Get Mystery Box with random crypto!

ዓርብ ጠዋት! ግንቦት 11/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች 1፤ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዓርብ ጠዋት! ግንቦት 11/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎች እንደገና ባግባቡ መፈተሽ እንደሚያስፈልግ ትናንት በተጀመረው የክልሉ አመራሮች ኮንፈረንስ ላይ ተናግረዋል። የሕዝቡ ነባር ጥያቄዌች ካሏቸው መካከል፣ የማንነትና ወሰን ጥያቄ፣ የሕገመንግሥት ማሻሻያ እና የብሄሩ ተወላጆች በማናቸውም የአገሪቱ ክፍሎች የመኖር መብታቸውን ጠቅሰው፣ የብሄሩ ጥያቄዎች የሚመለሱበትን መውጫ መንገድ ማስቀመጥ አስፈላጊ መኾኑን ገልጸዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ገዥው ፓርቲ የሕዝቡን ጥያቄ በመመለስ ሂደት ላይ እንደሚገኝ አውስተዋል። በክልሉ ሕዝብና በመሪ ድርጅቱ መካከል አለመተማምን እንዲጎለብት የሚሠሩ "ጽንፈኛ ኃይሎች" መኖራቸውንም ይልቃል ጠቅሰዋል።

2፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሸገር ከተማ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የሚያካሂደውን የመስጅድ ማፍረስ እንቅስቃሴ እንዲያስቆሙ ጠቅላይ ሚንስትሩን በደብዳቤ መጠየቁን አስታውቋል። ምክር ቤቱ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ደብዳቤ የጻፈው፣ የመስጅድ ማፍረሱ ድርጊት ባስቸኳይ እንዲቆም ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ለጻፈው ደብዳቤ ምላሽ ባለማግኘቱ እንደኾነ ገልጧል። ምክር ቤቱ ዐቢይ፣ በጉዳዩ ላይ "የሟያዳግም መፍትሄ" እንዲሰጡት ጠይቋል። ምክር ቤቱ፣ ጉዳዩ "በቀላሉ የሚታይ ሳይኾን የሕዝበ ሙስሊሙ የሃይማኖቱ ዋነኛ ሕልውናው" ነው ብሏል።

3፤ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ከአፍሪካ ኅብረት የሰላም ስምምነት ተቆጣጣሪ ቡድን መሪ ከኬንያዊው ጀኔራል ራዲና ጋር ትግራይ ውስጥ መነጋገራቸውን በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። አምባሳደር ኮቢያ፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጀኔራል ጻድቃን ገብረ ተንሳይ ጋር ጭምር መወያየታቸውን ገልጸዋል። አምባሳደር ኮቢያ ከረቡዕ:ለት ጀምሮ በክልሉ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።

4፤ በአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር በቀን በአማካይ ከ800 በላይ ሰዎች ከሱዳኑ ጦርነት እየሸሹ በመተማ በኩል እንደሚገቡ ማስታወቁን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል። በዞኑ ውስጥ ለስደተኞቹና ጥገኝነት ጠያቂዎቹ ቋሚ መጠለያ ካምፕ ለመገንባት 56 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን የዞኑ አስተዳደር መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ፣ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የተመድ ሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ገልጧል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja