Get Mystery Box with random crypto!

መተማ የመተማ ወረዳ ነዋሪዎች በሱዳን ተይዞ የነበረው የእርሻ መሬታችን ተለቋል፣ማረስ እንፈልጋለን | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መተማ
የመተማ ወረዳ ነዋሪዎች በሱዳን ተይዞ የነበረው የእርሻ መሬታችን ተለቋል፣ማረስ እንፈልጋለን የመንግስት እሳቤ ምንድን ነው? በማለት የአካባቢው አመራሮችን እየጠየቁ ይገኛሉ። የሰሜን ዕዝን ጥቃት ተከትሎ ሱዳን ይሄን ክፍተት በመጠቀም በርካታ የኢትዮጵያ መሬቶችን መውሰዷ ይታወቃል። በዚህ የተነሳ በርካታ አርሶአደሮች ማሳቸውን ማረስ ካቆሙ አመታት ተቆጥረዋል። ሰሞኑን በሱዳን ፈጥኖ ደረሽ ሀይል እና በሱዳን መከላከያ ጦር መካከል ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ የሱዳን ጦር እነዚህ መሬቶች ለቆ ወደ ኋላ ሄዷል። ለምሳሌ ደለሎ ቁጥር ሶስት እና አራት ሙሉ በሙሉ ተለቀዋል። መንግሥት በበኩሉ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ መሬቶች ከሱዳን ጋር ተወያይቶ በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚሞክር በተደጋጋሚ ገልጿል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja