Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkun_zemede — Zemedkun Bekele (ዘመዴ) Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkun_zemede — Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
የሰርጥ አድራሻ: @zemedkun_zemede
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-18 18:30:16
ለማ መገርሳ ስለ አዲስ አበባ የተናገረው አስገራሚ ንግግር #ሼር

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
261 views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 08:05:25 ኦነግ ሸኔ ኦሮሚያን እንዳስተዳድር ስልጣን ይሰጠኝ ሲል ለፌድራሉ መንግስት ጥያቄ አቀረበ!

በዛንዚባር መንግሥትንና እና ኦነግ ሸኔን  ያላስማማው ጉዳይ የኦሮሚያ ክልልን እንድንመራ ይሰጠን በማለታቸው እንደሆነ ተገለፀ
የኤርትራ መንግስት በሁለት ተፃራሪ ጎራ በአማራ ክልል ውስጥ እጁን አስገብቶ የደም መፋሰሱን እያቀጣጠለ ነው ሲል ጌታቸው ረዳ ከሰሰ!
የጅማ አገር ስብከት ከእውቅናው ውጭ ለኹለተኛ ጊዜ የተመደቡትን ‹‹ጳጳስ›› ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገለጸ!

ሙሉውን መረጃ ላላያችሁ ከስር ባለው ሊንክ ተመልከቱ አዲስ አበባ የሚገኙ የEMS በረዳት ዜና አቅራቢዎቻችን የቀረቡ የሀገር ውስጥ ዜናዎች ናቸው፣ መረጃዎችን በፍጥነት ከሀገር ቤት ወደ እኛ በፍጥነት የሚያደርሱን ባልደረቦቻችን ናቸውና፣ ዜናውን በማየት አበረቷቷቸው።
ይህን ተጫኑ


290 views05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 07:48:01
ሼር
፨ለሁሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች
፨ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
፨ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች
ጉዳዩ፡ የአገር አቀፍ ፈተና ቀናትን ስለማሳወቅ
1) በ2014 የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ኘሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ፤ ተቋማት ፈተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 50 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 50 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደት እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ።

2) በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 13 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ።

3) የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ።

በመጨረሻም ከ2016 ጀምሮ የትምህርት ካላንደሩን ሁሉም ተቋማት ፕሮግራሞቻቸውን በዚህ ማዕቀፍ ያስተካክሉ ዘንድ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አሳስበዋል።
#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
272 views04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 07:22:42 ሐሙስ ማለዳ! ግንቦት 10/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ በትግራይ ክልል የሦስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ትናንት መቀሌ ገብተዋል። አምባሳደሩ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ጋር በሰላም ስምምነቱ አፈጻጸምና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ እንደተወያዩ የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። አምባሳደሩ ወደ ሽሬና አዲግራት ጭምር በጦርነቱ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን እንደሚጎበኙ ዘገባው አመልክቷል።

2፤ ገንዘብ ሚንስቴር በተያዘው በጀት ዓመት ከውጭ ምንጮች ለማግኘት የታቀደው 7 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍ እስካሁን እንዳልተገኘ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት መናገሩን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል። ሚንስትር አሕመድ ሽዴ በሪፖርታቸው፣ ከታክስ፣ ታክስ ነክ ካልኾኑና ከውጭ አጋሮች ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍ 446 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ሚንስትሩ፣ መንግሥት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የሰበሰበው ጠቅላላ ገቢ የዕቅዱን 63 ነጥብ 3 በመቶ ብቻ እንደኾነ ገልጸዋል ተብሏል።

3፤ በደቡብ ክልል ጋሞ እና ደቡብ ኦሞን ጨምሮ በተወሰኑ ዞኖች በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ሳቢያ 18 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማስታወቁን ቪኦኤ ዘግቧል። 919 የክልሉ ነዋሪዎች ደሞ በበሽታው መያዛቸውን ኢንስቲትዩቱ መናገሩን ዘገባው አመልክቷል። ጤና ሚንስቴር በበኩሉ፣ ወረርሽኙ በአራት ክልሎች እንደተከሰተ ገልጦ፣ ከአንድ ዓመት በላይ ለኾኑ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዜጎች በመላ አገሪቱ ክትባት ለመስጠት ማቀዱን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጧል። ሚንስቴሩ የክትባት ዘመቻውን ማክሰኞ'ለት በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በናጸማይ ወረዳ አስጀምሬያለኹ ብሏል።

