Get Mystery Box with random crypto!

ለውጤታማ ስራ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ (ቀን ጥር 13/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ | Addis Ababa Education Bureau

ለውጤታማ ስራ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

(ቀን ጥር 13/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተነቃቃ የስራ አካባቢ እንዲኖርና በሚኖረው የልምድ ልውውጥ የተቀራረበ አስተሳሰብና የስራ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ለማድረግ እንዲያግዝ ሰኞ ሰኞ ከስራ ሰሃት መግቢያ በፊት ሰራተኞች በጋር እንዲገናኙ በሚያዘጋጀዉ የሰኞ ማለዳ የመአድ መቋደስ መርሃ ግብር ላይ የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት በመገኘት ከቢሮ ሰራተኞች ጋር መዓድ ተካፍለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃድ በሰኞ ማለዳ ከሰራተኞች ጋር በመገናኘት ለሳምንት ስራ ስንቅ የሚሆኑ የአዕምሮ ምግቦችን መመገብ ትልቅ የስራ መነሳሳት እንደሚፈጥር በመግለጽ ለውጤታማ ስራ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ አክለዉም ውጤታማ የስራ ሳምንት እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አበበ ቸርነት በጋር መስራትና ፋይዳዉ ፣ አገልጋይነትና መገለጫው ፣ ስለ አመራርነት እና ተያያዥ ስለሆኑ ጉዳዮች የተዘጋጀ አነቃቂ ሰነድ አቅርበዋል ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሱፐርቫይዘር አቶ ሰለሞን ወንድሙ በስራ ቆይታቸዉ ያጋጠማቸዉን ተሞክሮዎች እንዲሁም በጋራ መስራት የሚኖረዉን ጥቅም አስመልክተው ልምድ አካፍለዋል፡፡


ስራተኞችም በነበራቸዉ ቆይታ ደስተኛ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