Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkun_zemede — Zemedkun Bekele (ዘመዴ) Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkun_zemede — Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
የሰርጥ አድራሻ: @zemedkun_zemede
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-20 21:28:52 ሰበር ዜና

በባህር ዳር ማምሻውን ቦምብ ፈንድቷል። በአልማ ጽ/ቤት፡ ሰመርላንድ ሆቴል አከባቢ ፍንዳታው እንደደረሰ ታውቋል። የሪፐብሊካን ጋርድ በቦታው ተገኝቷል። ስለደረሰው ጉዳት ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። በባህር ዳር ዛሬ ከቀትር በኋላ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህና አቶ ተመስገን ጥሩነህ ሀሙስ የተጀመረውን ስብሰባ ሲመሩት እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።
#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
247 views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 12:03:29
15 የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ መምህራን በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው አለፈ

ቅዳሜ ግንቦት 12 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) 15 የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ መምህራን ዛሬ ማለዳ ለማስተማር ወደ ሻሸመኔ ካምፓስ በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰው የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡

የሮቤ ከተማ ከንቲባ ንጋቱ ሞቱማ ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት በተፈጠረው አደጋ እስካሁን 15 የዩንቨርሲቲው መምህራን ሕይወት ማለፉን ገለጸዋል ሲል ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
287 views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 09:23:32 ለሴት እህቶች ጠቃሚ ምክር
  በፌስቡክ ሚሴንጀር ሀይ አለሽ
  ሳትመልሺ ወደ ፕሮፋይሉ አቀናሽ
  ጥሩ መኪና አለው አለባበሱም ሆነ አቋሙ ያምራል
  በድጋሚ ሀይ አለሽ
  አሁን ግን በደስታ መለሽለት
  መልእክት መለዋወጥ ተጀመረ
  በአካል ለመገናኘት ቀጠሮ ተያዘ
  ጥሩ ለበስሽ ሽቶ ሜክአፕ ብቻ ተውበሻል
  ተገናኛችሁ
  ውድ የሆነ መዝናኛ ቦታ ወሰደሽ
  ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ጀመራችሁ
  እጆችሽን በፍቅር ያሻሽሻል በቀልዶች ያስቅሻል
  አይኖችሽን በፍቅር አይን ተመልክቶ ፈገግታ ይመግብሻል
  ብዙ ትውውቅ ያላችሁ ያህል ተሰማሽ
  ክፍል እንድትይዙ ጠየቀሽ ተስማማሽ
  ምቾት እንዲሰማሽ አደረገሽ
  በፍቅር በስሱ ከንፈሮችሽን መሳም ጀመረ
  ትክክል አለመሆኑ ቢገባሽም ደስታ ተሰምቶልሻ
  በእርጋታ ወደ አልጋው ወሰደሽ
  ለመቃወም አቅሙን አጣሽ
  ሌላው ቢቀር መከላከያ ለመጠቀም ሀሳብ አቀረብሽ
  በስሜት ጦፎ ስለነበር ሊሰማሽ አልቻለም
  አንቺም ተሸነፍሽ
  ፍልሚያውን ወደድሽው እርካታም አገኘሽ
  ከፍሪጅም ቀዝቃዛ ውሃ አምጥቶ እራሱ አጠጣሽ
  የሚያሳይሽ ክብር እጅጉን ማረከሽ
  ራስሽን ዕድለኛ አድርገሽም ቆጠርሽ
  የምትፈልጊው አይነት ወንድ እንዳገኘሽ ተሰማሽ
  ልብስሽን ለባበስሽ
  ወደ ታክሲ መሳፈሪያም አደረሰሽ
  ጉንጮችሽን ስሞ የደስታ ጊዜ ማሳለፉን ገለፀልሽ
  ለጉዞሽም ገንዘብ በእጅሽ አስጨበጠሽ
  ከልብሽ ፈገግ በማለት ነገ እንገናኝ ፍቅር አልሽው
  እሱ ግን መልስ አልሰጠሽም
  በደስታ ፈገግ እንልዳሽ ተጉዘሽ እቤት ደረስሽ
  በሰላም እቤት እንደደረስሽ መሴጅ ላክሽለት
  ኦንላየን ቢሆንም መልስ አልመለሰልሽም
  ግራ ተጋብተሽ በድጋሚ ፃፍሽለት
  አሁንም መልስ የለም
  ከደቂቃዎች በኃላ ከፌቡ ጓደኞችሽ ሊስት አጣሽው
  ብሎክ መደረግሽ ታወቀሽ
  ቀን ሳምንት ወራት አለፉ
  ህምመ ይሰማሽ ጀመር ድካም ክብደት መቀነስ
  ወደ ሆስፒታል በመሄድ ምርመራ አደረግሽ
  ከቆይታ በኃላ ነርሷ የምርመራ ውጤት ይዛ መጣች
  ኤችአይቪ ፖሰቲቭ እና እርጉዝ እንደሆንሽ ተነገረሽ
  እንዴት?
  ከእውነታው ጋር ተጋፈጥሽ
  ጭንቀት ነገሰብሽ በፍርሃት ተዋጥሽ
  ተስፋቢስነት ስሜት አልባነት ተሰማሽ
  ሞት ወደ አንቺ መቃረቡ ተገለጠልሽ
  ሁኔታዎች ወደ ኃላ ተመልሰው ብታድሻቸው ተመኘሽ
  እረፍዷል
  ወደ ሰማይ በማንጋጠጥ ፀሎት አደረስሽ
□ ይህችን ሴት አትሁኚ
□ በስሜታዊነት አትመሪ
□ በሀብት በንዋይ ሰውን አትመዝኚ
□ ሴት ልጅሽ እንድትሆንልሽ የምትመኚያ አይነት ሴት ሁኚ

