Get Mystery Box with random crypto!

የ6ኛ ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች መሰጠት ጀመረ። | Addis Ababa Education Bureau

የ6ኛ ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች መሰጠት ጀመረ።


(ቀን 1/5/2016 ዓ.ም) በከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ላይ 6ኛ፣ 8ኛና 12ኛ ክፍል በመማር ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ለከተማና ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች የሚያዘጋጃቸው ሞዴል ፈተናዎች መስጠት ጀምረዋል፡፡


የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርትና ፈተና ምዘና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እንዳሳወቀው ለ6ኛ ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለከተማ አቀፍና ለሃገር አቀፍ ፈተናዎች የሚያዘጋጁ የመለማመጃ ሞዴል ፈተናዎች በቢሮው በተዘጋጀ እቅድና ቢጋር መሰረት በ11ዱም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ካሉበት ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ያዘጋጇቸውን የሞዴል ፈተናዎች በየትምህርት ቤቶቹ እየሰጡ እንደሚገኝ አሳውቋል፡፡