Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkun_zemede — Zemedkun Bekele (ዘመዴ) Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkun_zemede — Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
የሰርጥ አድራሻ: @zemedkun_zemede
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-05-05 20:18:57
ጎንደር የነበረው የታቃውሞ ሁኔታ

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
292 views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 14:09:29
የሩሲያና ዩክሬን ዲፕሎማቶች በቱርክ ለስብሰባ ተገናኝተው ተደባደቡ

የሩሲያ እና ዩክሬን ዲፕሎማቶች በቱርክ ለስብሰባ በሄዱበት ቡጢ መሰናዘራቸው ተሰምቷል። የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 15ኛ ወሩ ላይ የሚገኝ ሲሆን በየጊዜው አዳዲስ ክስተቶችን እያስተናገደ ነው :: ዱፕሎማቶቹ መደባደባቸውን ተከትሎ የቱርክ መንግሥት የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እልባት እንዲያገኝ ብዙ ጥረቶችን እያደረግን ባለንበት ብዚህ ወቅት እንዲህ አይነት ክስተቱ መፈጸሙ ትክክል እንዳልሆነ በሀገሪቱ ፓርላማ ድረገጽ ላይ ይፋ ባደረገችው መግለጫ አስታውቃለች።
#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
310 views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 13:52:25 የአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የጸጥታው ሁኔታ ውጥረት ውስጥ መግባቱን የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የዶቼ ቬለ የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት ጎንደር ከተማ ላይ መንገዶች ተዘጋግተው የሥራ እንቅስቃሴ የቆመ ሲሆን እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስም በአንዳንድ የከተማው አካባቢዎች የተኩስ ድምጽ ሲሰማ ነበር። በተኩሱ የተጎዱ ሰዎች መኖራቸውን በማመልከትም በዛሬው ዕለት ደግሞ የተዘጉ መንገዶችን ለመክፈት እንቅስቃሴ መኖሩንም አመልክተዋል። እማኙ እንደሚሉትም ኅብረተሰቡ ለሀገር ሕልውና በመንግሥት ጥሪ ቀርቦላቸው ከመከላከያ ሠራዊት ጎን ተሰልፈው የነበሩ የአካባቢው ታጣቂዎች ላይ በመንግሥት ኃይሎች የሚወሰደውን የጥቃት እርምጃ አጥብቆ እየተቃወመ ነው። ለዚህ ተግባር በስፍራው እንደ ዙ 23 ያሉ የቡድን ከባድ የጦር መሣሪያዎችን ሳይቀር ይዞ የተሰማራው የመከላከያ ሠራዊት አካባቢውን ለቅቆ እንዲወጣ እየጠየቁ መሆኑንም ገልጸዋል። በጎንደር እና አካባቢውም ማንኛውም የሥራ እንቅስቃሴ መቆሙን ተመሳሳይ እርምጃም በሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች በቀጣይ ሊኖር እንደሚችልም አክለው ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። ይኽ በእንዲህ እንዳለም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች በመከላከያ ሠራዊት እና በአካባቢው ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥና በከባድ መሣሪያ ጭምር የታገዘ ጥቃት መኖሩን ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል። የተኩስ ልውውጥና ጥቃት ተፈጽሟል ባላቸው «በሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት ያለ መሆኑን፤ በተለይም ሸዋ ሮቢት፣ አርማኒያ፣ አንጾኪያ፣ ገምዛ እና ማጀቴ» ላይ «በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት የደረሰ መሆኑን እንዲሁም ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ በተለያዩ ጊዜያት የተዘጋ መሆኑን» ማረጋገጥ መቻሉንም ገልጿል። በተጨማሪም «በአማራ ክልል የተወሰኑ ተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የክልል ልዩ ኃይሎችን እንደገና የማዋቀር ውሳኔን በመቃወም የተካሄዱ ሰልፎችን መርተዋል/አስተባብረዋል የተባሉ የተወሰኑ ወጣቶች እና ከፋኖ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ የተወሰኑ ሰዎች እንደታሰሩ» መረዳቱንም አመልክቷል። ኢሰመኮ አክሎም «በአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው “የሕግ ማስከበር ዘመቻ” በሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን አንድምታና ተጽእኖ» በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝም አመልክቷል። ከዚህም ሌላ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)ም በበኩሉ ባወጣው መግለጫ «በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ሰላምና መረጋጋት እንደሌለና ዜጎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንዳልቻሉ መንግሥታዊ ሥራዎች ማከናወን አስቸጋሪ ሆኖ ኅብረተሰቡ ስጋት ውስጥ እንደወደቀ» መረጃዎች በአካባቢው ከሚገኘው ምንጮች እንደደረሱት አስታውቋል። «ውጥረቶች በሰላማዊ ውይይት እንጂ በጠመንጃ አፈሙዝ አይረግቡም» ያለው ኢዜማ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሰላማዊ መንገዶችን እንዲያስቀድሙ ጥሪውን አቅርቧል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ደግሞ በአማራ ክልል ለተፈጠሩ የፀጥታ ቀውሶች ምክንያቶቹ የፖቲካ ችግሮችና የመንግሥት ፍላጎት ማጣትና አቅም ማነስ ናቸው ሲል ተችቷል። አብን አክሎም በክልሉ የሚታዩት ችግሮች እልባት እንዲያገኙ መንግሥት ግንባር ቀደም ሚናውን እንዲወጣ በመጠየቅ፤ ፋኖና ሌሎች በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችም ከመካረር አልፈው ከመንግሥት የፀጥታ አመራሮች ጋር ንግግር እንዲጀምሩ አሳስቧል።
የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በበኩሉ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፣ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከሚያዝያ 5 ቀን 2015 ዓ ም ጀምሮ «በኢ መደበኛ የታጠቁ» ያላቸውን ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ በሰላም አስከባሪና በሚሊሺያ ሠራዊት እንዲደራጁ፣ የማይፈልጉ ደግሞ ወደ ግል ሥራቸው እንዲገቡ ተከታታይ የውይይት መድረክ መዘጋጀቱን አስታውቋል። «በሕገወጥ መንገድ በቡድን ታጥቃችሁ ግድያና ዘረፋ የምትፈፅሙ ኃይሎች በሰላም እጃችሁን ለመንግሥት እንድትሰጡ ጥሪ እናቀርባለን» ሲል የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል። የክልሉ መንግሥት «ከሕግ የራቁና የታጠቁ» ያላቸውን ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ እየሠራ እንደሆነ በማመልከትም፣ «አጥፊዎች» ያላቸው ኃይላት ወደ ሥግ እስኪቀርቡ ድረስ ሕግ የማስከበሩ ሥራ የሚቀጥል መሆኑን አሳስቧል። #ሼር ማድረግ ግን ለምንድነው የምትረሱት? መረጃ አይናቅም ሼር ይደረግ


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
299 views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 07:08:43 ዓርብ ማለዳ! ሚያዝያ 27/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ ኢዜማ በአማራ ክልል ባለው ግጭት ተጨማሪ የሰው ሕይወትም ኾነ የንብረት ውድመት እንዳይከሰት መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቋል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት "ከግጭት በመለስ ያሉ ሰላማዊ መንገዶችን" እንዲያስቀድሙ ኢዜማ ጥሪ አድርጓል። ፓርቲው፣ በመንግሥት ውስጥና ከመንግሥት ውጭ ያሉ "ጽንፈኛ ዘውጌ ብሄርተኛ ኃይሎች ጽንፍ የወጣ ትርክትና እንቅስቃሴ" በክልሉ በመከላከያ ሠራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተፈጠረውን ውጥረትና ግጭት አባብሶታል ብሏል። የክልል ልዩ ኃይሎችን ወደ ፌደራል ጸጥታ መዋቅር የማዋሃድ ሂደት የተከናወነበት "ደካማ መንገድ" በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ ስጋትና ጥርጣሬ መፍጠሩንም ፓርቲው ገልጧል።

2፤ ብሄራዊ ባንክ ከሚያዝያ 28 ጀምሮ ተግባራዊ የሚኾኑ የተለያዩ የወርቅ መግዣ ተመኖችን ማውጣቱን የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል። በማሻሻያው መሠረት፣ ባንኩ እስካሁን ከዓለማቀፍ የወርቅ ዋጋ ላይ ለወርቅ አቅራቢዎች ሲሰጥ የቆየው የ35 በመቶ ተጨማሪ ክፍያ እንዲቀር ተደርጓል። በምትኩ ባንኩ ከዓለማቀፍ የወርቅ ዋጋ ላይ በየዕለቱ በሚወጣው ዓለማቀፍ የወርቅ ዋጋ ላይ፣ ከ50 እስከ 150 ግራም ወርቅ ላይ 35 በመቶ፣ ከ150.01 ግራም እስከ 1 ሺህ ግራም 52 በመቶ፣ ከ1,000.01 ግራም እስከ 5 ሺህ ግራም 55 በመቶ እና ከ5 ሺህ ግራም በላይ 60 በመቶ ተጨማሪ ክፍያ ለመክፈል መወሰኑን ዘገባዎች አመልክተዋል።

3፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ጋር ትናንት በታላቁ ቤተመንግሥት መወያየታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል። ሾልዝ በኢትዮጵያ በነበራቸው የግማሽ ቀን ቆይታ፣ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር ጭምር ተነጋግረዋል። ሾልዝ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው፣ ትናንት ማምሻውን ናይሮቢ ገብተዋል።

4፤ የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ከዛሬ ጀምሮ ለሰባት ቀናት ተኩስ አቁም ለማድረግ የገቡትን ቃል ኪዳን ሳያከብሩት ቀርተዋል። በጦር ሠራዊቱና ፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት መካከል ውጊያው እስከ ትናንት እኩለ ሌሊት እንደቀጠለ የውጭ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጀኔራል ቡርሃን ልዩ መልዕክተኛ ዳፋላህ አልሃጂ ጋር ትናንት በጽሕፈት ቤታቸው መነጋገራቸውንና ኹለቱ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች "ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ" ጥሪ ማስተላለፋቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪም፣ ልዩ መልዕክተኛውን በጽሕፈት ቤታቸው ማነጋገራቸውን በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል።

5፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ላይ ማዕቀብ ለመጣል የአሜሪካ ግምጃ ቤት "ጦርነት አጋጋዮችንና ሰላም አደፍራሾችን" እንዲለይ አዲስ ባወጡት ፕሬዝዳንታዊ መመሪያ አዘዋል። የባይደን ትዕዛዝ፣ ተፋላሚ ወገኖችን በቀጥታም ይኹን በተዘዋዋሪ የረዱ ወይም ለመርዳት የሞከሩ የውጭ አካላት በአሜሪካ ያላቸው ገንዘብ እንዲታገድና ከአሜሪካ ኩባንያዎች ጋር የንግድ ግንኙነት እንዳያደርጉ ያዛል። ባይደን፣ ማዕቀቡ በሱዳን ሰላምና ጸጥታ ላይ ስጋት የሚደቅኑና ሲቪል ሽግግር መንግሥት እንዳይመሠረት እንቅፋት የሚኾኑ ድርጊቶችንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ያስቀራል ብለዋል። ግጭቱ በአሜሪካ ብሄራዊ ደኅንነትና የውጭ ፖሊሲ ላይ "ያልተለመደና የተለየ ስጋት" ደቅኗል ተብሏል። #ሼር ማድረግ ግን ለምንድነው የምትረሱት? መረጃ አይናቅም ሼር ይደረግ


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
314 views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 21:20:37 <<ውጥረቶች በሰላማዊ ውይይት እንጂ በጠመንጃ አፈሙዝ አይረግቡም!>> ኢዜማ

በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ሰላምና መረጋጋት እንደሌለና ዜጎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንዳልቻሉ መንግሥታዊ ሥራዎች ማከናወን አስቸጋሪ ሆኖ ኅብረተሰቡ ስጋት ውስጥ እንደወደቀ በአካባቢው ከሚገኙ ከተለያዩ ምንጮች መረጃዎች ደርሰውናል።

