Get Mystery Box with random crypto!

Addis Ababa Education Bureau

የሰርጥ አድራሻ: @wwwaddisababaeducationbureau
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 106.22K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-02-08 10:42:39
የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 4/2016 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

(ቀን ጥር 30/2016 ዓ.ም)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 4/2016 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
25.0K viewsAbebe Chernet, 07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-08 07:54:34
#ማ ስ ታ ወ ቂ ያ!

(ቀን ጥር 30/2016 ዓ.ም) ለድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ:-

የካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የ ድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ የመፈታኛ የይለፍቃል (Password) ከታችበተዘረዘሩት አማራጮች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. በምዝገባ ወቅት በሞላችሁት email በኩል

2. https://exam.ethernet.edu.et ላይ በመግባት የከፈላችሁበትን Transaction Number በማስገባት እንዲሁም

3. ከተመደባብችሁብት የመፈተኛ ተቋም ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ

• ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች የይለፍቃል (Password) የምታገኙት ከምትማሩበት ወይም ከተመደባብችሁበት የመፈተኛ ተቋም ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።

• ሁሉም ተፈታኞች የሞዴል ፈተናን እስከ የካቲት 5/2016 ዓ.ም መውሰድ ይኖርባቸዋል።

ትምህርት ሚኒሰቴር !

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
14.6K viewsAbebe Chernet, 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-07 20:56:15
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ጫወታን መሰረት ባደረገ የማስተማር ስነ ዘዴ ዙሪያ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህራን የሚ ሰጠው ስልጠና እንደቀጠለ ነው።

(ቀን ጥር 29/2016 ዓ.ም) ስልጠናው ከግል ትምህርት ቤት ለተውጣጡና ቀደም ሲል ስልጠናውን ላልወሰዱ መምህራን የተሰጠ ሲሆን ቀደም ሲል የአሰልጣኞች ስልጠና በወሰዱ መምህራን ስልጠናው መሰጠቱን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ስልጠናው መምህራኑ ተማሪዎቻቸውን ጫወታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነ ዘዴን ተከትለው ማስተማር እንዲችሉ በተግባር ተደግፎ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው ገልጸው በቀጣይ የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ከዚህ በፊት ስልጠና ላልወሰዱ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን ተመሳሳይ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑንም አስታውቀዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
14.2K viewsAbebe Chernet, 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-07 16:52:40 የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው ትምህርት ቤቶች የነገ የሀገር ተረካቢ ዜጎችም ሆኑ ተተኪ ስፖርተኞች የሚፈሩባቸው ተቋማት እንደመሆናቸው ቢሮው ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በትምህርት ቤቶች የሚገኙ የማዘውተሪያ ስፍራዎችን በማስፋፋትም ሆነ በተማሪዎችና መምህራን መካከል ስፖርታዊ ውድድሮችን በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በቀጣይ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚካሄደው የማለዳ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የስፖርት ሳይንስ መምህራን ሙያዊ ክህሎታቸውን የሚያሳድጉበት ስልጠና እንዲያገኙ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ባለፉት ሁለት አመታት ሁለቱ ቢሮዎች በጋራ ያከናወኑዋቸው እና በቀጣይ ትኩረት የሚደረግባቸውን ተግባራት አቅርበዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com
    
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
14.5K viewsAbebe Chernet, 13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-07 16:52:36
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በጋራ የሚያከናውኑዋቸውን ተግባራት መሰረት ያደረገ የስምምነት ፊርማ ተፈራረሙ፡፡

(ቀን ጥር 29/2016 ዓ.ም) የስምምነት ፊርማውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እና የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የተፈራረሙ ሲሆን መርሀ ግብሩ በቅርቡ በከተማ አስተዳደሩ በተደረገ የትምህርት ቤት አመራር ውድድር አልፈው ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙ ርዕሳነ መምህራን እና በየደረጃው የሚገኙ የሁለቱ ተቋማት አመራሮች በተገኙበት ነው የተካሄደው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በስምምነት ፊርማ መርሀግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ቤቶች የሚካሄድ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በአካልና አዕምሮ የዳበረ ትውልድ መፍጠር የሚያስችል ተግባር እንደመሆኑ ሴክተሩ ሪፎርም እያካሄደባቸው ከሚገኙ የትኩረት መስኮች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመው የትምህርት ቤት አመራሮችም በየትምህርት ቤቱ የሚካሄዱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ወጥ በሆነ መልኩ በማካሄድም ሆነ የማዝውተሪያ ስፍራዎቹን ለአከባቢው ማህበረሰብ በተለይም ለወጣቶች ክፍት በማድረግ ወጣቶቹ ከአልባሌ ቦታ መታደግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡
14.2K viewsAbebe Chernet, 13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-07 13:34:56
በቅርቡ በከተማ አስተዳደሩ በተደረገው የትምህርት ቤት አመራሮች ውድድር ወደ ርዕሰ መምህርነት ለመጡ የትምህርት ቤት አመራሮች የሚሰጠው ስልጠና ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡

