Get Mystery Box with random crypto!

ማክሰኞ ማለዳ! ሚያዚያ 17ቀን 2015 የEMS አበይት ዜናዎች 1. የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ ዛሬ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ማክሰኞ ማለዳ! ሚያዚያ 17ቀን 2015 የEMS አበይት ዜናዎች

1. የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ ዛሬ ፓርላማ ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። አዋጁ የሠራዊቱ አባላትን ጥቅም፣ የማዕረግ ዕድገት እና የምልመላ ጉዳዮችን ጭምር ይዟል። ቀደም ሲል አዋጁ ክርክር ተደርጎበት ወደ ኮሚቴ ተመልሶ ነበር።

2. በኦሮሞ ነፃነት ጦር (ኦነግ ሸኔ)ና በመንግስት መካከል ይደረጋል የተባለው ድርድር ዛሬ በታንዛኒያ እንደሚጀመር ይጠበቃል። ከድርድሩ አንድ ቀን አስቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ታንዛኒያ ገብተዋል። ደመቀ ታንዛንያን ጨምሮ በአራት የአፍሪቃ ሀገራት ጉብኝት የማድረግ ዕቅድ አላቸው። በታንዛኒያ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል። የደመቀ የታንዛኒያ ጉብኝት ከኦነግ ሸኔ ጋር ከሚደረገው ድርድር ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ አልተገለፀም።

3. ብሄራዊ የተሃድሶ ኮምሽን ተግባራዊ ስራ ለመጀመር መዘጋጀቱን አስታወቀ። ባለፉት ሶስት ወራት ኮምሽኑ ዓላማውን በማስተዋወቅና ግብረ መልስ በመሰብሰብ ላይ አተኮሮ ነበር። ኮምሽኑ በሀገሪቱ ያለ እስከ ሶስት መቶ ሺ የሚደርሱ ተዋጊዎችን በትኖ በመደበኛ ሕይወት የማቋቋም ሀላፊነት አለበት።

4. የኦሮምያ ሕብረት ስራ ባንክ በአዲስ አበባ ረጅሙን ፎቅ ለመገንባት መዘጋጀቱን ገለፀ። ፎርቹን እንደዘገበው ባንኩ 65 ወለል ያለው አዲስ ዋና መስሪያቤቱን ፍልውሃ አካባቢ ለመገንባት እየተዘጋጀ ነው። ከዚህ ቀደም የከተማው ረጅም ፎቅ 46 ወለል ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያቤት ሕንፃ ነው።

5. የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኀይልና የሱዳን ጦር ሰራዊት ከትናንት ዕኩለ ሌሊት ጀምሮ በመላው ሀገሪቲ ለ72 ሰዓታት የሚቆይ የተኩስ አቁምማድረጋቸውን አውጀዋል። የተኩስ አቁሙ ስምምነት የተደረሰው በአሜሪካ መንግስት አደራዳሪነት ሲሆን በዚሁ የዕፎይታ ጊዜ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግና የውጪ ሀገር ዜጎችን ለማስወጣት ታቅዷል። የኣሜሪካ የውጪጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን የተኩስ አቁሙን ዘላቂ ለማድረግ ሁሉም ወገን ጥረት እንዲያደርግ ጠይቀዋል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja