዓዊ ድጋፍ ተፈናቅለው ዓመት ከሆናቸው በኋላ በመንግስት 15 ኪሎ ስንዴ ማግኘት መጀመራቸውን ይናገራሉ፡፡ ይህኑ ድጋፍን አሁን ላይ ካገኙ አምስት ወራት ማለፉን የሚናገሩት ደመላሽ አዱኛ "እግዚአብሄር የከፈተውን ጉሮሮ ሳይዘጋው አያድርም" በማለት ኑሯቸውን ይገልጻሉ፡፡ 
ቤት ተከራይው እንደሚኖሩ የሚናገሩት ደመላሽ አዱኛ፤ ወሩ ሲደርስ ኪራይ ለመክፈል ጭንቅ ነው ይላሉ፡፡
"የምናደርገው ነገር ከሌለለ ያው ምንም አማራጭ የለም፡፡ ወደ ዛው ብትሄጂም አሁንም ሰው እየተገደለ ነው፡፡ ይህ ጊዜ ያልፍ ይሆን እያልን በጉጉት እየጠበቅን ነው" ይላሉ፡፡ 
በሰሜኑ ጦርነት ተፈናቅለው እንደመጡ የሚናገሩት ቦጋለ ፈንታ በእርሻ ስራ ይተዳደሩ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ እሳቸውንና አብዛኛው ተፈናቃይ በእሳቸው አጠራር "በስግሰጋ" ቤተሰብ ዘመድ እተሳሳበ ኑራቸውን በአካባቢው መመስረታቸውን ይገልጻሉ፡፡ ለረጅም ዓመታት ከኖሩበትና ቤተሰብ ካፈሩበት አካባቢ በ2013 ዓ.ም. በተቀሰቀሰው ጦርነት ከጀርባቸው የለበሷትን ልብስ እንደያዙ ሀብት ንብረታቸውን ጥለው እግሬ አውጭኝ ማለታቸውን ይናገራሉ፡፡
 "ጦርነቱ ሲነሳ ህብረተሰቡን ማሳደድ ተጀመረ፡፡ የብሄር ጸብ ተነሳ፡፡ አማራጩ መሸሽ ነው፡፡ ድንገት ነበር፡፡ ከሦስት እስከ አራት ቀን ጫካ ያደረ አለ፡፡ እየተሰባሰበ ከዚያም ከዚያም እያለ በአንድ ሳምንትም በሁለትም በወሩም የገባ አለ፡፡ እንደዚህ አድርገን ተሰደድን፡፡" ሲሉ ሁነቱን ይገልጻሉ፡፡
በጎ አድራጊዎችና መንግስት በሚያቀርቡት እርዳታ፣ ከዘመድ ጋር በመጠጋት እንዲሁም የቀን ስራ (የጉልበት ስራ) በመስራት የእለት ጉርስ ለማግኘት እየታገሉ መሆኑን ቦጋለ ፈንታ ተናግረዋል።     
"ህይወት አይገፋ የለም መቼም እየተገፋች ነው፡፡ ቀን ይመሻል፤ ሌሊት ይጠባል፡፡ ምክንያቱም ሰው የሚኖረው ሲደላው ነው፡፡ ሰው መኖር የሚችለው ሲኖረው ነው፡፡ የመኖር ያለመኖር ላይ ነው ጥያቄው፡፡ ሰው ሲፈጠር አንድ ነው፡፡ የሚበላለጠውና የሚተናነሰው ነገር የለም፡፡ ከተወለደና ከአደገ በኋላ ነው ሰው የሚበላለጠው፡፡ ስሜ ቦጋለ ነው፡፡ አሁን ተፈናቃይ ተብዬ ስም ተሰይሚያለሁ፡፡ የተፈናቃይ ልጅ ተብላ ልጄ እስከምትጠራ ድረስ" በማለት ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል    
እዚህ ግባ የሚባል እርዳታ እየደረሰን አይደለም የሚሉት ሌላው ተፈናቃይ መልካሙ ቁሜ "አሳሳቢ" የሚባል ሁኔታ ላይ ነን ይላሉ፡፡
"ስንዴውም ይህ ነው የሚባል አይደለም፡፡ በቂ አይደለም፡፡ ቋሚ አይደለም፡፡ እንዴውም እኛ ያለንበት ወረዳ ወደ ሌላ ወረዳ ሄዷል ተብሎ ገና አልገባልንም" በማለት ስለ ሰብዓዊ ድጋፉ ይናገራሉ፡፡
የአማራ ክል መንግስትም ግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ ተፈናቃዮች እንዳሉት ገልጾ፤ ሰብዓዊ አቅርቦት ለማድረግ እጅ ያጥረኛል ብሏል፡፡
የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ዳይሬክተር ብርሀኑ ዘውዱ በአማራ ክልል ስድስት መቶ ስልሳ ሽህ ተፈናቃዮች እንዳሉ ለአል ዐይን ተናግረዋል፡፡ አብዛኞቹም ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ መሆናቸውን የጠቀሱት ኃላፊው፤ ምዕራብ ጎጃምን ጨምሮ አብዛኛው ተፈናቃይ ባለባቸውን ዞኖች መንግስት እርዳታ እንደሚያቀርብ ገልጸዋል።   
ሰብዓዊ እርዳታው በቂ አለመሆኑን የሚያነሱት ኃላፊው፤ ይህም ከመንግስት አቅም ጋር የሚያያዝ ነው ብለዋል፡፡ እርዳታ በማጠሩ በየወሩ መሰጠት የነበረት እርዳታ ወራትን ከመሸገር አልፎ ዱካው የሚጠፋበት ጊዜ እንዳለም አልሸሸጉም፡፡ 
ክልሉ ለተፈናቃዮች እርዳታ ማቅረብ የአንድ ዞን ህዝብ መመገብ ማለት በመሆኑ ከብዶኛል ብሏል፡፡
ቀዳዳውን ለመሸፈን የክልሉን መጠባበቂያ በጀት እየተጠቀሙ መሆናቸውን የሚጠቁሙት ብርሀኑ ዘውዱ፤ "ማስታገሻ" እየሰጠን ነው ይላሉ፡፡
"ቢያንስ ሰው እንዳይሞት ነው እየሰጠን ያለነው፡፡ ጤናን ለመጠበቅ የሚያስፈለግ አቅርቦትን በተመለከተ ሰፊ ክፍተት ነው ያለው፡፡ በእናቶችና ህጻናት ያለው የስነ-ምግብ መጓደል [የተመጣጠነ ምግብ እጥረት] በየዓመቱ ከፍ እያለ ነው፡፡ ይሄ ማለት ባይሞቱም ጤናቸው ላይ ተጽዕኖ እያደረ ነው" ብለዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲቀርብላቸው እየወተወቱ ነው፡፡
ተፈናቃዮቹ ከእለት ጉርስ ባሻገርም በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን ጊዜና ሁኔታ እየናፈቁ ናቸው፡፡ በሰሜኑ ጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው ለመመለስ በመንግስት ተስፋ እንደተሰጣቸው ለአል ዐይን ተናግረዋል፡፡
የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ተፈናቃዮን ማቋቋም ከክልሉ አቅም በላይ መሆኑን በማንሳት ኃላፊነቱ በፌደራል መንግስቱ ትከሻ ላይ ያረፈ መሆኑን ጠቁመሟል፡፡ መልዕክቱን #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
ለማስታወቂያ ስራና ለመረጃ ጥቆማዎች @infoetrobot ይህን ይጠቀሙ
አል አይን
219 views13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 16:28:46 የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ይቅርታ ጠየቀ
የዒድ ሰላት ለመስገድ ከቤታችሁ ወጥታችሁ ላመለጣችሁ የከተማችንና አካባቢው ሙስሊሞች በሙሉ!!
ዛሬ በነበረው የኢድ ሰላት ፕሮግራም ላይ ለመታደም ጥሪያችንን አክብራችሁ በአንድነት  አምራችሁና ደምቃችሁ ግዙፉ የከተማችን ውበት ሆናችሁ በመዋላችሁ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እንገልፃለን።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በድጋሚ እንኳን ለ1444 ዓ.ሂ  የኢድ አልፊጥር በዓል  በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዛሬው እለት የተሰገደው የኢድ ሰላት በሰላም፣በደስታ መጠናቀቁ ቢያስደስትም የዒድ ሰላት ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት ከነበረው ሰአት ቀድሞ በመሰገዱ የዒድ ሰላት ላመለጣችሁ የከተማችን ሙስሊሞች ይቅርታ እንጠይቃለን።

