Get Mystery Box with random crypto!

Addis Ababa Education Bureau

የሰርጥ አድራሻ: @wwwaddisababaeducationbureau
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 106.22K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2024-01-23 16:33:29 በበጀት አመቱ ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በሁለቱም ዘርፎች በዳይሬክቶሬቱ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት በቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐር ቪዥን ቡድን መሪ ትግስት ድንቁ አቅርበው ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን የቢሮው አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ዳይሬክተሩ አቶ ጸጋዬ አሰፋ እንዲሁም የአፋን ኦሮሞ አጠቃላይ ትምህርት ሱፐር ቪዥን ቡድን መሪ አቶ ተሾመ ቀናሳ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰተዋል፡፡

መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
12.8K viewsAbebe Chernet, 13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-23 16:33:11
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት በ2016 ዓ.ም 6 ወራት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን ገመገመ፡፡

(ቀን ጥር 14/2016 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የቢሮውን ጨምሮ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ክላስተር ሱፐር ቫይዘሮችና የክፍለ ከተማ የዘርፉ አስተባባሪዎች የተሳተፉ ሲሆኑ በዳይሬክቶሬቱና በተመረጡ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ክላስተር ማዕከላት በ6 ወራት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በሱፐርቪዥን ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ስርአተ ትምህርቱ በአግባቡ ተግባራዊ መሆኑንም ሆነ ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርትቤት ድረስ በትምህርት ዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው በዛሬው ውይይት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን በአግባቡ በመገምገም በ2ኛ መንፈቅ አመት የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ አሰፋ በበኩላቸው የዛሬው መርሀ-ግብር በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ዘርፎች ከቢሮ ጀምሮ በሁሉም ክላስተሮች በ6ወራት ውስጥ የተከናወኑ የሱፐር ቪዥን ተግባራትን በመገምገም በሂደት የታዩ ጠንካራና ደካማ አፈጻጸሞችን መሰረት በማድረግ በቀጣዩ የትግበራ ምዕራፍ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመው በውይይቱ በዳይሬክቶሬቱ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ከመቅረቡ ባሻገር በክፍል ውስጥ የተደረገ ሱፐርቪዥን ሪፖርት ቀርቦ ውይይት መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡
12.7K viewsAbebe Chernet, 13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-22 13:04:44
እናመሰግናለን!

(ቀን ጥር 13/2016 ዓ.ም) የቤቴልሔም 2ኛ ደረጃና የሳፋሪ አካዳሚ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ደም ለግሰዋል፡፡

ማህበራዊ ሀላፊነታችሁን የሰዉ ህይወት በማትረፍ ስለተወጣችሁ እናመሰግናለን!

መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
16.7K viewsAbebe Chernet, 10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-22 10:52:12 መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
15.3K viewsAbebe Chernet, 07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-22 10:51:50
ለውጤታማ ስራ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

(ቀን ጥር 13/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተነቃቃ የስራ አካባቢ እንዲኖርና በሚኖረው የልምድ ልውውጥ የተቀራረበ አስተሳሰብና የስራ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ለማድረግ እንዲያግዝ ሰኞ ሰኞ ከስራ ሰሃት መግቢያ በፊት ሰራተኞች በጋር እንዲገናኙ በሚያዘጋጀዉ የሰኞ ማለዳ የመአድ መቋደስ መርሃ ግብር ላይ የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት በመገኘት ከቢሮ ሰራተኞች ጋር መዓድ ተካፍለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃድ በሰኞ ማለዳ ከሰራተኞች ጋር በመገናኘት ለሳምንት ስራ ስንቅ የሚሆኑ የአዕምሮ ምግቦችን መመገብ ትልቅ የስራ መነሳሳት እንደሚፈጥር በመግለጽ ለውጤታማ ስራ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ አክለዉም ውጤታማ የስራ ሳምንት እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አበበ ቸርነት በጋር መስራትና ፋይዳዉ ፣ አገልጋይነትና መገለጫው ፣ ስለ አመራርነት እና ተያያዥ ስለሆኑ ጉዳዮች የተዘጋጀ አነቃቂ ሰነድ አቅርበዋል ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሱፐርቫይዘር አቶ ሰለሞን ወንድሙ በስራ ቆይታቸዉ ያጋጠማቸዉን ተሞክሮዎች እንዲሁም በጋራ መስራት የሚኖረዉን ጥቅም አስመልክተው ልምድ አካፍለዋል፡፡