እንደሚታወቀው ክልሉ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተፈጠረው ጦርነት ገፈት ቀማሽ ነበር። ይህን ተከትሎም በድህረ ጦርነት ወቅት መሠራት ያለባቸው አያሌ ተግባራት ካለመከናወናቸው ጋር ተያይዞ የጦርነቱ ጠባሳ አሁንም የሚታይ ነው። ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላም ቢሆን በትግራይ እና በአማራ ክልል አካባቢ ላይ ያሉ የቅራኔ ቦታዎች "ምን አይነት መፍትሔ ያገኛሉ?" የሚለው ሐሳብ በክልሉ ላይ ከፍተኛ ውጥረት ፈጥሮ የተለያዩ መላ ምቶች እየተሰጡ ጉዳዩን እያጦዙት እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው።

ይህ ውጥረት ባለበት ሁኔታ እንደ መልካም እርምጃ ሊወሰድና ድጋፍ ሊቸረው የሚገባውን የክልሎች ልዩ ኃይል ወደ ፌደራል ፀጥታ መዋቅር ውስጥ የመካተት ሂደት የተከናወነበት ደካማ መንገድ የፈጠረው ውዥንብር ኅብረተሰቡን ከፍተኛ ስጋትና ጥርጣሬ ውስጥ ጨምሮታል። ይባስ ብሎም በክልሉ ውስጥ በፋኖ አደረጃጀት ስም የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እና በአማራ ብሔርተኝነት ፖለቲካ ውስጥ እጃቸውን የሚያስገቡ ኃይሎች ያገኙትን ቀዳዳ ተጠቅመው ያስተጋቡት አደገኛ ትርክት የሰው ሕይወት እስከ መቅጠፍ አድርሷል። በእነዚህ "ካልደፈረሰ አይጠራም" ባይ ኃይሎች አማካኝነትም ለሀገራቸው እና ሕዝባቸው መስዋዕትነት የከፈሉ እውነተኛ ፋኖዎች በጅምላ በፅንፈኝነት እንዲታዩ ተደርጓል። ትላንት ሀገር በጭንቅ ውስጥ ስታልፍ አብረው አጥንታቸውን ከከሰከሱ፣ ደማቸውን ካፈሰሱ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ጋርም ግጭቶች እንዲፈጥሩ ምክንያት እየሆኑ ይገኛሉ።

በአማራ ክልል ፖለቲካ ውስጥ እጃቸውን ሰድደው እንዳሻቸው የሚፈነጩ፣ ኃላፊነት የማይሰማቸው፣ በመንግስት ውስጥና ከመንግስት ውጪ ያሉ ጽንፈኛ ዘውጌ ብሔርተኛ ኃይሎች በሚያቀነቅኑት ፅንፍ የወጣ ትርክት እና እንቅስቃሴ ንፁሃን ዜጎች መከራቸውን ሊበሉ አይገባም። በክልሉ ሰላም ለማስከበር እየተንቀሳቀሰ ያለው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሕዝቡ አለኝታና መከታው ሆኖ መስዋዕትነት እንደከፈለ ለማህበረሰቡ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ ጽንፈኛ ዘውጌ ብሔርተኝነት አንዱ መገለጫው ብሔራዊ እሴት ያላቸው ተቋማትን በዘውግ መነፅር እያዩ ማጥላላትና ከህዝብ ጋር ሆድና ጀርባ እንዲሆኑ ማድረግ መሆኑን ህዝቡ ልብ ሊል ይገባል።

ከሁሉም በላይ መንግሥት ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበት በመረዳት ጉዳዮቹን በትዕግስት እና በሆደ ሰፊነት በማስተናገድ፣ ህግና ሥርዓት እንዲከበር በመስራት ተጨማሪ የሰው ሕይወትም ሆነ የንብረት ውድመት ተከስቶ አላስፈላጊ ትርምስ እንዳይኖር የሚቻለውን ጥንቃቄ በማድረግ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አንጠይቃለን።

ከጠብመንጃ አፈ ሙዝና በጉልበት የሚመጣ መፍትሔ እንደሌለ በመረዳት ሁሉም ወገኖቻችን  በሰላማዊ መንገድ  መነጋገርና መመካከር ባህል በማድረግ ችግሮችን መፍታት ይኖርብናል። መንግሥት ከህወሓት እና እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብሎ ከሚጠራው ኃይል ጋር የተፈጠሩ ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት የሄደበትን የውይይት መንገድ ሁሌም ቅድሚያ ቢሰጠው መልካም መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

