Get Mystery Box with random crypto!

Addis Ababa Education Bureau

የሰርጥ አድራሻ: @wwwaddisababaeducationbureau
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 106.22K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2024-03-15 21:24:45
አፍረካን ሊደርሺፕ ሜጋዚን ከንቲባ አዳነች አቤቤን የአፍሪካ ምርጥ ሴት መሪ በሚል ሸለመ፤


(ቀን መጋቢት 6/2016 ዓ.ም) አፍረካን ሊደርሺፕ ሜጋዚን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤን የአፍሪካ ምርጥ ሴት መሪ በሚል ሽልማት አበረከተላቸዉ።


መቀመጫዉን በእንግሊዝ ያደረገዉ እና በየአመቱ በአፍሪካ ምርጥ ብቃት ያሳዩ አፍሪካዉያን መሪዎችን የሚሸልመዉ የአፍሪካን ሊደርሺፕ ኦርጋናይዜሽን የፈረንጆቹን 2024 የሽልማት ስነስርቱን በአዲስ አበባ አከናዉኗል።


በስካይ ላይት ሆቴል የተከናወነዉ የሽልማት ስነስርአት በኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ ሰዉ በሚል ሲካሄድ የመጀመሪያዉ ነዉ።


የአፍረካን ሊደርሺፕ ኦርጋናይዜሽን አካል የሆነዉ አፍሪካን ሊደርሺፕ መጋዚን የአመቱን ምርጥ ሰዉና መሪ በላቀ የአመራር ብቃት የሚሸልም ሲሆን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤም ሽልማቱን የአፍሪካ ምርጥ ሴት አመራር በሚል ተሸልመዋል።


ሽልማቱን የተቀበሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሽልማቱ ስለተበረከተላቸዉ አመስግነዋል።


“የማይበገር የአፍረካን ኢኮኖሚ መገንባት” በሚል መሪቃል የተካሄደዉ የሽልማት ስነስርአቱ ከ25 በላይ የሚሆኑ እና በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ አፍረካዉያን መሪዎች የተገኙበት ነዉ።


የማይበገር ኢኮኖሚን መገንባት ችለዋል የተባሉት እና በአመራራቸዉ ዘላቂ የሆነ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማስመዘገብ የላቀ ሚና ያላቸዉ አመራሮች የተሸለሙበትም ስነስርአት ነዉ።
18.9K viewsAbebe Chernet, edited  18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-15 18:24:56
ለመምህራን የተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የማውጣት መርሀ ግብር በፎቶ


(ቀን መጋቢት 6/2016 ዓ.ም) ዕጣ የደረሳቸው መምህራን ደስታቸውን ሲገልጹ


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
21.0K viewsAbebe Chernet, 15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-15 18:05:28 ዶክተር ዘላለም አክለውም ቢሮው በየደረጃው ከሚገኙ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር አመራሮች እና አባላት እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ባከናወናቸው የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ውል ያልተፈጸመባቸውን 435 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በመለየት ለዛሬው የዕጣ ማውጣት መርሀ ግብር ማብቃቱን ጠቁመው በዕጣው መካተት ያልቻሉ መምህራን በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ህንጻ በመገንባት የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩንም አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አ ስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የዕጣ ማውጣት መርሀግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አስተዳደሩ የመምህራንን ጨምሮ ቤት ፈላጊ የሆኑ የከተማውን ነዋሪዎች ጥያቄ ለመመለስ በተለያዩ አማራጮች ቤት በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው መምህራንም በቅርቡ በማህበር ተደራጅተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የቀረበላቸውን እድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቅአለም ቶሎሳ ከተማ አስተዳደሩ የመምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ እያደረገ ለሚገኘው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው በዛሬው ዕጣ እድለኛ መሆን ያልቻሉ መምህራን የቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ በማህበር ተደራጅተው የቤት ባለቤት መሆን እንደሚገባቸው አስረድተዋል።




መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
19.3K viewsAbebe Chernet, 15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-15 18:05:17
ለመምህራን ተላልፈው በተለያዩ ምክንያቶች ውል ያልተፈጸመባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የማውጣት መርሀ ግብር ተካሄደ።

(ቀን መጋቢት 6/2016 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቅአለም ቶሎሳ እንዲሁም የካቢኔአባላት፣በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች እና መምህራን የተገኙ ሲሆን በ2009 ዓ.ም ለመምህራን ከተላለፉ 5000 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች ውል ሳይፈጸምባቸው የቆዩ 435 ቤቶች በዛሬው እለት ፍትሀዊ በሆነ የዕጣ ማውጣት ስነስርአት ለቤት ፈላጊ መምህራን ተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ መርሀ ግብሩ እንዳስታወቁት ከተማ አስተዳደሩ የመምህርነት ሙያ ለትምህርት ልማት ስራው ውጤታማነት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት ለመምህራን የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ከነዚህ ድጋፎች መካከልም የትምህርት ዕድል በመስጠት፣የቤት ኪራይ አበል ቀደም ሲል ከነበረው ከፍ እንዲል መደረጉ፣ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ እንዲሁም በ2009 ዓ.ም በኪራይ የተላለፈላቸውን የጋራ መኖሪያ ቤት በወቅቱ ዋጋ ወደ ግል እንዲያዘዋውሩ መደረጉ ከብዙ ድጋፎች መካከል ጥቂቶቹ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
20.0K viewsAbebe Chernet, 15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-06 12:07:26 የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸው መምህራን በህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ላደረጉት አስተዋፅዎና የከተማ አስተዳደሩ ለመምህራን ቅድሚያ በመስጠቱ ምስጋና አቅርበው መምህራኖችም የቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ የቤት ባለቤት የሚያደርጋቸውን ዕድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።



