Get Mystery Box with random crypto!

የሕይወት አዙሪት! ሕይወት አዙሪት ናት ፡፡ ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም ነገር ግን የ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሕይወት አዙሪት!

ሕይወት አዙሪት ናት ፡፡ ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም ነገር ግን የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው ፡፡ ልብ በል! ራቁትክን ትወለዳለህ ፤ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ ፡፡ በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ ፤ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ ። የሕይወትን ትግል እየዳህ ትጀምራለህ ፤ አጎንብሰህ ትጨርሳለህ ፡፡

ዘመንም ተምኔታዊ ነው ፡፡ መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሃል ፤ ሠኞ ማክሠኞ ብለህ ተጉዘህ ፤ እንደገና ሠኞ ትላለህ ፡፡ እናም ሕይወት አዙሪት ናት !

መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው ፡፡ የጀመርክበትን አትርሳ ፤ መጨረሻህ ነውና ፡፡ የጀመርክበትን አትናቀው ፤ ትጨርስበታለህና ፡፡ ተራ ሠው ሆነህ ትጀምራለህ ፤ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምርም ፤ ነግደህ ሃብት ብታገኝ ፤ ተሹመህ በሕዝብ ላይ ብትሠለጥን ፤ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ ፤ የምትጨርሠው እንደተራ ሠው አፈር ለብሠህ ነው ፡፡

ልብ በል! ባለማወቅ ትጀምራለህ ፤ በመዘንጋት ትጨርሳህ ፡፡ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሄድም ፡፡ በለቅሶ ትጀምራለህ ፤ በጭንቅ ትጨርሳለህ ፡፡ በሠው እቅፍ ትጀምራለህ ፤ በሠው ሸክም ትጨርሳለህ ፡፡ ልደትህ ከሞትህ በምን ይለያል ? ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል ? ሕይወት መጀመሪያዋና መጨረሻዋ አንድ ነው ፡፡ በዚህ የተነሣ ጠቢቡ እንዳለው ሁሉም የከንቱ ከንቱ ነው ፡፡ ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም ፡፡

ልብ በል! የዓለም #ከንቱነት ግን ውበትዋ ነው ፡፡ ዓለም አዲስ ነገር ቢኖራት እኛን እንዴት በፀፀተን ፤ ሞት የእውነት መጨረሻ ቢሆን እንዴት በቆጨን!! ‹‹ርቀህ የሄድክ ቢመስልህም ፤ ትልቅ ክብ ሰርተህ ተመልሰህ እዚህ ትመጣለህ ፡፡ ዋናውን ተግባርክን ግን እስካሁን አልጀመርከውም ፡፡››

"ጨለማን መተቸት ብርሃን አያመጣም ክፋትን መኮነንም ደግነት አይሆንም ኋላቀርነትን ማጥላላት ሥልጣኔ አያመጣም ጦርነትን መፍራትም ሠላም አይሆንም እንዲሁም ረሃብን አለመፈለግ ጥጋብ አያመጣም ። ዕውቀትና በጎ አመለካክት ግን ማህበረሰብን መቀየር ይችላሉ ።

ቴሌግራምን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም ። ማወቅ መልካም ነው ያውቁትን ማሳውቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ። በምድረ ላይ የምናደርጋቸው መልካም ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነዉ ይከፈሉናል ። ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ ።
መልካምነት ለራሱ ነው ።

ስለዚህ አንተም ይህ አሁን ያነበብከውን መጣጥፍ ትምህረት ሰጪ ሆኖ ካገኘኸው እርሰዎ ዘመዶችህ እንዲያነቡትና ትምህርት እንዲወስዱ ዘንድ በቅንነት ለየግሩፓችሁና ለየቻናላችሁ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሼር አድርጉላቸው ። ቻናላችንንም Join አድርገው ይቀላቀሉን ።
    @emsmereja