Get Mystery Box with random crypto!

ገና ቁስላችን ሳይደርቅ በፋኖ ላይ ጦርነት ከፍተውብናል። ህዝባችን ከውድመቱ ሳያገግም ሌላ ውድመት | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ገና ቁስላችን ሳይደርቅ በፋኖ ላይ ጦርነት ከፍተውብናል። ህዝባችን ከውድመቱ ሳያገግም ሌላ ውድመት ታውጆበታል። አማራ በህብረት ቆሞ፣ ለውጥ ማምጣት አለበት። ፋኖን መደገፍ አለበት።

የአማራ ህዝብ ሕግ ያለ እንዳይመስለው። ህግ የለም። እኔ በግሌ ለመሞት ነው የተነሳሁት። የሚያሳፍረው ግን የ3 አመት ልጄ ሳይቀር ታፍኗል። ይሄ የሚያሳየው በኦነጎች ዘንድ ህግም፣ ሞራልም አለመኖሩን ነው። አማራ የሚያስከብረው ኃይሉ ብቻ ነው። የሚያዋጣው መደራጀቱ ብቻ ነው።

አሁን ላይ ኢትዮጵያን የሚወደው ትክክለኛው የመከላከያ ሰራዊት የለም። አብዛኛው ሰራዊት ጥቅምት 24 በህወሃት ተረሽኗል። የቀረው ባለፉት ሁለት አመታት አልቋል። የተወሰኑ የተረፉ ቢኖሩም ወደ አማራ ህዝብ አንተኩስም በማለታቸው እየተረሸኑ ነው።

አሁን የመከላከያን ዩኒፎርም ለብሶ ወረራ የከፈተብን በብሔር ጥላቻ ያበደው የኦሮሞ ልዩ ኃይል ነው።

ሌላው ጠላት ይበቃናል። ስለዚህ የአማራን አመራር አንገድልም። የአማራን አመራር መግደል ብንፈልግ፣ በህወሃት ወረራ ጊዜ ህዝቡን ለጅብ ሰጥተው ቀድመው የፈረጠጡ አመራሮችን ነበር የምንገድላቸው። መግደል ብንፈልግ ኖሮ በክፉ ቀን የፈረጠጡት አመራሮች፣ ተመልሰው ስልጣን ሲይዙ ነበር የምንገድላቸው።

እንደ ፋኖ አስተሳሰብ ገዳዩም አማራ፣ ሟቹም አማራ እንዲሆን አንፈልግም። ይሄ የእስካሁን መርሃችን ነው። የአማራ አመራሮችም ከስህተታቸው ይወጣሉ በሚል እየጠበቅናቸው ነው። ነገር ግን የአማራ አመራሮች ዝምታችንን ካለመቻል ቆጥረው ዛሬም እንደ ትናንቱ እየተላላክን፣ ፋኖን እያሳደድን፣ የህዝብ ጥያቄ እያፈንን እንቀጥላለን ካሉ መርሃችንን ልንቀይር እንችላለን።
(ፋኖ ምሬ ወዳጆ - ከአበበ በለው ጋር ካደረገው የስልክ ቃለምልልስ ላይ የተወሰደ)
#ሼር በማድረግ ተባበሩን

የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ   
@emsmereja