4፤ የኢትዮጵያ፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳን የላፕሴት የጋራ ፕሮጀክት የሚንስትሮች ስብሰባ ትናንት ጁባ ውስጥ ተጀምሯል። ለሦስት ቀናት የሚቆየው የሚንስትሮች ስብሰባ መሪ ቃል፣ የላፕሴት የጋራ ፕሮጀክትን አፈጻጸም ማፋጠን" የሚል መኾኑን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ስብሰባው የላፕሴት ፕሮጀክቶችን ለማፋጠን የሚያስችል ሰነድ ያዘጋጃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚንስቴሩ ገልጧል። ኢትዮጵያ በስብሰባው እየተሳተፈች ያለችው፣ የገንዘብ ሚንስትር ደዔታ እዮብ ተካልኝ በመሩት ልዑካን ቡድን ነው።

5፤ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት አዛዥ ጀኔራል ደጋሎ ልዩ መልዕክተኛ የሱፍ እዛትን ተቀብለው እንዳነጋገሩ የፕሬዝዳንት ኪር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። ጀኔራል ደጋሎ፣ የተኩስ አቁም ስምምነቶችን ለማክበርና ግጭት ለማቆም ዝግጁ መኾናቸውንና የኢጋድ የሰላም ጥረትን እንደሚደግፉ ልዩ መልዕክተኛው ለፕሬዝዳንቱ እንደገለጡላቸው ተገልጧል። የሱዳን ጦር ሠራዊት አዛዥ ጀኔራል ቡርሃን ባለፈው ሳምንት ልዩ መልዕክተኛቸውን ወደ ፕሬዝዳንት ኪር ልከው ነበር።

6፤ የዩክሬን የእህል ምርት በጥቁር ባሕር በኩል ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ የሚያስችለው የዩክሬንና ሩሲያ ስምምነት ትናንት ምሽት ላይ ለሁለት ተጨማሪ ወራት መራዘሙን የውጭ ዜና ወኪሎች ዘግበዋል። ባለፈው መጋቢት ለሁለት ወራት ብቻ የተራዘመው ስምምነቱ ቀነ ገደቡ ዛሬ ያበቃ ነበር። የስምምነቱ መራዘም በተለይ ለአፍሪካ አገራት ትልቅ እፎይታ እንደኾነ ተገልጧል። ሩሲያ ለውጭ ገበያ በምታቀርበው ማዳበሪያና እህል ምርት ላይ የተጋረጡ ዓለማቀፍ መሰናክሎች ካልተወገዱ፣ ከስምምነቱ እንደምትወጣ ስታስጠነቅቅ መቆየቷ ይታወሳል። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
245 views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 17:35:33 ቪዲዮውን ተመልከቱ


257 views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 15:14:38
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የቤተ መንግሥት ግንባታ በአዲስ አበባ ሊጀመር ነው

በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኝ ከስድስት ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ፤ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ቤተ መንግሥት ሊገነባ ነው።

በግንባታው ማስጀመሪያ መርሃግብር በዛሬው ዕለት የተከናወነ ሲሆን፤ በመድረኩም የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያና የፌዴራል አመራሮች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የሲንቄ እናቶች ተገኝተውበታል።

የቤተ መንግሥቱ አጠቃላይ የግንባታ ሥራ በኹለት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ የተያዘ ሲሆን፤ ግንባታው ኹለት ምዕራፎች እንዳሉትም የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

የታቀደውን ቤተ መንግሥት ለመገንባት ከቻይናው ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (CCECC) ጋር የውል ስምምነት የፈጸመ ሲሆን፤ ኩባንያውን በተያዘለት ጊዜ ውስጥ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቋል።

ለቤተ መንግሥቱ ግንባታ የተመደበው ዋጋን አስመልክቶ እስከአሁን የተገለጸ ነገር የለም።

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                  
@emsmereja
272 views12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 21:36:02 አሳዛኝ ነው አረዷቸው

inbox
በጣም አሳዛኝ መረጃ
በሰበታ አካባቢ ዳለለቲ /ደረቶ/ሚባል ሰፈር ሰሞኑን ቤት እየፈረሰ ነበር። ትናንትም ሲያፈርሱ ውለዋል እና አፍራሾቹ ቤት የፈረሰባቸውን ሰዎች አካባቢውን ለቃችሁ ሂዱ እዚህ አትደሩ ብለዋቸው ሰዎቹ ደግሞ ለጊዜው መሄጃ ስለሌላቸው አልሄዱም ነበር። ከዚያ አፍራሾቹ ደበደቧቸው ከዚያም ሌሊት ተመልሰው አራቱን አርደዋቸው አደሩ ሁለቱ ባልና ሚስት ናቸው።
ዛሬ አስክሬናቸውን ወደ ትውልድ ቀያቸው ወደ ጉራጌ ሸኝተናል።
=====================
መልዕክቱን በቅንነት ለየግሩፓችሁና ለየቻናላችሁ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሼር አድርጉልን።
ቻናላችንንም Join አድርገው ይቀላቀሉን ።
                        @emsmereja
100 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 14:08:20
ገና ቁስላችን ሳይደርቅ በፋኖ ላይ ጦርነት ከፍተውብናል። ህዝባችን ከውድመቱ ሳያገግም ሌላ ውድመት ታውጆበታል። አማራ በህብረት ቆሞ፣ ለውጥ ማምጣት አለበት። ፋኖን መደገፍ አለበት።

