Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ጫ | Addis Ababa Education Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ጫወታን መሰረት ባደረገ የማስተማር ስነ ዘዴ ዙሪያ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህራን የሚ ሰጠው ስልጠና እንደቀጠለ ነው።


(ቀን ጥር 29/2016 ዓ.ም) ስልጠናው ከግል ትምህርት ቤት ለተውጣጡና ቀደም ሲል ስልጠናውን ላልወሰዱ መምህራን የተሰጠ ሲሆን ቀደም ሲል የአሰልጣኞች ስልጠና በወሰዱ መምህራን ስልጠናው መሰጠቱን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ስልጠናው መምህራኑ ተማሪዎቻቸውን ጫወታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነ ዘዴን ተከትለው ማስተማር እንዲችሉ በተግባር ተደግፎ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው ገልጸው በቀጣይ የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ከዚህ በፊት ስልጠና ላልወሰዱ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን ተመሳሳይ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑንም አስታውቀዋል።



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!


What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/