Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን ለታላቁ ለኢድ ዓል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ ! ኢድ ሙባረክ ! (ቀን ሚያዚያ 1/ | Addis Ababa Education Bureau

እንኳን ለታላቁ ለኢድ ዓል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ !

ኢድ ሙባረክ !

(ቀን ሚያዚያ 1/ 2016 ዓ.ም) ለ1445ኛውን ዓመት የኢድ ዓል ፈጥር በዓልን ስናከብር በጾሙ ወር ስናከናውናቸው የነበሩትን የመረዳዳት ፣ የመተጋገዝና አብሮ የመቋደስ ልምዳችንን ይበልጥ በማጎልበት ሊሆን ይገባል፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን በትምህርት ልማት ስራዉ ላይ ተገቢዉን ትኩረትና ርብርብ በማድረግ ነገ እንሰራዋለን ለማይባለው ትውልድ የመገንባት ስራ ጊዜ ሳንሰጥ ከፊት በመቆምና በመታገል ለውጤታማነቱ በጋራ በመስራት መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህንን ስናደርግ ለልጀቻችንና ለሀገራችን መበልጸግ የሚናችንን መወጣት እንችላለን፡፡


ሀገር የመገንባት ስራ ትውልድ መገንባት ላይ በምናደርገው ርብርብ ይወሰናል፡፡ ለዛም ነው የትምህርት ዘርፍ ስራ በአንድ ወገን ጥረት ብቻ ሊሳካ የማይችለው፡፡ የሁላችንም ተሰናስሎ መስራት በትምህርት ተደራሽነት ፣ ፍትሀዊነት ፣ ጥራት እና ተገቢነት ላይ የሚኖረው ሚና ቀላል ባለመሆኑ ከምንጊዜው በላይ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት እንደድንሰራ አደራ ለማለት እወዳለሁ፡፡


የኢድ ዓል ፈጥር በዓል የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የጤና እና የመረዳዳት እንዲሆን እመኛለሁ።

አመሰግናለሁ!

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