ይህ ማለት ግን ወንጀለኞች ያሻቸውን ሕገ ወጥ ተግባር እየፈጸሙና የሰው ሕይወት እየቀጠፉ በሰላም ስም እንዲከለሉ ሊፈቀድ ይገባል ማለት አይደለም፡፡ በኅብረተሰቡ ላይ የሚፈጸሙ ተራ ወንጀሎች፣ ግድያዎች እና ዝርፊያዎች ሕጋዊ በሆነ መንገድ ፍርድ የሚገባቸው እንደሆነ በፅኑ እናምናለን።

በጋዜጠኝነት፣ በአክቲቪስትነት እና በፖለቲከኛነት በንቃት የምትሳተፉ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያላችሁ አካላት ሁሉ ሕዝብን ለበለጠ አደጋ ከሚያጋልጡ ተግባራትና ቅስቀሳዎች በመቆጠብ አዎንታዊ ሚና እንድትወጡ እየጠየቅን፤ ለሚመለከታቸሁ አካላት ሁሉ  ከግጭት መለስ ያሉ ሰላማዊ መንገዶችን ሁሉ እንድታስቀድሙ ጥሪ እናቀርባለን።

#ሼር ማድረግ ግን ለምንድነው የምትረሱት? መረጃ አይናቅም ሼር ይደረግ


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
299 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 07:35:24 ረቡዕ ማለዳ! ሚያዝያ 18/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ ኢጋድ የኢትዮጵያ መንግሥትና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ተወካዮች ታንዛኒያ ዛንዚባር ውስጥ ንግግር መጀመራቸውን መግለጡን ሮይተርስ ዘግቧል። ኢጋድ የኹለቱ ወገኖች ንግግር ወደ ፖለቲካዊ ስምምነት ያመራል ብሎ እንደሚጠብቅ ቃል አቀባዩ ኑር መሐመድ ሼክ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ሮይተርስ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትን ወክሎ የሚደራደረውን ቡድን የሚመሩት የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን መኾናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ሰምቻለሁ ብሏል።

2፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን ጋር ትናንት በመቀሌ ጽሕፈት ቤታቸው መወያየታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል። ጌታቸው ውይይቱ ፌደራል መንግሥትና ሕወሃት በደረሱበት ሰላም ስምምነት አፈጻጸም፣ በፍትህ፣ በወንጀል ተጠያቂነት፣ በሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት መሰናክሎችና አሜሪካ በመልሶ ግንባታ መስክ ሊኖራት በሚገባ ሚና ዙሪያ እንደነበር ገልጸዋል።

3፤ ከ1 ሺህ 600 ቱርካዊያን ዜጎች ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በአውቶብስ መጓጓዛቸውን ከዲፕሎማቲክ ምንጮች መስማቱን የቱርኩ አናዶሉ ዜና ወኪል ዘግቧል። ቱርካዊያኑ ወደ መተማ እና ከዚያም ወደ ጎንደር የተጓጓዙት በአውቶብስ መኾኑን የጠቀሰው ዘገባው፣ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በአውሮፕላን መጓጓዛቸውን መስማቱን ጠቅሷል። ቱርካዊያኑን በኢትዮጵያ በኩል ከሱዳን የማስወጣቱ ተልዕኮ እንደቀጠለ መኾኑንም ዘገባው አመልክቷል።

4፤ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ትናንት ምሽት በሱዳን ግጭት ዙሪያ ምክክር አካሂዷል። የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት፣ የሱዳኑ ግጭት ወደ ጎረቤት አገራት ሊዛመት እንደሚችል እና የሱዳን ጎሳዎችና የታጠቁ ኃይሎችም በግጭቱ ጎራ ለይተው ለመዋጋት እየተዘጋጁ መኾኑን በማስጠንቀቅ፣ ሁለቱ የአገሪቱ ተፋላሚ ወገኖች ባስቸኳይ ውጊያውን እንዲያቆሙ ጥሪ አድርገዋል። በተመድ የሱዳን ተወካይ አል ሐሪት ሞሐመድም በግጭቱ ላይ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ የሰጡ ሲኾን፣ ሱዳን በግጭቱ ዙሪያ የውጫ ጣልቃ ገብነቶችን እንደማትቀበል ገልጸዋል።