በመርሀግብሩ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና ከህብረት ስራ ኮሚሽን መምህራኑ በህብረት ስራ ማህበራቱ ለመደራጀት መከተል ስለሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና እስካሁን የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን በተመለከተ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ለተነሱ ጥያቆዎች የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዲሳ አራርሳ፣ የህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሉሊት ግደይ እንዲሁም በመምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ድንቃለም ቶሎሳ እና በዶክተር ዘላለም ሙላቱ ምላሽ ተሰቷል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
14.7K viewsAbebe Chernet, 09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-06 12:07:23
ቤት ፈላጊ መምህራን በህብረት ስራ ማህበራት በመደራጀት የጋራ መኖሪያ ህንጻ ገንብተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁ ተገለጸ።

(ቀን የካቲት 27/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከከተማው መምህራን ማህበር ጋር በጋራ በመሆን በጉዳዩ ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ያካሄደ ሲሆን በውይይቱ የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን ጨምሮ ርዕሳነ መምህራን ፣ ከየትምህርት ቤቱ የመጡ የመሰረታዊ መምህራን ማህበር ሰብሳቢዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኮሚሽን አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አስተዳደሩ መምህራን የቤት ባለቤት ሆነው ከተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ተላቀው ትውልድ የመገንባት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲከናወኑ መቆየቱን ገልጸው ትምህርት ቢሮ ቤት ፈላጊ መምህራን በህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ህንጻ ገንብተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ከመምህራን ማህበር እንዲሁም ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና ከህብረት ስራ ኮሚሽን ጋር ሲያከናውን የቆየው ቅድመ ዝግጅት በመጠናቀቁ ከነገ ጀምሮ ወደ ተግባር እንደሚገባም አስታውቀዋል።
15.1K viewsAbebe Chernet, 09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-29 21:51:38 የአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የስርዓተ ትምህርት ፣መረጃና የትምህርት ቴክኖሎጂ ስራዎች አስተባባሪ አቶ ሞሲሳ ኃይሌ በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት በክፍለከተማው በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ1ኛ መንፈቀ ዓመት ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት የትምህርት ልማት ስራው አበረታች ውጤት ማስመዝገቡን ገልጸው በቀጣይ ወራት  በክፍለከተማው የተማሪዎችን ውጤት እና ስነ ስነ-ምግባር ለማሻሻል የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት፣በትምህርት ቤቶች ውስጥ የከተማ ግብርና ፣ ሰላማዊ መማር ማስተማርን ማረጋገጥ፣የትምህርት ለትውልድ  ንቅናቄ እና ሌሎች ስራዎች የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ማስገንዘባቸውን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com    
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
13.8K viewsAbebe Chernet, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-29 21:51:21
የአዲስ ከተማ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት የ1ኛ መንፈቀ ዓመት ስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።


(ቀን የካቲት 21/2016 ዓ.ም) በመድረኩ የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት የ2016 ዓ.ም የ1ኛ ሴምስተር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የተማሪዎች ውጤት ትንተና እና የቀጣይ ትኩረት መስኮች ቀርበው ውይይት ተካሂዷል ።


በጽህፈት ቤቱ የመምህራን የሱፐርቪዥን እና የትምህርትቤት መሻሻል የስራዎች አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ቱጂ በመድረኩ በ2016 በ1ኛ መንፈቀ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በዚህም በ11ግቦች ስር የተከናወኑ የተለያዩ ተግራትን እና በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን አቅርበው ውይይት ተካሂዱዋል፡፡


የስርዓተ ትምህርት ክትትልና ትግበራ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ቤኩማ ደበሎ በበኩላቸው የተማሪዎችን ውጤት ትንተና በማቅረብ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡
13.2K viewsAbebe Chernet, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-10 16:12:28 ስልጠናውን 1200 የሚሆኑ ዋና እና ምክትል ርዕሳነ መምህራን መውሰዳቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል ጠቁመው ቢሮው በቀጣይ የአመራሮቹን አቅም የማሳደግ ተግባሩን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።

በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ የስልጠናው ተሳታፊዎች ስልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው በማጠናቀቃቸው የዕውቅና የምስክር ወረቀት በክብር እንግዶች ተበርክቶላቸዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!


What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
14.1K viewsAbebe Chernet, 13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-10 16:12:21
በከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ በተካሄደው የትምህርት ቤት አመራሮች ውድድር አልፈው ለተመደቡ ርዕሳነ መምህራን ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።

(ቀን የካቲት 2/2016 ዓ.ም) ስልጠናውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ለተከታታይ ስድስት ቀናት እንዲሰጥ በማድረግ በዛሬው እለት ተጠናቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በስልጠናው ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርም ሆነ ስልጠናውን የሰጡ ምሁራን የትምህርት አመራሮቹ በየተመደቡባቸው ተቋማት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ግንዛቤ በመፍጠራቸው ምስጋና አቅርበው ርዕሳነ መምህራኑም በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀትም ሆነ ክህሎት መሰረት በማድረግ የተቋማቸውን ደረጃ ማሳደግና የተማሪዎቻቸውን ውጤትና ስነ-ምግባር ማሻሻል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒ ቨርሲቲ ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር አብዱላዚዝ መሀመድ በበኩላቸው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ሴክተሩን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም ለትምህርት አመራሮችም ሆነ መምህራን ስልጠናዎችን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ አስረድተዋል።
13.5K viewsAbebe Chernet, 13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