የኮሪያው አለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ(ኮይካ) በዳግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተለያዩ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን ሊሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡ (ቀን 1/5/2016 ዓ.ም) በዛሬው ዕለት የኮሪያው አለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ(ኮይካ) ምክትል ዳይሬክተር ቾይ ህዬጄንግ እና ሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡ በጎፍቃደኞች የቅድመ ዝግጅት ስራቸውን አጠናቀው ወደ ተግባር ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን በውይይቱ የገለጹ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ቢሮው የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ለኮሪያው አለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ(ኮይካ) ተወካዮች ገልጸዋል፡፡ መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728 TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/ Website: - aaceb.gov.et Email;- aacaebc@gmail.com Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/ 15.0K viewsAbebe Chernet, 08:06