(ቀን ጥር 29/2016 ዓ.ም) በስልጠናው የሶስተኛ ቀን ውሎ ለትምህርት ቤት አመራሮቹ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጡ ምሁራን በትምህርት አመራር (instructional leadership) ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰቱዋል ።

ስልጠናው ወደ አመራርነት እንደ አዲስ ለመጡትም ሆነ ቀደም ሲል በርዕሰ መምህርነት ሲያገለግሉ ለቆዩ አመራሮች ከትምህርት አመራር ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ ጨብጠው በተመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራውን በአግባቡ መምራት እንዲችሉ ታስቦ መሰጠቱን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ስልጠናው ለተከታታይ ስድስት ቀናት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን መሰረት አድርጎ የሚሰጥ መሆኑን ቀደም ሲል መገለጹ ይታወቃል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
14.5K viewsAbebe Chernet, 10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-05 17:24:05

13.0K viewsAbebe Chernet, 14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-05 15:47:39
የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና አባላት ታላቁን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ጎብኝተዋል::

(ቀን ጥር 27/2016 ዓ.ም) የዓድዋ ድል መታሰቢያ የኢትዮጵያውያን የአብሮነት፤ የአንድነትና የአሸናፊነት ተምሳሌት የሆነው የዓድዋ ድልን የሚመጥን እና ለትውልድ የሚተላለፍ ህያው ታሪክ ሆኖ መገንባቱን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላቱ በጉብኝት ወቅት ተናግረዋል::

የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው አባቶቻችን በህብረት ካገኙት ድል በመማር የእኛ ትውልድ ሃገርን ለማፅናትና ለነገው ትውልድ ለማስተላለፍ እንዲሁም የጀመርነውን የልማት ጉዞ ከግብ ለማድረስ በጋራ ልንቆም ይገባል ብለዋል::

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
13.6K viewsAbebe Chernet, 12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-05 13:44:23
የሰዓት አጠቃቀም ለውጤታማ ስራ ቁልፍ መሆኑ ተገለጸ፡፡

(ቀን ጥር 27/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከስራ ሰሃት መግቢያ በፊት ሰኞ ማለዳ በሚያዘጋጀው የሰራተኞች የጋር መአድ መቋደስ መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተካፍለዋል።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ እና ትግበራ ደይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጌታቸው ታለማ በሰዓት አጠቃቀም ጽንሰ ሀሳብና ተያየዥ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ሰራተኛው የሚያከናውናቸውን ስራዎች የላቀ ለማድረግ አንዱ ጉዳይ ሰዓትን በአግባቡ መጠቀም መሆኑን በመጥቀስ ሰዓትን በአግባቡ መጠቀም ለመደበኛ ህይወትም የሚኖረው ሚና ላቅ ያለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
12.7K viewsAbebe Chernet, 10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-05 11:52:49
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ በተደረገው የትምህርት ቤት አመራሮች ውድድር ወደ ርዕሰ መምህርነት ለመጡ የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና መሰጠት ጀመረ፡፡

(ቀን ጥር 27/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ በተደረገው የትምህርት ቤት አመራር ውድድር ወደ ርዕሰ መምህርነት ለመጡ የትምህርት ቤት አመራሮች ለስድስት ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀምራል።

ስልጠናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የሚሰጥ ሲሆን በስልጠና መድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የትምህርት ጥራትን ለማምጣትና ትውልድን በተገቢው ሁኔታ ለማነጽ ከዚህ በፊት በሚፈለገው ደረጃ ውጤት እንዳይምጣ ካዳረጉ ጉዳዮች መካከል የትምህርት አመራሩ በቁርጠኝነት ተቀናጅቶ አለመስራት ነዉ ያሉ ሲሆን ይህንን ክፍተት ለመሙላትና በትምህርት ዘርፍ ውጤት ለማስመዝገብ በውድድር ወደ ርዕሰ መምህርነት የመጡ የትምህርት አመራሮች በቁርጠኝነትና በብቃት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ሀላፊዉ አክለዉም ትውልድን ለመምራት የበቃና የነቃ እንዲሁም ተቀናጅቶና ተሰናስሎ መስራት የሚችል የትምህርት አመራር ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን ቢሮ ያዘጋጀው የስልጠና መርሀ ግብር በአዲስ የተደራጀዉን የትምህርት ቤት አመራር አቅም ለማጎልበት ያግዛል በማለት ለስልጠናዉ መሰካት አስተዋጽዎ ላበረከቱ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ለኮሜርስ ካምፓስ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
13.4K viewsAbebe Chernet, 08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