Get Mystery Box with random crypto!

' የእኔን ወላጆች ጨምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች አሉን መመለስ መቻል አለባቸው ' - አቶ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

" የእኔን ወላጆች ጨምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች አሉን መመለስ መቻል አለባቸው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ዛሬ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ " ጦርነት ይብቃ፣ ሰላምን እናፅና " በሚል መሪ ቃል የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት በሰላም እና በንግግር እንዲቋጭ ላደረጉ አካላት የምስጋና መርሀ ግብር ተካሂዶ ነበር።

በዚህ ስነስርት ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት፣ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ አምባሳደር ማይክ ሀመር እና ሌሎችም በርካታ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተው ነበር።

በዚሁ መድረክ ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ንግግር አድርገው ነበር።

በንግግራቸው ምን አሉ ?

አቶ ጌታቸው ረዳ ፦

" የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል። ጠብመንጃ የመነቅነቅ አባዜ በፍፁም አይኖረም በዚህ አጋጣሚ ከትግራይ ይዤ የመጣሁት መልዕክት የሰላም እና የፍቅር መልዕክት ብቻ ነው።

አሁንም አራት ዓመት በላይ ትምህርት የሚባል ያላየሁ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ልጆች አሉን ትምህርት ቤት መግባት መቻል አለባቸው።

አሁንም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች አሉን የኔን ወላጆች ጨምሮ መመለስ መቻል አለባቸው ፣ ስራቸውን መስራት መቻል አለባቸው።

ሁሉንም ነገር ለሰላም በሚሆን መልኩ እናድርገው ፣ ከጎረቤት ወንድም ህዝቦች በተለይም ከአማራ እና ከአፋር ጋር ሊያጋጨን የሚገባ ነገር ሳይኖር ፣ ግጭት ተፈጥሮ በሁላችንም ዘንድ ታሪክ ይቅል ሊለው የማይገባ ብዙ ጥፋት ተፈፅሟል።

ይሄንን ነገር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ዘግተን ቋንቋችንን የሰላም እና የመከባበር፣ ልዩነቶቻችንን በመከባበር ፣ በመቻቻል እና በህግ ብቻ ለመፍታት እስከሰራን ድረስ በጋራ ሀገራችንን ከመገንባት አልፈን ፣ በሁለቱም በሶስቱም ጎረቤት እህትማማች፣ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ተጥሮ ያለውን መቃቃይ የሚመስል ስሜት አስወግደን ወደ ተሻለ ደረጃ የማናሳድግበት ምክንያት የለም።

... አሁንም ደግሜ ደጋግሜ የምለው የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል ፤ አንገሽግሾታል ይህ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አካባቢዎች እንደ ኖርማል የሚወሰዱ ህፃናትን ትምህርት ቤት በሰዓቱ መላክ መመለስ የሚመስሉ ጉዳዮች፣ ማረስ፣ ማለስለስ፣ ማጨድ መዝራት የሚባሉ ነገሮች ይናፍቁታል ፈጥነን ወደዚህ መመለስ መቻል አለብን።

ሁሉንም ለማድረግ የሁሉንም አቅም መጠቀም ያስፈልገናል። ከምንም ነገር በላይ ጠንካራ ሰራተኛ የሆነው የትግራይ ህዝብ ተመልሶ ወደ ስራው ተሰማርቶ የሰላም ችግር ሳይሆን ምን ያክል አተረፍኩ ምን ያክል አመረትኩ በሚል ፉክክር ውስጥ እንዲገባ ለማስቻል የጀመርነውን ጥረት አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል፤ ሁሉም ክልሎች የዚህ እንቅስቃሴ አካል እንደሚሆኑ እምነቴ የፀና ነው ፤ ከፌዴራል መንግሥት ጋር የጀመርናቸው መልካም ግንኙነቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ አውንታዊ በሆነ መልኩ ትልቅ ደረጃ ላይ እንደሚደርሱ እምነታችን የፀና ነው። "

#ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

                                   @emsmereja