5፤ የዓለም ምግብ ፕሮግራም አውሮፓ ኅብረት በጣለው ማዕቀብ ሳቢያ ከወራት በፊት ላትቪያ ውስጥ የተወረሰ የሩሲያ ማዳበሪያን ወደ ኬንያ እየተጓጓዝ መኾኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ወደ ኬንያ መጓጓዝ የጀመረው የመጀመሪያው ዙር 200 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ መኾኑን ዘገባው አመልክቷል። ላትቪያ ማዳበሪያውን ወደ ኬንያ የላከችው፣ የምትወርሰውን የሩሲያ ማዳበሪያ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በኢኮኖሚያቸው ላይ ጉዳት ላደረሰባቸው አገራት በነጻ እንዲከፋፈል በወሰነችው መሠረት እንደኾነ ተገልጧል።

6፤ የደቡብ አፍሪካ ገዥ ፓርቲ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግሬስ ደቡብ አፍሪካ ከዓለማቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እንድትወጣ መወሰኑን ፕሬዝዳንት ሴሪል ራማፎዛ መናገራቸውን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ዓለማቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በርካታ የዩክሬን ሕጻናትን በግዳጅ ወደ ሩሲያ ወስደዋል በማለት ባለፈው መጋቢት የእስር ማዘዣ እንዳወጣባቸው ይታወሳል። የፍርድ ቤቱ መመስረቻ ስምምነት ፈራሚ የኾነችው ደቡብ አፍሪካ በመጭው ነሐሴ በምታዘጋጀው የብሪክስ አገራት የመሪዎች ጉባኤ ላይ፣ ፕሬዝዳንት ፑቲን የሚገኙ ሲሆን፣ ደቡብ አፍሪካም የፍርድ መመስረቻ ስምምነት ፈራሚ እንደመኾኗ ፕሬዝዳንት ፑቲንን አስራ ለፍርድ ቤቱ የማስረከብ ግዴታ አለባት።

7፤ የሱማሌላንድ ራስ ገዝ መንግሥት ለተመድ ጸጥታው ምክር ቤት አቤቱታ ማስገባቱን የሱማሌላንድ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የራስ ገዟ መንግሥት ለጸጥታው ምክር ቤት ያስገባው አቤቱታ፣ በላስ አኖድ ከተማ በተቀሰቀሰው ግጭት የአልሸባብ፣ የፑንትላንድና የሱማሊያ ፌደራል መንግሥት ታጣቂዎች በቀጥታ ተሳታፊ ናቸው በማለት የሚከስ መኾኑን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። የሱማሌላንድ መንግሥት ሦስቱ አካላት ወረራና ጥቃት ፈጽመውብኛል በማለት ሲከስ መክረሙ ይታወሳል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
159 views04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 22:39:15
የ35 የአማራ፣ 2 የአፋር ባለሃብቶችና ድርጅቶች የባንክ አካውንት ታገደ። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
187 views19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 20:10:57 ማክሰኞ ምሽት! ሚያዝያ 17/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የተሻሻለውን የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ በስድስት ድምጸ ተዓቅቦ አጽድቋል። መንግሥት አዘጋጅቶ ያቀረበው የተሻሻለ ረቂቅ አዋጅ፣ ኅብረ ብሄራዊ ተዋጽዖውን የጠበቀ ዘመናዊ የአገር መከላከያ ሠራዊት ለመገንባት ማነቆ ኾነዋል የተባሉ የሕግ ማዕቀፎችን ለማሻሻል ያስችላል ተብሏል። ተሻሽሎ የጸደቀው አዋጅ፣ የሠራዊቱ አባላት የጡረታ መውጫ የእድሜ ጣሪያን አወሳሰን፣ የ12ኛ ክፍል ወይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በፍቃዳቸው ለኹለት ዓመት ብሄራዊ አገልግሎት የሚሰጡበትን አግባብ፣ የአገር ሕልውና ከባድ አደጋ ላይ በሚወድቅበት ጊዜ ከሠራዊቱ የተገለሉ የቀድሞ አባላትን መልሶ መቅጠር የሚቻልበትና ሌሎች የሠራዊቱ መብትና ጥቅማ ጥቅሞችን እንዳካተተ ተገልጧል።