ማህበራዊ ሚዲያን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም ፡፡ ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ፡፡ በምድር ላይ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና ፡፡

ስለዚህ አንተም ይህ አሁን ያነበብከው መጣጥፍ ትምህርት ሰጪ ሆኖ ካገኘሀው የእርስዎ ዘመዶችህ እንዲያነቡትና ትምህርት እንዲወስዱ ዘንድ ሼር ያድርጉላቸው ።

አዳዲስና ትምህርት ሰጪ እንዲሁም ፈጣንና ተማኝ ዜናዎችን በየቀኑ በቴግራም እንዲደርሳችሁ ትፈልጋላችሁ እንግዲያውስ ይሄ ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ነው ግቡና Join አድርጉን ።
@emsmereja
266 views06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 08:38:37 ቅዳሜ ጠዋት! ግንቦት 12/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ምክር ቤት የዓለም ምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት በትግራይ ክልል ያቋረጡትን የዕርዳታ ሥርጭት እንዲቀጥሉ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ምክር ቤቱ ከትግራይ የዕርዳታ እህል መዘረፉን ማረጋገጡን ገልጦ፣ "የዕርዳታ ሥርጭት ተቋርጦ መቀጠሉ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል" ብሏል። ምክር ቤቱ፣ ፌደራልና የክልሉ መንግሥት በዕርዳታ ዝርፊያው ላይ ምርመራ አድርገው አጥፊዎችን ተጠያቂ እንዲያደርጉም ምክር ቤቱ አሳስቧል። ሁለቱ ድርጅቶች ባለፈው ወር የዕርዳታ ሥርጭት ያቋረጡት፣ በክልሉ የዕርዳታ እህል ተዘርፎ ገበያ ላይ እንደተሽጠ ደርሰንበታል በማለት ነበር።

2፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ "የኤርትራ ሠራዊት የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ስምምነት ተቆጣጣሪ ሥራን እያደናቀፈ ነው" በማለት መክሰሳቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ጌታቸው ይህን የተናገሩት፣ በሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ዙሪያ ለተቆጣጣሪ ቡድኑ በሰጡት ገለጻ መኾኑን ዘገባው ጠቅሷል። የተቆጣጣሪ ቡድኑ ሃላፊ ሜጀር ጀኔራል ስቲፈን ራዲና፣ ቡድናቸው ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውጭ ሌሎች ኃይሎች ይኑሩ አይኑሩ ለማጣራት በቀጣዩ ወር ደቡባዊና ምዕራብ ትግራይን እንደሚጎበኝ መናገራቸውን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።

3፤ ዓለም ባንክ የኢትዮጵያ መንግሥት ለአገሪቱ ችግሮች ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን የሚያሰፍኑ መፍትሄዎችን እንዲያመጣ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። በመላ አገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መኾኑን የገለጠው ባንኩ፣ የሰላም ግንባታ፣ የእርቅና ዘላቂ ልማት መርሃ ግብሮችን መደገፉን እንደሚቀጥል ገልጧል። ባንኩ ድጋፍ የሚደግፋቸው ዘርፎች፣ የሁሉንም ሕዝብ ፍላጎቶች የሚመልሱ ስለመኾናቸውና ከመድልዖ የጸዱ፣ በሕዝባዊ ምክክርና አሳታፊነት ላይ መመስረታቸውን፣ የንብረት ባለቤትነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት መስፈኑን በቅድሚያ እንደሚያረጋግጥ አመልክቷል። ባንኩ እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ የምግብ ዋስትና፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ ሴቶችን ማብቃትና የማኅበራዊና የአካባቢ ጥበቃ የመሳሰሉ መሠረታዊ አገልግሎቶችን በማገዝ ላይ እገኛለኹ ብሏል።