የአማራ ህዝብ ሕግ ያለ እንዳይመስለው። ህግ የለም። እኔ በግሌ ለመሞት ነው የተነሳሁት። የሚያሳፍረው ግን የ3 አመት ልጄ ሳይቀር ታፍኗል። ይሄ የሚያሳየው በኦነጎች ዘንድ ህግም፣ ሞራልም አለመኖሩን ነው። አማራ የሚያስከብረው ኃይሉ ብቻ ነው። የሚያዋጣው መደራጀቱ ብቻ ነው።

አሁን ላይ ኢትዮጵያን የሚወደው ትክክለኛው የመከላከያ ሰራዊት የለም። አብዛኛው ሰራዊት ጥቅምት 24 በህወሃት ተረሽኗል። የቀረው ባለፉት ሁለት አመታት አልቋል። የተወሰኑ የተረፉ ቢኖሩም ወደ አማራ ህዝብ አንተኩስም በማለታቸው እየተረሸኑ ነው።

አሁን የመከላከያን ዩኒፎርም ለብሶ ወረራ የከፈተብን በብሔር ጥላቻ ያበደው የኦሮሞ ልዩ ኃይል ነው።

ሌላው ጠላት ይበቃናል። ስለዚህ የአማራን አመራር አንገድልም። የአማራን አመራር መግደል ብንፈልግ፣ በህወሃት ወረራ ጊዜ ህዝቡን ለጅብ ሰጥተው ቀድመው የፈረጠጡ አመራሮችን ነበር የምንገድላቸው። መግደል ብንፈልግ ኖሮ በክፉ ቀን የፈረጠጡት አመራሮች፣ ተመልሰው ስልጣን ሲይዙ ነበር የምንገድላቸው።

እንደ ፋኖ አስተሳሰብ ገዳዩም አማራ፣ ሟቹም አማራ እንዲሆን አንፈልግም። ይሄ የእስካሁን መርሃችን ነው። የአማራ አመራሮችም ከስህተታቸው ይወጣሉ በሚል እየጠበቅናቸው ነው። ነገር ግን የአማራ አመራሮች ዝምታችንን ካለመቻል ቆጥረው ዛሬም እንደ ትናንቱ እየተላላክን፣ ፋኖን እያሳደድን፣ የህዝብ ጥያቄ እያፈንን እንቀጥላለን ካሉ መርሃችንን ልንቀይር እንችላለን።
(ፋኖ ምሬ ወዳጆ - ከአበበ በለው ጋር ካደረገው የስልክ ቃለምልልስ ላይ የተወሰደ)
#ሼር በማድረግ ተባበሩን

የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ   
@emsmereja
183 views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 11:53:26
ትምህርት ሚኒስቴር መጋቢት/2015 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚያገለግል መመሪያና ደንብ አውጥቷል
1. አንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር ተመሳሳይ አካዳሚክ ደረጃ ላይ መቆየት የሚችለው 8 ዓመት ብቻ ነው፤ለምሳሌ ማስተርስ ያለው መምህር 8 ዓመት ከመሙላቱ በፊት ፒኤችዲ መማር አለበት ማለት ነው፤እንግዲህ ማስተርስ ይዘህ ወዴ አሲስታት ፕሮፌሰር ማዕረግ ያላደክ ወይም ፒኤችዲ ያልያዝክ መምህር ካለህ ስምንት አመት ሳይሞህ የፒኤችዲ ትምህርትህን ጀምር አለበለዚያ
2. አንድ የማስተርስ ተማሪ ትምህርቱን በሁለት አመት ማጠናቀቅ አለበት፣በተለያዩ አሳማኝ ምክንያቶች እስከ አራት አመት ሊቆይ ይችላል።
3. አንድ የፒኤችዲ ተማሪ ትምህርቱን በአራት አመት ማጠናቀቅ አለበት፤በተለያዩ አሳማኝ ምክንያቶች እስከ ስድስት አመት ብቻ መቆየት ይችላል፤በተለያዩ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የፒኤችዲ ትምህርት ጀምረው 7 ዓመት፣8 ዓመት፣9 ዓመትና 10 ዓመት የሞላቸው ተማሪዎች ሞልተዋል።
የእኛ ጥያቄ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ለአንድ ሶስተኛ ድግሪ (PhD) ተማሪ የሚያስፈጉ መሰረታዊ ግብአቶች (ጥራታቸው የጠበቁ ዶርሚተሪዎች፣በቂ የምርምር ገንዘብና ጥቅማ ጥቅም፣ስማርት የመማሪያ ክፍሎች፣በደንብ የተደራጁ ላቦራቶሪዎች፣ቅንና ታታሪ አድቫይዘሮች ወዘተ) አላቸው ወይ?
=============
ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሼር አድርጉላቸው ። ቻናላችንንም Join አድርገው ይቀላቀሉን ።
                        @emsmereja
190 views08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 07:33:19 የሕይወት አዙሪት!