2፤ በሱዳን የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሱዳኑ ውጊያ ቢያንስ ስምንት ኢትዮጵያዊያን እንደተገደሉና ሌሎች አራት ኢትዮጵያዊያን የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው መናገሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ኢትዮጵያዊያኑ ለሞት እና ለመቁሰል አደጋ የተዳረጉት፣ በተባራሪ ጥይት እና ከባድ መሳሪያ አረሮች ፍንጣሪ ሳቢያ መኾኑን ኢምባሲው መግለጡን ዘገባው አመልክቷል። ከአገሪቱ መውጣት የሚፈልጉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በአውቶብስ ወደ መተማ ለመሸኘት እየመዘገበ መኾኑን ኢምባሲው መግለጡን የጠቀሰው ዘገባው፣ የኢምባሲው ሠራተኞች ካርቱምን ለቀው ለኢትዮጵያ ቅርብ በኾነችው የሰሜን ሱዳኗ ገዳሪፍ ከተማ ሥራቸውን እያከናወኑ መኾኑን ጠቅሷል።

3፤ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ዛሬ መቀሌ መግባታቸውን የትግራይ ክልል ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ከልዩ መልዕክተኛ ሐመር ጋር በኢትዮጵያ የአሜሪካ ዋና ጉዳይ አስፈጻሚ ትሬሲ ጃኮብሰን አብረው መቀሌ ይገኛሉ ተብሏል። ሐመር ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ዘገባው አመልክቷል። ሐመር፣ ባለፈው ኅዳር የሕወሃት የሰላም ተደራዳሪዎችን በአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላን አሳፍረው ወደ ፕሪቶሪያ መውሰዳቸው ይታወሳል።

4፤ ትናንት በታንዛኒያ ጉብኝት ያደረጉት ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ ዛሬ በኮሞሮስ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። ደመቀ ዛሬ ከኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒ ጋር ተገናኝተው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሕወሃት ጋር በደረሰበት የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ዙሪያ ለፕሬዝዳንቱ ገለጻ እንዳደረጉላቸው ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ፕሬዝዳንት አዛሊ፣ በአፍሪካ ኅብረት አስተባባሪነት በሕዳሴ ግድብ ውዝግብ ላይ ተቋርጦ የቆየው የሦስትዮሽ ድርድር እንዲቀጥል ጥረት አደርጋለሁ በማለት ለደመቀ እንዳረጋገጡላቸው ተገልጧል። ፕሬዝዳንት አዛሊ የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ናቸው።

5፤ አውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕወሃት መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነት ዘላቂ አፈጻጸምን መሠረት በማድረግ ከመንግሥት ጋር ያቋረጠውን ግንኙነት ደረጃ በደረጃ እንደገና ወደነበረበት ለመመለስ ጥረት እንደሚያደርግ ትናንት ባወጣው መግለጫ በድጋሚ አስታውቋል። ኾኖም ኅብረቱ፣ በሰሜኑ ጦርነት ኹሉም ተፋላሚ ወገኖች የፈጸሟቸው ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና በሰላማዊ ሰዎችና ስደተኞች ላይ የተፈጸሙ የጦር ወንጀሎች በገለልተኛ መርማሪ አካል አማካኝነት ግልጽና ገለልተኛ ምርመራ የማድረግ ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው እጅግ አስፈላጊ ነገር መኾኑን በመግለጫው አመልክቷል። ኅብረቱ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ባሁኑ ወቅት እየታዩ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ውጥረቶችና ግጭቶች እንዳሳሰቡት ገልጦ፣ በአገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈንችግሮቹ በፖለቲካዊ እና ዲሞክራሲያዊ አግባብ በንግግር ብቻ እንዲፈቱ ጥሪ አድርጓል። ኅብረቱ በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን የበጀት ድጋፍ ያቋረጠው፣ ከኹለት ዓመት ከመንፈቅ በፊት ነበር።

