በቅርቡ በከተማ አስተዳደሩ በተደረገው የትምህርት ቤት አመራሮች ውድድር ወደ ርዕሰ መምህርነት ለመጡ የትምህርት ቤት አመራሮች የሚሰጠው ስልጠና ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡ (ቀን ጥር 29/2016 ዓ.ም) በስልጠናው የሶስተኛ ቀን ውሎ ለትምህርት ቤት አመራሮቹ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጡ ምሁራን በትምህርት አመራር (instructional leadership) ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰቱዋል ። ስልጠናው ወደ አመራርነት እንደ አዲስ ለመጡትም ሆነ ቀደም ሲል በርዕሰ መምህርነት ሲያገለግሉ ለቆዩ አመራሮች ከትምህርት አመራር ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ ጨብጠው በተመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራውን በአግባቡ መምራት እንዲችሉ ታስቦ መሰጠቱን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ስልጠናው ለተከታታይ ስድስት ቀናት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን መሰረት አድርጎ የሚሰጥ መሆኑን ቀደም ሲል መገለጹ ይታወቃል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728 TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc 14.5K viewsAbebe Chernet, 10:34