ሕይወት አዙሪት ናት ፡፡ ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም ነገር ግን የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው ፡፡ ልብ በል! ራቁትክን ትወለዳለህ ፤ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ ፡፡ በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ ፤ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ ። የሕይወትን ትግል እየዳህ ትጀምራለህ ፤ አጎንብሰህ ትጨርሳለህ ፡፡

ዘመንም ተምኔታዊ ነው ፡፡ መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሃል ፤ ሠኞ ማክሠኞ ብለህ ተጉዘህ ፤ እንደገና ሠኞ ትላለህ ፡፡ እናም ሕይወት አዙሪት ናት !

መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው ፡፡ የጀመርክበትን አትርሳ ፤ መጨረሻህ ነውና ፡፡ የጀመርክበትን አትናቀው ፤ ትጨርስበታለህና ፡፡ ተራ ሠው ሆነህ ትጀምራለህ ፤ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምርም ፤ ነግደህ ሃብት ብታገኝ ፤ ተሹመህ በሕዝብ ላይ ብትሠለጥን ፤ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ ፤ የምትጨርሠው እንደተራ ሠው አፈር ለብሠህ ነው ፡፡

ልብ በል! ባለማወቅ ትጀምራለህ ፤ በመዘንጋት ትጨርሳህ ፡፡ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሄድም ፡፡ በለቅሶ ትጀምራለህ ፤ በጭንቅ ትጨርሳለህ ፡፡ በሠው እቅፍ ትጀምራለህ ፤ በሠው ሸክም ትጨርሳለህ ፡፡ ልደትህ ከሞትህ በምን ይለያል ? ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል ? ሕይወት መጀመሪያዋና መጨረሻዋ አንድ ነው ፡፡ በዚህ የተነሣ ጠቢቡ እንዳለው ሁሉም የከንቱ ከንቱ ነው ፡፡ ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም ፡፡

ልብ በል! የዓለም #ከንቱነት ግን ውበትዋ ነው ፡፡ ዓለም አዲስ ነገር ቢኖራት እኛን እንዴት በፀፀተን ፤ ሞት የእውነት መጨረሻ ቢሆን እንዴት በቆጨን!! ‹‹ርቀህ የሄድክ ቢመስልህም ፤ ትልቅ ክብ ሰርተህ ተመልሰህ እዚህ ትመጣለህ ፡፡ ዋናውን ተግባርክን ግን እስካሁን አልጀመርከውም ፡፡››

"ጨለማን መተቸት ብርሃን አያመጣም ክፋትን መኮነንም ደግነት አይሆንም ኋላቀርነትን ማጥላላት ሥልጣኔ አያመጣም ጦርነትን መፍራትም ሠላም አይሆንም እንዲሁም ረሃብን አለመፈለግ ጥጋብ አያመጣም ። ዕውቀትና በጎ አመለካክት ግን ማህበረሰብን መቀየር ይችላሉ ።

ቴሌግራምን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም ። ማወቅ መልካም ነው ያውቁትን ማሳውቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ። በምድረ ላይ የምናደርጋቸው መልካም ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነዉ ይከፈሉናል ። ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ ።
መልካምነት ለራሱ ነው ።

ስለዚህ አንተም ይህ አሁን ያነበብከውን መጣጥፍ ትምህረት ሰጪ ሆኖ ካገኘኸው እርሰዎ ዘመዶችህ እንዲያነቡትና ትምህርት እንዲወስዱ ዘንድ በቅንነት ለየግሩፓችሁና ለየቻናላችሁ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሼር አድርጉላቸው ። ቻናላችንንም Join አድርገው ይቀላቀሉን ።
    @emsmereja
184 views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