በትናንትናው እለት ከፌደራል መጅሊስ ጋር በጋራ በሰጠነው መግለጫ ሸሪአውን በጠበቀ መልኩ በእለቱ ንግግሮች እንደማይኖሩና በማለዳ ሰግደን እንደምንበተን ለህዝባችን ገልፀን ቢሆንም በእለቱ የተገኙት ሚድያዎች በአብዛኛው በሚባል መልኩ ትኩረት ሰጥተው ባለማስተላለፈቸው እና ከሚዲያዎቹ በተጨማሪ ሌሎች አማራጮችን በሰፊው  ባለመጠቀማችን ችግሩ እንዲፈጠር ምክንያት እንደነበሩ ተረድተናል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት የነበረውን ሂደትን ለማሻሻል በሚል መልካም እሳቤ በተፈጠረ ክፍተት ሰላት ላመለጣችሁ ሁሉ ታላቅ ይቅርታ እየጠየቅን በቀጣይ የሚስተካከል መሆኑን ህዝባችን እንዲገነዘብ እያልን፣
በበጎና ገንቢ በሆነ መልኩ አስተያየታችሁን ለለገሳችሁን የከተማችን ነዋሪዎች ምስጋና እያቀረብን በዓሉ የሰላም የደስታ፣የመተዛዘን፣የመረዳዳት እንዲሆን መልካም ምኞታችንን ለመግለፅ እንወዳለን። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
ለማስታወቂያ ስራና ለመረጃ ጥቆማዎች @infoetrobot ይህን ይጠቀሙ
208 views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 13:50:01 ማንን ትቼ ማንን ልጥራ?! በደፈናው ሁላችሁንም እንኳን አደረሳችሁ ማለት አይከብደኝም። ግን እስቲ የተወሰኑትን ልሞክር። ከሁሉም በላይ የሮመዳንን ጾም አጠናቀህ፡ የዛሬዋ ዕለት ላይ ለመድረስ አምላክ ሳይፈቅድልህ አራት ቀናት ሲቀሩት በሞት መልዕክተኞች ከጎናችን የተነጠከው ውዱ ወንድሜ ተገኔ ኑርዬ ሁሌም አስታውስሃለሁ። ሀዋሳ አረብ ሰፈር ያላችሁ፡ የእምነት መስመር ሳታሰምሩ ላሳደጋችሁን፡ አብራችሁኝም ላደጋችሁ፡ ከሸምሳን ሱቅ እስከ ጎንደር ጠጅ ቤት፡ በዚህም ከቶታል እስከ ሞቢል ድረስ ላላችሁ የሙስሊም አባቶቼ እናቶቼ፡ ወንድምና እህቶቼ እንኳን ለጾም ፍቺው አደረሳችሁ። ኢድ ሙባረክ ብዬአችኋለሁ።የሸምሳን ልጆች፡ የሀሽም ልጆች፡ የአብደላ ልጆች፡ የሽኩሬ ልጆች፡ የጋሽ ከማል ልጆች፡ የጋሽ ሳህሉ ልጆች፡ አረ እንደምን ናችሁ? እንኳን አደረሳችሁ!

