Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ | Addis Ababa Education Bureau

የትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

(ቀን ጥር 11/2016 ዓ.ም)  የትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡ሲሆን


የተፈጥሮ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት


የማኅበራዊ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት


ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል።


በዚህም የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል።


ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑንም ገልጿል።


የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያውቁት እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስባል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!


You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau