Get Mystery Box with random crypto!

1444ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በመከበር ላይ ነው በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

1444ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በመከበር ላይ ነው

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የዒድ አል ፈጥር በዓል በዛሬው ዕለት በዒድ ሶላት እና በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል።

በመላው ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎችም የዘንድሮው 1444ኛ የዒድ አልፈጥር በዓል፤ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች በደመቀ መልኩ እየተከበረ ይገኛል።

ከማለዳው አንስቶ በርካታ ቁጥር ያላቸው የእምነቱ ተከታዮች፤ የዒድ ሶላት ሥነ ስርዓት ወደሚከናወንባቸው ስፍራዎች በማቅናት በዓሉን በሶላትና በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥርዓቶች አክብረውታል።

በአሁኑ ሰዓትም በተለያዩ አካባቢዎች የተካሄደው የኢድ ሶላት ሥነ ስርዓት በመጠናቀቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ወደ ቤቱ በመመለስ በዓሉን ከቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ዘመድ ጎረቤት ጋር በመሰብሰብ በድምቀት ያከብረዋል።

ዒድ ሙባረክ!
ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
ለማስታወቂያ ስራና ለመረጃ ጥቆማዎች @infoetrobot ይህን ይጠቀሙ