4፤ ዘንድሮ ከጋምቤላና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ወደ ብሄራዊ ባንክ የገባው የወርቅ ምርት በከፍተኛ መጠን መቀነሱን ዶይቸቨለ ዘግቧል። ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር፣ ከቤንሻንጉል ለባንኩ የገባው ወርቅ በ1 ሺህ 400 ኪሎ ግራም እንዲሁም ከጋምቤላ የገባው በ900 ኪሎ ግራም መቀነሱን ዘገባው አመልክቷል። ከሁለቱ ክልሎች የሚገባው ወርቅ የቀነሰው፣ የሕገወጥ ንግድ በመስፋፋቱ እንደኾኑ ተገልጧል። መንግሥት የወርቅ ሕገወጥ ንግድን ለመቆጣጠር በቅርቡ ግብረ ኃይል ማቋቋሙ ይታወሳል።

5፤ በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ጠቅላላ ጉባኤው ተስተጓጉሎበት የነበረው ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በቀጣዩ ዕሁድ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን ሊያካሂድ መኾኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን የሚያካሂደው፣ በኢትዮጵያ ሆቴል አዳራሽ መኾኑን ገልጧል። ምርጫ ቦርድ ባልደራስና እናት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔያቸው በጸጥታ ኃይሎች መሰናከሉን አውግዞ፣ የራሱን አዳራሽ ለፓርቲዎቹ እንደሚፈቅድ ገልጦ ነበር።

5፤ ዛሬ አዳሩን በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በቆጂ ከተማ ከ5:00 እስከ ሰባት ሰዓት ድረስ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ነበር። ተኩሱን የጀመረው እራሱን የኦሮሞ ነፃ አውጪ ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ሲሆን በዚህ የተኩስ ልውውጥ አንድ የቀበሌ አመራር መገደሉን ምንጮች ገልፀዋል። የተኩሱ አላማ እስረኞችን ለማስፈታት ነበርም ተብሏል።
#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
224 views05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 23:46:15
በመጨረሻም ተሸነፈች

ነፍስ ይማር ሳምሪ


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
232 views20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 20:31:12 ዓርብ ምሽት! ግንቦት 11/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ላቀደው ብሄራዊ ምክክር አጀንዳ ሊኾኑ የሚችሉ ጉዳዮችን ከዛሬ ጀምሮ ከኅብረተሰቡ መቀበል መጀመሩን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ኮሚሽኑ በቀጣዩ ሳምንት በሲዳማ፣ ጋምቤላ፣ ሐረሬና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በአገራዊ ምክክሩ ሂደት የሚሳተፉ ግለሰቦችን መለየት እንደሚጀምር በመግለጫው አመልክቷል። ኅብረተሰቡ የአገራዊ ምክክሩ ተሳታፊዎችን የሚመርጠው በወረዳ ደረጃ መኾኑን ኮሚሽኑ ገልጧል።

2፤ ገቢዎች ሚንስቴር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያሻሻለውን የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል። አዋጁን ማሻሻል ያስፈለገው፣ በአንዳንድ ምርቶች ላይ የተጣሉ ተደራራቢ ኤክሳይስ ታክሶችን ለማንሳት፣ ከአንዳንድ ምርቶች ላይ ኤክሳይስ ታክሱን ሙሉ በሙሉ ለማንሳትና የቴሌኮምንኬሽን አገልግሎቶችን ኤክሳይስ ታክስ ለማስከፈል እንደኾነ ሚንስቴሩ ገልጧል። የተሻሻለው አዋጅ፣ በሞባይል ኢንተርኔትና የሞባይል ድምጽና የጽሁፍ መልዕክቶች ላይ የ5 በመቶ ኤክሳይስ ታክስ የጣለ ሲኾን፣ ባንጻሩ በኪሮዚን፣ ቤንዚንና ናፍጣ ላይ የተጣለውን የ30 በመቶ ኤክሳይስ ታክስ ወደ 15 በመቶ ዝቅ እንዳደረገው ተገልጧል።

3፤ በየመን በረሃ ላይ ሞተው በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የአስከሬናቸው ምስሎች ሲሰራጩ የሰነበቱት ፍልሰተኞች ኢትዮጵያዊያን እንደኾኑ መረጋገጡን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ፍልሰተኞቹ ሕይወታቸው ያለፈው በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ከየመን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ በእግር በመጓዝ ላይ ሳሉ መኾኑን የዓይን ምስክር ፍልሰተኞች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። 20 ያህል የሚኾኑት ወንድና ሴት ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ሕይወታቸው ያለፈው፣ በድካም፣ ርሃብና ውሃ ጥም መኾኑን የዓይን ምስክሮቹ መናገራቸውን ዜና ምንጩ አመልክቷል። ዓለማቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት፣ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያንና ሱማሊያዊያን ፍልሰተኞች በፑንትላንድ፣ ሱማሌላንድና ጅቡቲ በኩል ወደ የመን የሚሻገሩበት መስመር በርካቶችን ለሞት፣ ለአስገድዶ መደፈርና ድብደባ እያጋለጣቸው የሚገኝ እጅግ አደገኛ መስመር መኾኑን በተደጋጋሚ ይገልጣል።

4፤ የኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን መንግሥታት ሀለቱን አገራት የሚያገናኝ የመንገድ ግንባታ ስምምነት ዛሬ ጁባ ውስጥ መፈራረማቸውን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። መንገዱ ከተገነባ፣ የሁለቱን አገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስርና የጋራ የድንበር ጸጥታ ይበልጥ እንደሚያጠናክረው በስምምነቱ ፊርማ ስነ ሥርዓት ላይ ተገልጧል። የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ፣ ምዕራብ ኢትዮጵያን ከሰሜን ምሥራቅ የደቡብ ሱዳን ግዛቶች ጋር የሚያገናኝ ነው።

5፤ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መርማሪ ፖሊስ በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩ ስድስት ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራውን አጠናቆ እንዲያቀርብ የ7 ቀናት ጊዜ መስጠቱን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ችሎቱ ውሳኔውን የሰጠው፣ የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆችና መርማሪ ፖሊስ ትናንት ያቀረቡትን መከራከሪያ ከመረመረ በኋላ ነው። ከተጠርጣሪዎቹ መካከል፣ የ"ንቃት ኢትዮጵያ" ዩትዩብ ጣቢያ ባለቤት መስከረም አበራ ትገኝበታለች። መርማሪ ፖሊስ፣ በቀደሙት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜያት ከባንኮች የተጠርጣሪዎችን የገንዘብ ዝውውር ሰነዶች ማሰባሰቡን፣ የተጠርጣሪዎቹን የተከሳሽነት ቃላቸውን መቀበሉን፣ በተጠርጣሪዎቹ መኖሪያ ቤት ብርበራ ማካሄዱንና ሌሎች ክንውኖችን መጥቀሱን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

6፤ የሱማሊያ ደኅንነት ከሞቃዲሾ ወደብና አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለአልሸባብ ሊላኩ የነበሩ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ጦር መሳሪያዎችና ተቀጣጣይ ፈንጂዎች መያዙን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። በሕገወጥ መንገድ ከገባው ጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የሱማሊያ ባለስልጣናት መናገራቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ጦር መሳሪያዎቹና ተቀጣጣይ ፈንጂዎች ከየት አገር እንደገቡና በቁጥጥር ስር የዋሉትን ግለሰቦች ማንነት ባለሥልጣናቱ እንዳልጠቀሱ ተገልጧል። የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ከ30 ዓመት በፊት በሱማሊያ ላይ የጣለውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እስካኹን አላነሳም።

7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ2545 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ3398 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 64 ብር ከ3987 ሳንቲምና መሸጫው 65 ብር ከ6867 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ58 ብር ከ6222 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ59 ብር ከ7946 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
249 views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 12:57:35 አንድ ግለሰብ 7 የህገወጥ ቤት አፍራሽ ግብረሀይሎችን ገደለ
በአዲስ አበባ ለገጣፎ ቤቱን በማፍረስ ላይ የነበሩ አፍራሽ ግብረሀይሎችን ማፍረስ እንዲያቆሙ ለማድረግ ሲከላከል ሚስቱ ተወው ይገሉሀል በማለት መሀል ትገባለች። ቤት አፍራሾቹ አባውራውን ለመምታት የተኮሱት ጥይተ እሱን ስቶ ሚስቱን ይገድላታል።
ባልየውም የሰውን ጎጆ አፍርሶ ማን በሰላም እንደሚኖር እናያለን በማለት፣ በገዛው መሳሪያ 7ቱን ቤት አፍራሽ ግብረሃሎችን ከገደላቸው በኋላ ተሰውሯል ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።
#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
266 views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 08:14:00

