Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በጋራ | Addis Ababa Education Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በጋራ የሚያከናውኑዋቸውን ተግባራት መሰረት ያደረገ የስምምነት ፊርማ ተፈራረሙ፡፡


(ቀን ጥር 29/2016 ዓ.ም) የስምምነት ፊርማውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እና የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የተፈራረሙ ሲሆን መርሀ ግብሩ በቅርቡ በከተማ አስተዳደሩ በተደረገ የትምህርት ቤት አመራር ውድድር አልፈው ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙ ርዕሳነ መምህራን እና በየደረጃው የሚገኙ የሁለቱ ተቋማት አመራሮች በተገኙበት ነው የተካሄደው፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በስምምነት ፊርማ መርሀግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ቤቶች የሚካሄድ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በአካልና አዕምሮ የዳበረ ትውልድ መፍጠር የሚያስችል ተግባር እንደመሆኑ ሴክተሩ ሪፎርም እያካሄደባቸው ከሚገኙ የትኩረት መስኮች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመው የትምህርት ቤት አመራሮችም በየትምህርት ቤቱ የሚካሄዱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ወጥ በሆነ መልኩ በማካሄድም ሆነ የማዝውተሪያ ስፍራዎቹን ለአከባቢው ማህበረሰብ በተለይም ለወጣቶች ክፍት በማድረግ ወጣቶቹ ከአልባሌ ቦታ መታደግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