Get Mystery Box with random crypto!

Addis Ababa Education Bureau

የሰርጥ አድራሻ: @wwwaddisababaeducationbureau
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 106.22K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2024-01-13 17:47:28 መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com    
Instagram: -  https://www.instagram.com/aacaeb/
16.9K viewsAbebe Chernet, 14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-12 11:32:55 መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
14.5K viewsAbebe Chernet, 08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-12 11:32:49
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ህንጻ ግንባታ ያለበት ደረጃ ምልከታ ተካሄደ፡፡

(ቀን 3/5/2016 ዓ.ም) በምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳና ሌሎች የማህበሩ አባላት ተሳተፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ሁለገብ ህንጻ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት የመምህራን ማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ግንባታው በተያዘለት የማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ መሰረት እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን እንዲሁም ግንባታውን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 448 ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልግ በመግለጽ ለእቅዱ መሳካት የበጀት እጥረት እንቅፋት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ኮንትራክተር አቶ ሽመልስ በሰጡት መግለጫ የህንጻው ግንባት አፋጻጸም 20% መድረሱን ጠቁመዉ በቀጣይ ህንጻዉን ለማጠናቀቅ ካለዉ የኮንስትራክሽን እቃዎች የዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ የበጀት እጥረት መግጠሙን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ቢሮ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ማህበሩን ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን በመጥቀስ ማህበሩ በቀጣይ የተጀመረው ህንጻ እንዲጠናቀቅ ቢሮ ሊያግዝ የሚችልበትን ጉዳዮች ያካተተ ማስፈጸሚያ እቅድ በማቀድ እንዲያቀርብ አሳስበዋል፡፡

በምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለማህበሩ በቢሮነት እንዲያገለግሉ የሰጣቸው ክፍሎች የታዩ ሲሆን በቀጣይ መሰራት በሚገባቸዉ ጉዳዮች ላይ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
14.5K viewsAbebe Chernet, 08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-10 16:09:36 የሞዴል ፈተናው ተማሪዎች በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ ያላቸውን አቀባበል ለመገምገም እንደሚረዳ የገለጹት የአጠቃላይ ትምህርትና ፈተና ምዘና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ከዚህ ባለፈም ፈተናውን መውሰዳቸው በመንፈቀ አመቱ ያገኙትን እውቀት ለማየትና የበለጠ ለመስራት እንዲሁም ተማሪዎች ለከተማ አቀፍና ለብሄራዊ ፈተናዎች ራሳቸውን ለማዘጋጀት እንደሚረዳቸው አብራርተዋል፡፡ ተማሪዎችም የሞዴል ፈተናው በቀጣይነትም የሚሰጥ መሆኑን አውቀው የበለጠ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል፡፡

መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
14.7K viewsAbebe Chernet, 13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-10 16:09:27
የ6ኛ ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች መሰጠት ጀመረ።

(ቀን 1/5/2016 ዓ.ም) በከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ላይ 6ኛ፣ 8ኛና 12ኛ ክፍል በመማር ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ለከተማና ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች የሚያዘጋጃቸው ሞዴል ፈተናዎች መስጠት ጀምረዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርትና ፈተና ምዘና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እንዳሳወቀው ለ6ኛ ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለከተማ አቀፍና ለሃገር አቀፍ ፈተናዎች የሚያዘጋጁ የመለማመጃ ሞዴል ፈተናዎች በቢሮው በተዘጋጀ እቅድና ቢጋር መሰረት በ11ዱም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ካሉበት ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ያዘጋጇቸውን የሞዴል ፈተናዎች በየትምህርት ቤቶቹ እየሰጡ እንደሚገኝ አሳውቋል፡፡
14.1K viewsAbebe Chernet, 13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-10 12:12:38
ቀን 1/5/2016 ዓ.ም

መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
14.9K viewsAbebe Chernet, edited  09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-10 11:06:54
የኮሪያው አለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ(ኮይካ) በዳግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተለያዩ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን ሊሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