297 views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 07:55:18 ዓርብ ጠዋት! ግንቦት 11/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎች እንደገና ባግባቡ መፈተሽ እንደሚያስፈልግ ትናንት በተጀመረው የክልሉ አመራሮች ኮንፈረንስ ላይ ተናግረዋል። የሕዝቡ ነባር ጥያቄዌች ካሏቸው መካከል፣ የማንነትና ወሰን ጥያቄ፣ የሕገመንግሥት ማሻሻያ እና የብሄሩ ተወላጆች በማናቸውም የአገሪቱ ክፍሎች የመኖር መብታቸውን ጠቅሰው፣ የብሄሩ ጥያቄዎች የሚመለሱበትን መውጫ መንገድ ማስቀመጥ አስፈላጊ መኾኑን ገልጸዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ገዥው ፓርቲ የሕዝቡን ጥያቄ በመመለስ ሂደት ላይ እንደሚገኝ አውስተዋል። በክልሉ ሕዝብና በመሪ ድርጅቱ መካከል አለመተማምን እንዲጎለብት የሚሠሩ "ጽንፈኛ ኃይሎች" መኖራቸውንም ይልቃል ጠቅሰዋል።

2፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሸገር ከተማ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የሚያካሂደውን የመስጅድ ማፍረስ እንቅስቃሴ እንዲያስቆሙ ጠቅላይ ሚንስትሩን በደብዳቤ መጠየቁን አስታውቋል። ምክር ቤቱ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ደብዳቤ የጻፈው፣ የመስጅድ ማፍረሱ ድርጊት ባስቸኳይ እንዲቆም ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ለጻፈው ደብዳቤ ምላሽ ባለማግኘቱ እንደኾነ ገልጧል። ምክር ቤቱ ዐቢይ፣ በጉዳዩ ላይ "የሟያዳግም መፍትሄ" እንዲሰጡት ጠይቋል። ምክር ቤቱ፣ ጉዳዩ "በቀላሉ የሚታይ ሳይኾን የሕዝበ ሙስሊሙ የሃይማኖቱ ዋነኛ ሕልውናው" ነው ብሏል።

3፤ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ከአፍሪካ ኅብረት የሰላም ስምምነት ተቆጣጣሪ ቡድን መሪ ከኬንያዊው ጀኔራል ራዲና ጋር ትግራይ ውስጥ መነጋገራቸውን በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። አምባሳደር ኮቢያ፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጀኔራል ጻድቃን ገብረ ተንሳይ ጋር ጭምር መወያየታቸውን ገልጸዋል። አምባሳደር ኮቢያ ከረቡዕ:ለት ጀምሮ በክልሉ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።

4፤ በአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር በቀን በአማካይ ከ800 በላይ ሰዎች ከሱዳኑ ጦርነት እየሸሹ በመተማ በኩል እንደሚገቡ ማስታወቁን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል። በዞኑ ውስጥ ለስደተኞቹና ጥገኝነት ጠያቂዎቹ ቋሚ መጠለያ ካምፕ ለመገንባት 56 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን የዞኑ አስተዳደር መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ፣ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የተመድ ሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
269 views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 20:09:46 ሐሙስ ምሽት! ግንቦት 10/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የፌደራልና ክልል መንግሥታት ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንደገጠማቸው ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች። መንግሥት በርካታ የግዥ ጨረታዎችን የሰረዘ ሲኾን፣ አንዳንድ ክልሎች ደሞ ለመንግሥት ሠራተኞች ለወራት ደመወዝ አልከፈሉም። በካሳ ክፍያና ከግንባታ ግብዓቶች ዋጋ መናር ሳቢያ፣ 40 መንግሥታዊ ፕሮጀክቶች በእንጥልጥል ላይ እንደኾኑ የፌደራል መንገዶች አስተዳደር ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። መንግሥት ለበጀት ዓመቱ ካጸደቀው 786 ቢሊዮን ብር ውስጥ፣ በርካታ ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የተመደበላቸው የበጀት ድጎማ ሙሉ በሙሉ አልተለቀቀላቸውም። የዘንድሮው በጀት ሲጸድቅ፣ በብድርና በበጀት ድጋፍ የሚሞላ የ300 ቢሊዮን ብር ጉድለት ነበረበት።