6፤ የሱዳን ጦር ሠራዊትና ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት በአሜሪካ አደራዳሪነት ከትናንት እኩለ ሌሊት ጀምሮ የደረሱበት የ72 ሰዓታት የተኩስ አቁም ስምምነት ካርቱም ውስጥ ከሞላ ጎደል ተግባራዊ እየኾነ መኾኑን ዓለማቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። በኦምዱሩማንና ሌሎች ከተሞች ግን ውጊያው እንደቀጠለ መኾኑን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የጦር ሠራዊቱ ዋና አዛዥ ጀኔራል አል ቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎ ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ ተገናኝተው ፊት ለፊት እንዲነጋገሩ ጥረቶች እየተደረጉ መኾኑን የግብጽ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ1241 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ2066 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 64 ብር ከ3057 ሳንቲም እና መሸጫው 65 ብር ከ5918 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ59 ብር ከ6015 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ60 ብር ከ7935 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
207 views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 07:27:49 ማክሰኞ ማለዳ! ሚያዚያ 17ቀን 2015 የEMS አበይት ዜናዎች

1. የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ ዛሬ ፓርላማ ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። አዋጁ የሠራዊቱ አባላትን ጥቅም፣ የማዕረግ ዕድገት እና የምልመላ ጉዳዮችን ጭምር ይዟል። ቀደም ሲል አዋጁ ክርክር ተደርጎበት ወደ ኮሚቴ ተመልሶ ነበር።

2. በኦሮሞ ነፃነት ጦር (ኦነግ ሸኔ)ና በመንግስት መካከል ይደረጋል የተባለው ድርድር ዛሬ በታንዛኒያ እንደሚጀመር ይጠበቃል። ከድርድሩ አንድ ቀን አስቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ታንዛኒያ ገብተዋል። ደመቀ ታንዛንያን ጨምሮ በአራት የአፍሪቃ ሀገራት ጉብኝት የማድረግ ዕቅድ አላቸው። በታንዛኒያ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል። የደመቀ የታንዛኒያ ጉብኝት ከኦነግ ሸኔ ጋር ከሚደረገው ድርድር ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ አልተገለፀም።

3. ብሄራዊ የተሃድሶ ኮምሽን ተግባራዊ ስራ ለመጀመር መዘጋጀቱን አስታወቀ። ባለፉት ሶስት ወራት ኮምሽኑ ዓላማውን በማስተዋወቅና ግብረ መልስ በመሰብሰብ ላይ አተኮሮ ነበር። ኮምሽኑ በሀገሪቱ ያለ እስከ ሶስት መቶ ሺ የሚደርሱ ተዋጊዎችን በትኖ በመደበኛ ሕይወት የማቋቋም ሀላፊነት አለበት።

4. የኦሮምያ ሕብረት ስራ ባንክ በአዲስ አበባ ረጅሙን ፎቅ ለመገንባት መዘጋጀቱን ገለፀ። ፎርቹን እንደዘገበው ባንኩ 65 ወለል ያለው አዲስ ዋና መስሪያቤቱን ፍልውሃ አካባቢ ለመገንባት እየተዘጋጀ ነው። ከዚህ ቀደም የከተማው ረጅም ፎቅ 46 ወለል ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያቤት ሕንፃ ነው።

5. የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኀይልና የሱዳን ጦር ሰራዊት ከትናንት ዕኩለ ሌሊት ጀምሮ በመላው ሀገሪቲ ለ72 ሰዓታት የሚቆይ የተኩስ አቁምማድረጋቸውን አውጀዋል። የተኩስ አቁሙ ስምምነት የተደረሰው በአሜሪካ መንግስት አደራዳሪነት ሲሆን በዚሁ የዕፎይታ ጊዜ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግና የውጪ ሀገር ዜጎችን ለማስወጣት ታቅዷል። የኣሜሪካ የውጪጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን የተኩስ አቁሙን ዘላቂ ለማድረግ ሁሉም ወገን ጥረት እንዲያደርግ ጠይቀዋል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja
243 views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 21:25:12
ኢትዮጵያን እንወቅ ይህ ቦታ ምን ይባላል?
A~ Baro
B~ Tekeze
C~Abay(Nile)
227 views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