ስራተኞችም በነበራቸዉ ቆይታ ደስተኛ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡
15.8K viewsAbebe Chernet, 07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-20 16:44:29
ዛሬ የጥምቀት እለትን ጨምሮ ቀንና ሌሊት ያለ እረፍት ፕሮጀክቶችንን እየገነቡ ካሉ ትጉህ ሰራተኞቻችን ጋር ምሳ በጋራ በመብላት የጥምቀት በዓሉን አክብረናል::

(ቀን ጥር 11/2016 ዓ.ም)  የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለማቅለል እና የከተማችንን ገፅታ ለመቀየር የጀመርናቸው ታላላቅ ፕሮጀክቶችንና ሰው ተኮር ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት በጥራት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ዉብ አበባ እናደርጋታለን።

ፈጣሪ የኢትዮዸያና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
12.8K viewsAbebe Chernet, 13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-20 14:54:53
የትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

(ቀን ጥር 11/2016 ዓ.ም)  የትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡ሲሆን

የተፈጥሮ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

የማኅበራዊ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል።

በዚህም የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል።

ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑንም ገልጿል።

የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያውቁት እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስባል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
18.1K viewsAbebe Chernet, 11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-19 11:36:14 በመጨረሻም ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለአየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ! እያልኩ በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ፡፡

አመሰግናለሁ!

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ

መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
15.6K viewsAbebe Chernet, 08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-19 11:35:59
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለበዓለ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!

(ቀን ጥር 10/2016 ዓ.ም) የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ እሴትነቱ ባሻገር ለማህበራዊ ትስስራችን መጎልበት ከፍተኛ ሚና ያለው ነው፡፡ በሀገራችን በአደባባይ ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል ከሀይምኖታዊ ስርዓቱ ባለፈ የሀገራችን ቱባ ባህላዊ ትእይንቶች ጎልተዉ የሚወጡበት ፣ ብሄር ብሄረሰቦች በአልበሳትና በብዝሃ ቋንቋቸዉ ደምቀዉ የሚታዩበት ፣ የኢትዮጵያዊነት ማሳያ የብዝኀነትና የአንድነት ነጸብራቅ በመሆን ያገለግላል፡፡

በጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች ተጋምደው አንዱ የሌላው ውበትና ጉልበት ድምቀትና ሕይወት የሚሆኑበት ብቻ ሳይሆን የአለምን አይን በሙሉ የሚስብ ታላቅ በዓል ነዉ፡፡ ለዛም ነው የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች በአለም ቅርስነት ተመዝግቦ በአለም አደባባይ ደምቀን እንድንታይ የሆነዉ።

በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ዘንድሮ ጥር 10 እና 11 ቀን የሚከበሩት የከተራ እና የጥምቀት በዓላት ከሃይማኖታዊ በዓልነት ባሻገር የሀገርን መልካም ገጽታን ከመገንባት እና የቱሪስት ፍሰትን ከማጎልበት አንጻር ጉልህ ሚና የሚጫወቱ በመሆኑ እንግዶችን በፍቅር ተቀብሎ በማስተናገድ በዓሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ በተለይም ደግሞ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ከፀጥታ አካላት ጋር እጅና ጋንት በመሆኑ መስራት ይኖርባችዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ብዝኀ ማንነቶቻችን በማክበርና አንድነታችን በማጠናከር የጋራ ቤታችን የሆነችውን ሀገራችንን ለማልማትና ሰላሟን ለማስጠበቅ ሁላችንም በአንድነትና በመከባበር እንድንቆም በዚሁ አጋጣሚ መልእክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ፡፡
13.8K viewsAbebe Chernet, 08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-19 10:25:12
(ቀን ጥር 10/2016 ዓ.ም)

መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
13.5K viewsAbebe Chernet, 07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