2፤ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በባሕርዳር ከተማ ክልል ዓቀፍ ኮንፈረንስ መጀመሩን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በኮንፈረንሱ ላይ ከ1 ሺህ 400 በላይ ከፍተኛና መካከለኛ የፓርቲና የመንግሥት አመራሮች እንደሚሳተፉ ዘገባው አመልክቷል። የኮንፈረንሱ ዓላማ፣ በክልሉ ወቅታዊ ፈተናዎችና ችግሮች ዙሪያ በመወያየት የፓርቲውንና የክላሉን መንግሥት ጥንካሬ ማጎልበት እንደኾነና በመድረኩ ላይ ጠንካራ የውስጠ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ትግል ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ፓርቲው መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል።

3፤ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሠረተበትን 60ኛ ዓመት ከግንቦት 17 ጀምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች አዲስ አበባ ውስጥ ለአንድ ዓመት ያህል እንደሚከበር የውጭ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን የአገር ውስጥ ዜና አውታሮች ዘግበዋል። መርሃ ግብሮቹ፣ ፓን አፍሪካኒዝምን በማጠናከር እና አፍሪካ ኅብረት እኤአ በ2063 ዓ፣ም ለማሳካት የያዛቸውን ግቦች በማውሳት ላይ የሚያተኩሩ እንደሚኾኑ ቃል አቀባዩ መግለጣቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። የኅብረቱ አባል አገራት በዓሉን በየራሳቸው መንገድ እንደሚያከብሩት ተናግረዋል ተብሏል።

4፤ የ"ንቃት ኢትዮጵያ" ዩትዩብ ጣቢያ ባለቤት መስከረም አበራና ሌሎች አምስት ተከሳሾች ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተሰጣቸው ቀጠሮ መሠረት እንደቀረቡ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። መርማሪ ፖሊስ በባለፈው ቀጠሮ፣ በተጠርጣሪዎቹ ላይ "በአማራ ክልል ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር" የሚለውን የምርመራ መዝገቡን ቀይሮ "የሽብር ወንጀል" መዝገብ በመክፈት፣ የ14 ቀናት ተጨማሪ ቀጠሮ እንደተሰጠው ይታወሳል። መርማሪ ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲሰጠው ዛሬም በድጋሚ መጠየቁንና፣ የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆችም የደንበኞቻቸው የዋስትና መብት እንዲከበር መጠየቃቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ችሎቱ፣ የሁለቱን ወገኖች ክርክር መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ተብሏል።

5፤ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ የሚመሩት ልዑካን ቡድን ዛሬ በትግራይ ክልል በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ከሁለት ዓመት በላይ የመማር ማስተማር ሥራውን ካቋረጠው የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር መወያየቱን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። የአዲግራት ዩኒቨርስቲ አመራሮች በጦርነቱ ወቅት በዩኒቨርስቲው ላይ የደረሰውን ውድመትና ሌሎች ጉዳቶች የያዘ ዝርዝር ሰነድ ለኅብረቱ ልዑካን ቡድን ማስረከባቸውን ዘገባው አመልክቷል። አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ በትግራይ ክልል ከሚገኙ አራት የፌደራል ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ነው፡ የአውሮፓ ኅብረት ልዑካን ቡድን ከአዲግራት ቀጥሎ፣ በሽሬ ከተማና አካባቢዋ በሚገኙ መሠረተ ልማቶች ላይ ጦርነቱ ያደረሰውን ጉዳት ይጎበኛል ተብሏል።

6፤ ትምህርት ሚንስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 13 ድረስ በሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መፈተኛ ማዕከላት ውስጥ እንደሚሰጥ አስታውቋል። ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መውጫ የተዘጋጀውን ፈተና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ጭ እንደሚወስዱት ሚንስቴሩ ገልጧል። ሚንስቴሩ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና የሚሰጠው፣ ሁሉም ተመራቂዎች በተመረቁበት የትምህርት መስክ በሥራ ዓለም ለመሠማራት የሚያበቃቸውን የእውቀትና ክህሎት ደረጃ ማሟላት አለማሟላታቸውን ለማረጋገጥ ነው።

7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ0576 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ1388 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 64 ብር ከ0924 ሳንቲምና መሸጫው 65 ብር ከ3742 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ59 ብር ከ3174 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ60 ብር ከ6037 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
258 views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