Get Mystery Box with random crypto!

ለክርስትና ዕምነት ተከታዩች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን ! (ቀን | Addis Ababa Education Bureau

ለክርስትና ዕምነት ተከታዩች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን !


(ቀን ታህሳስ 27/2016 ዓ.ም) በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በየዓመቱ የሚከበረዉ የገና በዓል ከሀይማኖታዊ በዓልነቱ ባለፈ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክር ነው፡፡ በዓሉ ለሌሎች ብርሀን በመሆን፣ ወንድማማችነትን በማጎልበት ፣ ፍቅርን በማብዛት እና እርስ በእርስ በመደጋገፍ የሚከበር በመሆኑ ለሀገር ሁለንተናዊ ግንባታ የሚኖረዉ ሚና የጎላ ነው፡፡


በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረዉ ይህ በዓል ያለንን ተካፍለን ፣ አቅመ ደካምችንና አረጋዊያንን አግዘን እንዲሁም የተቸገሩትን በመርዳት የምናከብረዉ እንደሚሆን እምነቴ ሲሆን በዓሉ በሠላም እንዲጠናቀቅም ሁላችንም ኃላፊነታችንን እንድንወጣ አደራ ለማለት እወዳለሁ።


በመጨረሻም ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን ! እያልኩ በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የመረዳዳት፣ የሰላም ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆን ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡


አመሰግናለሁ!


ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ




መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/