የካምፓስ ጓደኛዬ፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የስፖርት ጋዜጠኛ የነበርከው ወንድሜ ኢዘዲን ከድር ምነው አሜሪካ ስትመጣ ድምጽህ ጠፋብኝ? እንኳን አደረሰህ። የጋዜጠኝነት ሜንተሬ፡ ብዙ ነገሮችን የተማርኩብህ፡ እንደቅርብ ዘመድ የቀረብኩህ፡ አስተናጋጄ የዶቼቬሌው ጋዜጠኛ ነጋሽ መሀመድ ባለቤትህ ሙና፡ ልጆችህ ሳምራና አዩብ ሁላችሁንም እንኳን አደረሳችሁ ብዬአለሁ። ለጊዜው ስምህን ዘነጋሁት። ከ20ዓመት በፊት በብሩንዲ የሰላም ማስከበር ዘመቻ በአስተርጓሚነት አብረኸኝ የነበርከው፥ የወባ ትንኝ እንዳይነድፈኝ አጎበርህን አውሰከኝ አንተ ግን ለታመምከው የትግራዩ ወዳጄ (ኑረዲን መሰለኝ ስምህ) ተግባርህንና መስዋዕትነትህን ዝንታለሜን የማስታውሰው መሆኔን ስገልጽልህ ካለህበት እንኳን አደረሰህ በማለት ነው። የኤርትራው በረሀ ጓዶቼ ኑርጀባ ሁሴን፡ የአየር ሃይሉ ሄሊኮፕተር አብራሪ ጠይብ ቃዲ፥ ኢድ ሙባረክ ብዬአችኋለሁ።