(ቀን 1/5/2016 ዓ.ም) በዛሬው ዕለት የኮሪያው አለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ(ኮይካ) ምክትል ዳይሬክተር ቾይ ህዬጄንግ እና ሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

በጎፍቃደኞች የቅድመ ዝግጅት ስራቸውን አጠናቀው ወደ ተግባር ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን በውይይቱ የገለጹ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ቢሮው የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ለኮሪያው አለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ(ኮይካ) ተወካዮች ገልጸዋል፡፡

መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
15.0K viewsAbebe Chernet, 08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-08 11:19:58
የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዋና እና የምክትል ርዕሰ መምህራን ውድድር የፅሁፍ ፈተና ውጤት ተገመገመ።

(ቀን ታህሳስ 29/2016 ዓ.ም) የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዋና እና የምክትል ርዕሰ መምህራን ውድድር የፅሁፍ ፈተና ውጤት አብይ ኮሚቴ በመሰብሰብ የገመገመ ሲሆን ኮሚቴው በቀጣይ መሰራት በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ የፈተና ውጤቱ ከዛሬ ጀምሮ ይፋ እንዲሆን ውሳኔ አሳርፋል፡፡

የፈተና ውጤቱን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫንና የፈተና ኮድ በማስገባት መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማስፈንጠሪያው፡- http://aaceb.gov.et/Result/

መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
14.7K views08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-06 12:24:00
ለክርስትና ዕምነት ተከታዩች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን !

(ቀን ታህሳስ 27/2016 ዓ.ም) በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በየዓመቱ የሚከበረዉ የገና በዓል ከሀይማኖታዊ በዓልነቱ ባለፈ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክር ነው፡፡ በዓሉ ለሌሎች ብርሀን በመሆን፣ ወንድማማችነትን በማጎልበት ፣ ፍቅርን በማብዛት እና እርስ በእርስ በመደጋገፍ የሚከበር በመሆኑ ለሀገር ሁለንተናዊ ግንባታ የሚኖረዉ ሚና የጎላ ነው፡፡

በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረዉ ይህ በዓል ያለንን ተካፍለን ፣ አቅመ ደካምችንና አረጋዊያንን አግዘን እንዲሁም የተቸገሩትን በመርዳት የምናከብረዉ እንደሚሆን እምነቴ ሲሆን በዓሉ በሠላም እንዲጠናቀቅም ሁላችንም ኃላፊነታችንን እንድንወጣ አደራ ለማለት እወዳለሁ።

በመጨረሻም ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን ! እያልኩ በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የመረዳዳት፣ የሰላም ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆን ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

አመሰግናለሁ!

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
16.1K views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-06 10:23:04
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለአቅመ ደካሞች እና አረጋውያን የማዕድ ማጋራት መርሀ-ግብር አከናወነ።

(ቀን ታህሳስ 27/2016 ዓ.ም) የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 እና 3 ስር ለሚገኙ አቅመ ደካሞች እና አረጋውያን የማዕድ ማጋራት መርሀ-ግብር አከናወነ።

በማዕድ ማጋራት መርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እንኳን አደረሳችሁ በማለት በቦታው ለተገኙ አካላት ቢሮ ከጎናቸው እንደቆመ በመግለጽ በቀጣይም ሰው ተኮር ስራዎችን መሰረት በማድረግ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ገልጸው በዓሉ ያማረና የደመቀ እንዲሆን ተመኝተዋል ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የዲሞክራሲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው ትምህርት ቢሮ ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎችን እየሰራ በመሆኑ ምስጋና አቀርባለሁ በማለት በቦታው ለተገኙ አካላት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል ።

በማዕድ ማጋራቱ ስነ-ስርአት ላይ የትምህርት ቢሮ የማኔጅመንት አባላት ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል ።

መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
14.1K views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