Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ህንጻ ግንባታ ያለበት ደረጃ ምልከታ ተካሄደ፡፡ | Addis Ababa Education Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ህንጻ ግንባታ ያለበት ደረጃ ምልከታ ተካሄደ፡፡

(ቀን 3/5/2016 ዓ.ም) በምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳና ሌሎች የማህበሩ አባላት ተሳተፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ሁለገብ ህንጻ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት የመምህራን ማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ግንባታው በተያዘለት የማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ መሰረት እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን እንዲሁም ግንባታውን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 448 ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልግ በመግለጽ ለእቅዱ መሳካት የበጀት እጥረት እንቅፋት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ኮንትራክተር አቶ ሽመልስ በሰጡት መግለጫ የህንጻው ግንባት አፋጻጸም 20% መድረሱን ጠቁመዉ በቀጣይ ህንጻዉን ለማጠናቀቅ ካለዉ የኮንስትራክሽን እቃዎች የዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ የበጀት እጥረት መግጠሙን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ቢሮ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ማህበሩን ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን በመጥቀስ ማህበሩ በቀጣይ የተጀመረው ህንጻ እንዲጠናቀቅ ቢሮ ሊያግዝ የሚችልበትን ጉዳዮች ያካተተ ማስፈጸሚያ እቅድ በማቀድ እንዲያቀርብ አሳስበዋል፡፡


በምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለማህበሩ በቢሮነት እንዲያገለግሉ የሰጣቸው ክፍሎች የታዩ ሲሆን በቀጣይ መሰራት በሚገባቸዉ ጉዳዮች ላይ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