የምስራቁ በር ግድግዳ አጥርና ማገር ለሆንከው ውድ ውደጄ ሙስጠፌ መሀመድ፡ ለረጅም ዓመታት የትግል አጋሮቼ ሆናችሁ አሁን ድረስ በወዳጅነት ለዘለቃችሁት ጀማል ዲርዬና አብዱላሂ ሁሴን ቀናነታችሁ፡ ደግነታችሁ ሳይደበዝዝ ሁሌም አብሮአችሁ እንዲኖር እመኛለሁ። እንኳን አደረሳችሁ። የአብኑ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ውዱ ወንድሜ ጣሂር መሀመድ አንተንም በተለየ ሁኔታ እንኳን አደረሰህ ልልህ እጅጉን ወደድኩኝ። ወዲህ ወደአሜሪካ ስምጣ ብዙ ናችሁና ሁላችሁንም እንኳን ለዚህ ለተቀደሰ ቀን አደረሳችሁ እላለሁ። በፖለቲካ ምክንያት የተኳረፍነው ግን ደግሞ ብዙ ደግ ጊዚያትን አብረን ያሳለፍነው ወዳጄ ሳዲቅ አህመድ ከእነቤተሰቦችህ እንኳን አደረሰህ ስል መልካም ምኞቴን አቀርባለሁ። የአባይ ጉዳይ ዓለም አቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ ኢትዮጵያዊ ወኔ ሰንቀህ እየሞገትክ ላለኸው ኡስታዝ ጀማል ረሽድ የእንኳን አደረሰህ መልዕክቴ ካለህበት ይድረስህ። የኢትዮ ቲዩብ ባልደረባና የቅርብ ወዳጄ ዩሱፍ ኢብራሂም አንተንም ከነቤተሰቦችህ መልካም በዓል እንዲሆንህ እመኛለሁ። እዚህ አጠገቤ አንድ ህንጻ ተጋርተን ለምንኖረው፡ ከሀዋሳ ጀምሮ ወዳጅነታችን ለዘለቀው አብደላና ቤተሰቦችህ እንኳን አደረሳችሁ ስል መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።

ስማችሁን ያልጠቀስኳችሁ ግን ደግሞ ልዩ ስፍራ በውስጤ ያላችሁ ሙስሊም ወዳጆቼ በሙሉ እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ በሚል ጠቅልዬ መልካም ምኞቴ እንዲደርሳችሁ እፈልጋለሁ። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በየትኛውም የዓለም ጥግ የምትገኙ፡ የዛሬዋ ዕለት የሰላም የፍቅር የደስታ ይሁንላችሁ ዘንድ እመኛለሁ። ክፉ አይንካችሁ። የኢትዮጵያ አድባር በያላችሁበት ይከተላችሁ። ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን። መልካም በዓል። ኢድ ሙባረክ! መልዕክቴ ከደረሳቸው #ሼር እንደምታደርጉልኝ ተስፋ አደርጋለው

@emsmereja

#mesaymekonnen
189 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 13:50:01
ማንን ትቼ ማንን ልጥራ?
172 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 12:56:30
1444ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በመከበር ላይ ነው

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የዒድ አል ፈጥር በዓል በዛሬው ዕለት በዒድ ሶላት እና በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል።

በመላው ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎችም የዘንድሮው 1444ኛ የዒድ አልፈጥር በዓል፤ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች በደመቀ መልኩ እየተከበረ ይገኛል።

ከማለዳው አንስቶ በርካታ ቁጥር ያላቸው የእምነቱ ተከታዮች፤ የዒድ ሶላት ሥነ ስርዓት ወደሚከናወንባቸው ስፍራዎች በማቅናት በዓሉን በሶላትና በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥርዓቶች አክብረውታል።

በአሁኑ ሰዓትም በተለያዩ አካባቢዎች የተካሄደው የኢድ ሶላት ሥነ ስርዓት በመጠናቀቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ወደ ቤቱ በመመለስ በዓሉን ከቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ዘመድ ጎረቤት ጋር በመሰብሰብ በድምቀት ያከብረዋል።

