Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር መጋቢት/2015 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚያገለግል መመሪያና ደንብ አውጥቷ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ትምህርት ሚኒስቴር መጋቢት/2015 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚያገለግል መመሪያና ደንብ አውጥቷል
1. አንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር ተመሳሳይ አካዳሚክ ደረጃ ላይ መቆየት የሚችለው 8 ዓመት ብቻ ነው፤ለምሳሌ ማስተርስ ያለው መምህር 8 ዓመት ከመሙላቱ በፊት ፒኤችዲ መማር አለበት ማለት ነው፤እንግዲህ ማስተርስ ይዘህ ወዴ አሲስታት ፕሮፌሰር ማዕረግ ያላደክ ወይም ፒኤችዲ ያልያዝክ መምህር ካለህ ስምንት አመት ሳይሞህ የፒኤችዲ ትምህርትህን ጀምር አለበለዚያ
2. አንድ የማስተርስ ተማሪ ትምህርቱን በሁለት አመት ማጠናቀቅ አለበት፣በተለያዩ አሳማኝ ምክንያቶች እስከ አራት አመት ሊቆይ ይችላል።
3. አንድ የፒኤችዲ ተማሪ ትምህርቱን በአራት አመት ማጠናቀቅ አለበት፤በተለያዩ አሳማኝ ምክንያቶች እስከ ስድስት አመት ብቻ መቆየት ይችላል፤በተለያዩ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የፒኤችዲ ትምህርት ጀምረው 7 ዓመት፣8 ዓመት፣9 ዓመትና 10 ዓመት የሞላቸው ተማሪዎች ሞልተዋል።
የእኛ ጥያቄ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ለአንድ ሶስተኛ ድግሪ (PhD) ተማሪ የሚያስፈጉ መሰረታዊ ግብአቶች (ጥራታቸው የጠበቁ ዶርሚተሪዎች፣በቂ የምርምር ገንዘብና ጥቅማ ጥቅም፣ስማርት የመማሪያ ክፍሎች፣በደንብ የተደራጁ ላቦራቶሪዎች፣ቅንና ታታሪ አድቫይዘሮች ወዘተ) አላቸው ወይ?
=============
ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሼር አድርጉላቸው ። ቻናላችንንም Join አድርገው ይቀላቀሉን ።
                        @emsmereja