ዒድ ሙባረክ!
ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
ለማስታወቂያ ስራና ለመረጃ ጥቆማዎች @infoetrobot ይህን ይጠቀሙ
187 views09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:21:33 ሐሙስ ምሽት! ሚያዝያ 12/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል "ግጭት መቀስቀስ የሚፈልጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ" አዲስ ባወጡት መግለጫ አስጠንቅቀዋል። ዐቢይ አንዳንድ አካላት የኢትዮጵያና ሱዳን ግንኙነትንና በወንድማማችነት ላይ የተመሠረተ ጉርብትና ለማበላሸት፣ "ኢትዮጵያ ወታደሮቿን ሱዳን ውስጥ አስገብታለች በማለት ሐሰተኛ መረጄ እያሠራጩ ነው" በማለት ከሰዋል። የኢትዮጵያና ሱዳን የድንበር ውዝግብ በንግግር ይፈታል ያሉት ዐቢይ፣ "ኢትዮጵያ የሱዳንን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ ለውዝግቡ መጠቀሚያ ልታደርገው አትፈልግም" ብለዋል። አንዳንድ ወገኖች ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ በነበረችበት ወቅት "ሉዓላዊነቷን በመጣስና መሬቷን በኃይል በመቆጣጠር የፈጸሙትን ድርጊት ኢትዮጵያ በሱዳን ላይ እንደማትፈጽም ዐቢይ ገልጸዋል።

2፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጦር ጉዳተኞች ምክር ቤት ማቋቋሙን አስታውቋል። የክልሉ አስተዳደር ምክር ቤቱን ያቋቋመው፣ የጦር ጉዳተኞችንና በጦርነቱ ተዋጊዎች የሞቱባቸውን ቤተሰቦች ለመርዳት እንደኾነ የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ አስተዳደሩ ለጦር ጉዳተኞች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ የጦር ጉዳተኞች ባለፈው ወር በመቀሌ ከተማ በሰላማዊ ሰልፍ ችግራቸውን በገለጹበት ወቅት ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

3፤ በካርቱም የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን ዜጎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ ጥረት እያደረገ መኾኑን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጡን የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል። መንግሥት በሱዳን የሚኖሩ ዜጎችን ደኅንነት ለመከታተል እንዲያመቸው፣ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማትና የሱዳን አጎራባች ከኾኑ ክልላዊ መንግሥታት የተውጣጣ ግብረ ኃይል ማቋቋሙን ሚንስቴሩ ይፋ ማድረጉንም ዘገባዎቹ አመልክተዋል። በሱዳን የኢትዮጵያ ኢምባሲ በበኩሉ፣ በግጭቱ የተገደሉ ኢትዮጵያዊያን ስለመኖራቸው መረጃ እንደደረሰው ገልጦ ነበር።

4፤ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎ ከአገሪቱ ጦር ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል ቡርሃን ጋር ለድርድር አልቀመጥም ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። ግጭቱን የጀመሩት ጀኔራል ቡርሃን ናቸው ያሉት ጀኔራል ደጋሎ፣ ወደፊትም ከባላንጣቸው ጋር ድርድር እንደማይኖር መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የሱዳን ጦር ሠራዊትም፣ ከፈጥኖ ደራሽ ሠራዊቱ ጋር የሚደረግን ድርድር ውድቅ አድርጓል። ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ጥሪ ብናደርግም የጦር ሠራዊቱ አዛዦች ግን ተኩስ አቁም አይፈልጉም ያሉት ጀኔራል ደጋሎ፣ ነገ ለሚከበረው ኢድ አልፈጥር በዓል ተኩስ አቁም ቢደረግ ተቃውሞ የለንም ማለታቸው ተገልጧል። ጀኔራል ደጋሎ ሠራዊታቸው ከሩሲያው የግል ወታደራዊ ኩባንያ "ዋግነር" ድጋፍ ያገኛል መባሉን አስተባብለዋል።

5፤ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በሱዳን ጦር ሠራዊትና በፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት ላይ ማዕቀብ ለመጣል እያሰላሰለ መኾኑን ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት ዘግቧል። ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን በያዘው የሁለቱ ወገኖች ውጊያ ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን፣ የዓለም ጤና ድርጅት በግጭቱ 330 ሰዎች መገደላቸውንና 3 ሺህ 200 ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የካርቱም ነዋሪዎች ውጊያውን በመሸሽ ከተማዋን ለቀው እየወጡ እንደኾነ ተነግሯል።

6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ0852 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ1669 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 64 ብር ከ0425 ሳንቲም እና መሸጫው 65 ብር ከ3234 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ59 ብር ከ1043 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ60 ብር ከ2864 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
ለማስታወቂያ ስራና ለመረጃ ጥቆማዎች @infoetrobot ይህን ይጠቀሙ
115 views17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 07:16:28 ሐሙስ ማለዳ! ሚያዝያ 12/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ መከላከያ ሠራዊት ትናንት ዲሽቃ፣ ሞርታርና ሌሎች የቡድን ጦር መሳሪያዎችን ከሕወሃት መረከብ መጀመሩን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል። የቡድን ጦር መሳሪያዎቹ ልዩ ስሙ ደንጎላት በተባለ ቦታ ላይ የተሰበሰቡ እንደኾኑ ዘገባው ጠቅሷል። የቡድን መሳሪያዎች ርክክብ እስከ ሚያዝያ 16 ይቀጥላል መባሉን ዘገባው ጠቅሷል። ሠራዊቱ በመጀመሪያው ዙር ከባድ የጦር መሳሪያዎችንና በሁለተኛው ዙር የአየር ኃይል መሳሪያዎችን ከሕወሃት ኃይሎች መረከቡ ይታወሳል።

2፤ የቡድን 7 አገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የጀመረው የሽግግር ፍትህ ሂደት እንዲጠናከር፣ ተጠያቂነት እንዲሠፍንና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተቆጣጣሪዎች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ባወጡት መግለጫ አሳስበዋል። ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ፣ አፍሪካ ኅብረት በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና በሕወሃት መካከል የሰላም ስምምነት እንዲደፈረም ያደረገውን አዎንታዊ ጥረት በመግለጫቸው አድንቀዋል። የቡድን-7 ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ይህን ያሉት፣ በጃፓን ሒሮሺማ ከተማ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ባወጡት መግለጫ ነው።

3፤ የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ትግራይን እንዳይጎበኙ የኢትዮጵያ መንግሥት አግዷቸዋል ተብሎ ስለወጣው መረጃ ቃል አቀባያቸው ስቲፋኒ ዱጃሪች ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተጠይቀው ነበር። ኾኖም ዱጃሪች ጥያቄውን በቀጥታ በመመለስ ፋንታ፣ ጉተሬዝ ወደ ኢትዮጵያ በሄዱበት ወቅት ወደ ትግራይ እንዳልሄዱ በወቅቱ ግልጽ አድርገናል በማለት መልሰዋል። ጉተሬዝ ባለፈው የካቲት በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት፣ ትግራይን እንዳይጎበኙ መንግሥት እንደከለከላቸው ዋሽንግተን ፖስት ከአሜሪካ መንግሥት ያፈተለኩ የስለላ መረጃዎችን ጠቅሶ ትናንት ዘግቦ ነበር።

4፤ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የሱዳኑ ግጭት ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕግጋት የሚጣሱበት ደረጃ ላይ ደርሷል ሲሉ በማለት ተናግረዋል። ሩቶ፣ የሱዳን ጀኔራሎች ግጭቱ ከአገሪቱ ድንበር አልፎ የቀጠናው ስጋት እንዲኾን የሚያደርግ ኹኔታ ፈጥረዋል አስጠንቅቀዋል።.ካርቱም ውስጥ ሕዝብ በሚኖርባቸው መንደሮች ውጊያ እየተካሄደ መኾኑንና በውጭ ዲፕሎማቲክ አካላት ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ሩቶ በአስረጅነት ጠቅሰዋል። ሩቶ እና የጅቡቲውና የደቡብ ሱዳኑ አቻቸው ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ ትናንት ካርቱም ለመሄድ ይዘውት የነበረው ዕቅድ ሳይሳካ ቀርቷል።

5፤ የሱዳን ጦር ሠራዊትና ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት ለ24 ሰዓት ተኩስ አቁም ለማድረግ ትናንት ምሽት ላይ ለሁለተኛ ጊዜ በተናጥል የደረሱበት ስምምነት በድጋሚ እንደተጣሰ የውጭ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የ24 ሰዓታት ተኩስ አቁም ለማድረግ ቀድሞ ዝግጁነቱን የገለጠው ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት ሲሆን፣ ጦር ሠራዊቱም ዘግየት ብሎ ፍቃደኛነቱን አሳውቆ ነበር። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
ለማስታወቂያ ስራና ለመረጃ ጥቆማዎች @infoetrobot ይህን ይጠቀሙ
207 views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